የምንለዉ “ የኑሮ ዉድነት ወይስ የህልዉና ሥጋት?”

በእኛ አገር መኖር እንደሬት መምረር የጀመረዉ ብዙዉን  ኢትዮጵያዊ አማኝ እና መናኝ አድርጎ የማየት የፖለቲካ ሴራ ገመድ ከተሸረበበት ጊዜ አንስቶ እንደነበር ከኋላ ታሪክ መረዳት እና ማየት ግድ ይላል፡፡

በአንድ አገር ግዛት እና አስተዳደር አንድን ህዝብ ገባር እና ነባር በማድረግ ጥገኛ አደር እንዲሆን የተደረገዉ በክፉ አሳቢ እና ተሳቢ ተባባሪዎች የግፍ እና ጭቆና ጫና እንዲሸከም ከተፈረደበት ከጭለማዉ ዘመን መባቻ ከግንቦት ፳ ቀን ፩ ሽ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት ዓ.ም. ጀምሮ አስከዛሬ ነዉ ፡፡

የኑሮዉ መጎምዘዝ ስሜት፣ ዓይነት እና ብዛት ይለያይ እንጂ ሠዉ ሠራሽ መሆኑን ሠዉ ለሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ መረዳት አይገድም፤ አዲስ ክስተትም  አይደለም ፡፡

ኑሮ የሚወደድ እኮ በመኖር ነዉ ፡፡ መኖር እና ሠባዊ ነፃነት በክፉዎች ችሮታ በሚቸበቸብበት አገር ኑሮ ይወደዳል ወይም ያጓጓል ማለት ልማድ የሆነ ሠሞነኛ ስሙኝ ባይነት  ነዉ ፡፡

የዋጋ ንረት ለማለት ከሆነ በኢትዮጵያ ሠዉ እና ብር እንዲረክስ የተጠነሰሰዉ ያኔ መሆኑን እና ከዚያ አስከዛሬ የወረደ ኢትዮጵያዊነት እና የተዋረደ ዜጋ እንድንሆን ሲሰራ መኖሩን ክደን ኑሮ ተወደደ ምክነያቱ ፍላጎት እና አቅርቦት መራራቅ እያሉ ከመዘባረቅ  እያሉ መሳለቅ እና ለዕዉነኛ መንስኤ እና መፍትሄ ለመቆም አለመቻል ዛሬም ያስተዛዝባል፡፡

መኖር በሌለበት ስለኑሮ ዉጣዉረድ መዘባረቅ ከዕዉነት እና ከህዝብ መራራቅ ከማስከተል ዉጭ ጉንጭ ማልፋት ነዉ ፡፡

ኑሮ ተወደደ ማለት ኢትዮጵያዊነት ወደቀ ለማለት ከሆነ ከመዉደቃችን በፊት እጂ ለእጂ ተያይዘን እንበርታ ሲባል እኔ ከሞትኩ …ሠርዶ አይብቀል …እንዳለችዉ በምን ቸገረኝ ልማድ ከተተበተበ ያኔም ሆነ ዛሬ መላ መጠበቅ የድንቁርና ከዳሚነት ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አትሌት ሽህ አለቃ ደራርቱ ቱሉ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈች

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ከሶስት አሰርተ ዓመታት በላይ በናት አገርምድር ላይ መፃተኛ እና ባይታዋር ሆነዉ በሚሳደዱባት እና በሚሞቱባት አገር ላይ የዕለት እንጀራ በልቶ ማደር ታሪክ ቢሆን ምን ይገርማል፡፡

የሠራ በማይከበርባት እና በማይወደስባት፣ የተዘራ በሚመክንባት፣ የዘረፈ በሚከብርባት ፣ሰርቶ ያገኘ በጉልበተኛ ጠሚቀማባት ፣የአገር እና ህዝብ ጠላት -ገዳይ በአገር ክህደት ክህደት እና  ህዝብ ሞት በሚፈነጭባት ኢትዮጵያ ኑሮ ሲወደድ(ሲያጓጓ) ማለት በህልም ቅቤ መጠጣት ነዉ ፡፡

የዜጎች በአገራቸዉ ሠርተዉ ለሚያገኙት አንጡራ ሀብት ተጠቃሚ እና ባለመብት ሊሆኑ ቀርቶ በህይወት ዉሉ ማደር ብርቅ እና እንግዳ አስከመሆን በሚታይባት አገር የሠዉ ልጂ ህይወት እንደዋዛ በማንአለብኝነት በሚያልፍባት ፤ ዕንባ እና ደም በጋ ከክረምት እንደሚፈስ ጅረት ከዓመት ዓመት በማይቐረጥባት አገር እና ምድር ዕህል ዉኃ ማለት እንዴት ይሆናል፡፡

ሠዉ በአገሩ ለመኖር ምኞት በሆነባት አገር ከዉጭ የሚገኙ እና በስደት ዓለም የነበሩት ይምጡ ስንል በአገር ዉስጥ ፲፪ አስከ ፳ ሚሊዮን የሚቆጠር የአገር ዉስጥ ስደተኛ በር እየዘጋን ስለ ስኳር እና ዘይት ማጮኸ ልማዳችን ካልሆነ በቀር መዳኛችን ሆኖ ዘላቂ መፍትሄ ችግር ሆኖ አያዉቅም ፤አይሆንም ፡፡ እየየም ሲደላ ነዉ መጮህም እኮ በመኖር ነዉ ፡፡

መኖር አለመኖር የተፈጥሮ ህግ እና ሠባዊ መብት ሆኖ ሳለ በክፉ መንፈስ የጥፋት እና ሞት ጌኛዎች መሽቶ አስኪነጋ የመከራ እና የሞት ከበሮ በሚደለቅባት አገር ስለመኖር ፤አለመኖር ዝም ያልን እና ዉኃ፣ ማር..ቅቤ ለምን ጠፋ ያላልን ዘይት …. ጠፋ መንጫጫት ለዓመታት ሰያበብስ እንጂ ችግር ሲያስታግስ አልታየም፡፡  ስንሞት እና ስንጠፋ ያልነበርን ሲርበን በችርቻሮ ማልቀስ ከድህነት ቀርቶ ከሞት አልታደገንም፤ አይታደገንም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአንድ ሳምንት የጦር ድል|ዶ/ር ይልቃል ትኬት ቆረጠ | ደመቀ አማላጅ ሆነ | ፋኖ ዕቅዱን ይፋ አደረገ

ነፃነት እና መብት ባልተረጋገጠበት የሆድ ችግር ዕልባት ለማስገኘት መሞከር ጉም ከመዝገን አይለይም እና በቅድሚያ እየኖርን መሆኑን እርግጠኛ ሆነን ስለ ኑሮ ዉጣ ዉረድ ( መወደድ፤መጠላት) ይታሰብበታል፡፡ ከዶሯዋ ካልተማርን እንዴት ከራሳችን ችግር እንማራለን፡፡ ዶሯዋ ርቧት ኖሯል  ጌታዋን ገብስ ስትል ጠይቃ  ለፍስለታ (ከነሃሴ አጋማሽ) ስትባል“ እኔ እምሞት ዛሬ ማታ ገብስ የሚደርስ ዛሬ ማታ ” አለች አሉ ፡፡ ስንዴ ፣ስኳር፣ዘይት….እየመጣ ነዉ  ላለፉት ረጅም ዓመታት ጀምሮ አስካሁን ይጓዛል  ፤ይመጣል የሞኝ ዘፈን ሆኖ “ ወንዝ ነዉ ዕድሜ ልክ ይጓዛል ”  ኢሀዴግም ይላል አንድ ቀን ይደርሳል ከሌለሁ ይቀራል ፡፡ እና ወንዙን ስንጠብቅ ዓመታት ነጉደዋል እኛም የጃችንን ብንቆምም ወድቀናል ፤ ብንቀሳቀስም ተንቀሳቃሽ በድን ስም የለሽ  ሆነናል፡፡

ማላጂ

“ምንጊዜም ኢትዮጵያ ”

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share