March 16, 2022
2 mins read

Ad ends in 17s የአማራ ልዩ ሀይል ተከዜ ብርጌድ ደመወዝና ሎጂስቲክስ መቋረጡ ተገለፀ

275846325 2790061484634435 4749141181291664791 nተወርዋሪው የአማራ ልዩ ኃልል ተከዜ ብርጌድ 3 ወር ሙሉ ደሞዝ መቋረጡንና እና ሎጅስቲክ አለመቅረቡ ተገለፀ። በአማራ ልዩ ሃይል ላይ የታቀደው ሴራ እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ የልዩ ሃይል አመራር እና አባላት ይሄን ጉዳይ ብስለት በተሞላበት መልኩ በመያዝ ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ተገልጿል።
በዚሁ ምክንያት ከባህር ዳር ጎንደር ዛሬ ከጧት ጀምሮ ትራንስፖርት ተቋርጦ ውሏል::
የአማራ ልዩ ሀይል ከተለያዩ ግንባሮች በክልሉ መንግስት በቂ ድጋፎች እየተደረገላቸው ባለመሆኑ ሰላም የማስከበር ስራ አንሰራም በማለት ለክልሉ መንግስት ቅሬታ ለማቅረብ ወደ ባህር ዳር እየተጓዙ ባለበት ወቅት አዲስ ዘመን አካባቢ ከመንግስት አካላት በቀረበላቸው ጉዳዩን በውይይት እንፍታው የሚል ጥያቄ መሰረት ውይይት እያካሄዱ በመሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ የአዲስ ዘመን ከተማ ብልጽግና ሀላፊ አቶ ምስጋናው ማስረሻ ለአሻራ ሚዲያገልጸዋል::
ሀላፊው ለትራንስፖርት መቋረጡ በምክንያትነት ያነሱት ለቅሬታ ከመጡ የልዩ ሃይል አባላት ጋር የሚደረገው ውይይት አስፓልት ላይ በመሆኑ ነው የሚል ምላሽ ሰጠዋል::
ውይይቱ ለሁለት ቀን ያክል አስፓልት ላይ እየተካሄድ መሆኑን በመግለጽ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ተኩስ ተከፈተ የሚባለው ወሬ ውሸት ነው ሲሉም ተናግረዋል ::
አሻራ ሚዲያ 

 

1 Comment

  1. While the other regional special forces are maintained the Amhara special forces should not have any problem.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በኢትዮጵያ እና ህዝብ ላይ ለደረሰዉ እና ለሚደርሰዉ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚወስደዉ  ማን ነዉ ? -ማላጂ

138368
Next Story

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አፈናና የተማሪና ወላጅ ተስፋ ያጨለመው ውሳኔ | Hiber Radio

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop