March 14, 2022
12 mins read

አንተም ተው አንተም ተው

223333 [email protected]

ባለፈው በአበበ ገላው ቡድንና በኤርምያስ ለገሰ መካክል መወነጫጨፍ ተጀምሮ ወደ ክስ ማምራቱን ሰምተን እልኻቸው ሲበርድ ተስማምተው ለዚች አገር ዉል ያለው ስራ ይሰራሉ ብለን ብንጠብቅም ነገሩ ስር በስር እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ መዝገብ ተከፍቶ፤ እማኞች ተጠርተው በፈረንጅ ፍርድ ቤት ሊዳኙ ቀጠሮ መያዙን እያዘንን ሰማን። በስንቱ ሃገር የተቀጣጠለውን እሳት ያጠፋን ኢትዮጵያዉያን እሳቱ እኛው መሀል ገብቶ ሲፈጀን እያየሁ መቀመጥ ስላላስቻለኝ ቢሰሙኝ ብዬ ባድራሻቸው ሊደርስ ይችላል በሚል ግምት ወደ ድር ጥንጥን መልእክቴን ላክሁ።

በአንድ ወቅት ኤርምያስ ለገሰ የግምቦት 7 አባሎች፤ የዲሲ ግብረ ሀይልና ካምፓኒያቸው በስልክና በተለያየ የመገናኛ መስመሮች  ያስፈራሩኛል አሜሪካ የሰጠችኝን መብት ተጋፍተውኛል በማለት በሚሰራበት ሚዲያ ወገን እንዲያዉቅለት ከገለጸ በኋላ አበበ ገላው ኤርምያስ ለገሰን የዲሲ የህወአት ሰው፤ የበረከት ስምኦን ተወካይ በማለት የመልስ ምት ሰጠ። ነገሩን በመለጠጥም እንግሊዝኛ ያለ መቻሉንም ጠቆም አድርጎ አለፈ። ይህንን ታክኮ ደረጀ ሀብተወልድም ኤርምያስ ዶ/ር አብይን አላግባብ ተጋፋው በማለት በአንድ ዝግጅቱ ብቀላ በሚመስል መልኩ የአማራና የኦሮሞ ጠላት አድርጎ በቅንብር አቀረበው።

እንግዲህ የዚህ ነገር ክሩ ሲመዘዝ ለኢትዮጵያ ምንም ፋይዳ ላልሰራውና ለኢትዮጵያ እዳ ከሆነው የግምቦት 7 ድርጅት ጋር መያያዙን የኢትዮጵያ ፖሊቲካን ለተከታተለ እምብዛም ስውር አልነበረም።  አበበ ገላው፤አንዳርጋቸው ጽጌ፤ነአምን ዘለቀ፤ብርሃኑ ነጋና መሰሎቻቸው በኢሳት ቆይታቸው ለኤርምያስ ሰፊ ሽፋንና የአየር ሰአት ሲሰጡት ከበረከት ስሞን ጋር መስራቱን ሳያውቁ ቀርተው አልነበረም እንደውም የገረማቸው እንዲህ ያለ ወምበር ጥሎ መሰደዱን ነበር። በእርግጥ እንደ ኤርምያስ ያለ ከአንድ አርስት ወደ ሌላ አርእስት እራሱን እየወረወር ማብራሪያ የሚሰጥ ተንታኝና ጋዜጠኛ በእውቀትና በልምድ እራሱን የካበተና የአይን ምስክርነቱን የሚሰጥ እውር ድምብሩ የጠፋውን ኢሳትን ጥሎ ሌላ ሚዲያ መመስረቱ ድንጋጤ መፍጠሩ አይቀሬ ነበር።

ኤርምያስ ከወያኔ ጋር ሰርቷል አንዳርጋቸውም ወያኔ ሲደናበር ጣቱን ይዞ ለአዲስ አበባ ህዝብ አስተዋዉቆታል፤ ዶ/ር ብርሃኑም መለሰ ዜናዊ አላመነውም እንጅ በህወአት አካባቢ ዉር ውር ሲል ነበር የዩኒቨርስቲ መምህራን ሲባረሩም መለስ ዜናዊን ለማስደሰት ገብቶ ሲሰራ ነበር። ኤርምያስን ከነ ግምቦት 7  የሚለየው እነ አንዳርጋቸው ጽጌ ህብረተሰቡን የሚከፋፍል ጽሁፍ እየጻፉ ልዩነትን መተዳደሪያቸው ሲያደርጉ ኤርምያስ ለገስ በተጻራሪው የህወአትን ክፉ ስራ ነቅሶ የህወአት አገዛዝን ብትንትኑ እንዲወጣ የረዳ ዜጋ ነበር። እንደሚባለውም የመጽሃፉን ሺያጭም ለኢሳት እንዳዋለው ከሌሎች ሲነገር ተደምጧል። ዛሬ ኤርምያስ ብቻውን የቆመ ይመስላል የግምቦት 7፤ የኢሳት፤ የዲሲ ግብረ ሀይል በጠንካራ የእውቀት መሰረት ላይ ቁመው ኤርምያስን ከመሞገት ይልቅ የነሱ አለቆች ወያኔና ሻቢያ ጋር እንዳልሰሩ ሁሉ እሱን ባለፈ ስራው ሊያሸማቅቁት ይሞክራሉ። በህወአት ቁጥር 1 እድሉ ያመለጣቸው ግምቦቶች በህወአት ቁጥር 2 ስልጣን የተሰጣቸው ተሰጥቷቸው ያላገኙት ሽራፊ ስልጣን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። አበበ ገላው ኤርምያስ እንግሊዝኛ አይችልም ያለው በሱ ደረጃ ይህ አስተያየት ባይሰጥ መልካም ነበር እሱም በተለያየ ጊዜ እንግዶችን በእንግሊዝኛ ሲጠይቅ እንደ ሰሚ ያስተዋልነውን አስተውለናልና።እዚህ በፈረንጁ አለም ተወልደው የኛም ልጆች በተፈለገው ደረጃ የቋንቋው ክህሎት ላይ አልደረሱም እንግሊዝኛን አቀላጥፎ አለመናገርም የእውቀት መስፈርት ተደርጎ ባልተወሰደም ነበር።

እዚህ ላይ አበበ ገላው  ደጎስ ያለ መጽሃፍ ባይደርስም በተክታታይ የፖለቲካ ትንተናዎች ላይ እንደ ኤርምያስ ባናየውም  ለኢትዮጵያ ህዝብ የዋለው ዉለታ ግን እንዲህ በቀላሉ ሊረሳ አይገባም። አበበ ገላው ያንን የመርዝ ብልቃጥ በጌቶቹ መሀል ያለ አቅሙ ተኮፍሶ ቁጭ ባለበት በዛ ሃያል ድምጹ የኢትዮጵያ አምላክ ታክሎበት ላይመለስ የሸኘልን የክፉ ጊዜ ወንድማችን ነው። ይህ ጀግና ዉለታውን ኢትዮጵያ ትክፈለው ከማለት ሌላ ምን ይባላል? ይህ ገድሉ በታሪክ ሲጠቀስም ይኖራል።  ታዲያ የዚህን ግፈኛ ሰው (መለሰ ዘራዊን) አስመልክታ ሰላም በያን የምትባለው ምሁር ያበበ ገላውን ገድል ዉብ በሆነውና በተካነችበት የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲህ አድርጋ አቅርባዋለች አንብቡት ሳይሆን አጥኑት እላለሁ።The Cause of Zenawi’s Death and Its Import | Ethiopian Uprising (wordpress.com) አቤም እንግሊዝኛን አድናቂ ከሆነ ይህን ጽሁፍ ያንብብ።

አንድ ነገር ሳይጠቀስ ሊታለፍ የማይገባው ኤርምያስ ለገሰ ወከባ በበዛበት ጊዜ ይህን አጋጣሚ ሲጠብቅ የነበረው ቴዎድሮስ ጸጋዬ በተደጋጋሚ ጋብዞት በመሪ ጥያቄ እየነዳ በይሉኝታና የእሱ ያልሆነውን ሃሳብ እንዲናገር በመሰሪ አቀራረቡ መጥለፉንም ማስታወስ እንፈልጋለን ይህ ሃብታሙንም ይጨምራል። ሲጀመር ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰዉ ወይም ተቋም በቴዎድሮስ ጸጋዬ ቦይ መፍሰስ አልነበረበትም። ኢትዮ 360ም ማንኛውንም ትንተና የሚዲያ ደረጃውን በጠበቀ  መልኩ ቢቀርብልን መልካም ነበር። የምንኖረው በምእራቡ አለም ሁኖ በእነሱ ደረጃና ከዛም በላይ መሆን እየተቻለ አንዳንድ ብሽሽቅ የመሰለ ነገር አቀራረብ ላይ ባይስተዋል መልካም ነበር። እዚህ ላይ የስራ ጫናችሁንም እንገነዘባለን በብዙ ሰራተኞች የሚሰራውን ስር በጥቂት ወገኖች ወደኛ ለማድረስ የምትደክሙትንም ጥረት ዘንግተን አይደለም በተቻለው ሁሉ ተቸገሩልን ማለታችን እንጅ።

ባጠቃላይ ዛሬ ኢትዮጵያ የነበረች ሃገር ሳትሆን ገና ልትመሰረት ዝግጅት የተጀመረባት ይመስላል። የሰሜን የባህር በራችን በትግሬዎች ለሻቢያ ተሰጥቷል፤ ስዩም መስፍንም ባድሜና ሽራሮ የትግሬ ግዛት አይደሉም ብሎ ለላይኛዉ ወገኖቹ አስረክቧል፤ የባንዳ ልጆች ብሄራዊ ክብረ በአል በደረሰ ቁጥር መሸማቀቁ ስለበዛባቸው ኢትዮጵያን አፍርሰው እፎይ ማለትን መርጠዋል። ፈረንጆችም በሃሳብ የተጎዱ ዜጎችን ተረት እየጋቱ አገራቸውና ወንድሞቻቸው ላይ እንዲዘምቱ አድርገዋል፤ ታሪካው ጠላቶቻችን አረቦችም የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቅም አጥሩን በመነቅንቅ ላይ ናቸው። በዚህ ላይ መንግስት ለመኖሩም እርግጠኛ አይደለንም። ሹመት በዘር ነው አምባሳደሮቻችን ከኢትዮጵያ በተጻረረ መልኩ መግለጫ ሲስጡ (ሱሌማን ደደፎ፤ ሌንጮ ባቲ) አበጀህ ይባላሉ፤ መልካም ሰዎችና ህዝብ ተስፋ የጣለባቸው ወይ ይገደላሉ ወይ ወደ ጎን ይገፋሉ(ዶ/ር ስለሺ በቀለ፤ሙስጠፌ …) ዜጎች እንደ አዉሬ ሲገደሉ ለመንግስት ምኑም አይደለም።

ታዲያ አገር እንዲህ ምስቅልቅሏ በወጣበት ሰአት ለሀገራችን አብረው ቢሰሩ ብዙ ሊጠቅሙ የሚችሉ ኤርምያስ ለገሰና አበበ ገላው አስፈላጊ ባልሆነ እሰጥ አገባ ተጠምደው ጊዜያቸውን ማባከናቸው ልብን ያደማል። ኤርምያስም ሆነ አበበ ገላው መልካም ዜጎች ስለሆናችሁ ሁለታችሁም ሰይፋችሁን ወደ ሰገባው መልሳችሁ ለሃገራችሁ ትደክሙ ዘንድ በኢትዮጵያ ስም እንጠይቃለን። በተከፈተው ፋይል አገራችን ውስጥ አለም አቀፍ ወንጀልን የፈጸሙ፤ ዜጎችን ያረዱ፤ያቃጠሉ፤የሰቀሉ ወንጀለኞች በስልጣንና በጫካ በመኖራቸው የናንተን ፋይል ዘግታችሁ ወደዚህኛው ብታተኩሩ ምስጋናችን የበዛ ይሆናል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር [email protected]

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop