ዘ-ሐበሻ (Zehabesha.com) ርእስ አንቀጽ

መረጃ ኃይል ነው። በብዙ የሰለጠኑ አገራት መረጃን የሚያቀርቡ  ሜዲያዎች ከሕግ አውጭው፣ ከሕግ አስከባሪዉና ከሕግ ተርጓሚው የመንግስት ሶስት ቅርንጫፎች በተጨማሪ አራተኛው የ”መንግስት” ቅርንጫፍ ተደርገው የሚቆጠሩ ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የሕዝብ ሜዲያዎች የመንግስት ፕሮፖጋንዳ መሳሪያዎች የሆኑበት፣ የግል ሜዲያዎችም ከፍተኛ ጫናና እንግልት የሚደርስባቸው አገር ሆና ነው የቆየችው።

ዘ-ሐበሻ፣ ይሄንን ክፍተት በተወሰነ መልኩ ለመምሏት፣ በኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ፣ ላለፉት አስራ ሰባት አመታት ፣ በኢትዮጵያ ፍትህ፣ ሰላም፣ እድገትና ዴሞክራሲ እንዲኖር፣ ኢትዮጵያዉያን በአገራቸው ጉዳይ ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲያገኙ ለማድረግ በመስራት ላይ ያለ ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ከገዢዎች ሆነ ከፖለቲካ ድርጅቶች ተጽኖ ውጭ የሆነ ሜዲያ ነው፡፡

Zehabesha.com፣ ዘ-ሐበሻ ትዩብ  (Zehabesha Tube)  በሚል በዘ-ሐበሻ ስም በመጀመሪያ የተከፈተ የዩቱብ ቻናል አለው

ሆኖም  ብዙ  በዘሐበሻ  ወይም ሃበሻ ስም በርካታ ድህረ ገጾች ፣ዩቱቦች ፣ የፌስቡክ አካውንቶች ተከፍተዋል። ሐበሻ ትዩብ ፣ ዘ-ሐበሻ 1፣ ዘ-ሐበሻ 2፣ ዘ-ሐበሻ 3፣ ዘ-ሐበሻ 4 , Habesha  Market and Zehabesha Restaurant   የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል።

በነዚህ ሜዲያዎች የሚቀርቡ ዝግጅቶችና የሚተላለፉ መልእክቶች፣ “ዘ-ሐበሻ ” በሚል ስለሆነ፣ የኛን ሜዲያ ከነዚህ ሜዲያዎች ጋር አንድ አድርጎ የመውሰድ ሁኔታ በአንዳንድ ወገኖች እያየን ነው።

በዚህ አጋጣሚ በነዚህ በዘ-ሐበሻ ስም በሚንቀሳቀሱ ሜዲያዎች የሚቀርቡ መረጃዎች ሆነ ዝግጅቶች የ Zehabesha.com፣ እና ዘ-ሐበሻ ትዩብ (Zehabesha Tube) እንዳልሆነ በአክብሮት ለመግለጽ እንወድለን።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው፣ በዶር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት አገርን ወደ ከፋ ደረጃ እየወሰደ ነው የሚል እምነት ነው ያለን። በብዙ የአገራችን ክፍሎች እየሞቱ፣ እየተፈናቀሉ፣ ለረሃብ ለጠኔ እየተጋለጡ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት እየተፈጸመባቸው ያሉ ዜጎች ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  በትህነግ የጦርነት ክተት አዋጂ  “ወራሪ እና ተስፋፊ ” ማን ነበር ? - ማላጅ

መንግስት ነን ብለው በሃላፊነት ላይ የተቀመጡ መሪዎችም፣ ለሕዝብ ሰቆቃ ትኩረት ከመስጠት፣ የሕዝብን ችግር ከመፍታት፣ ጊዜና ጉልበታቸውን፣ የአገርንም ሃብት፣ አላስፈላጊ ድግሶች፣ ፊስቲቫሎች የመሳሰሉት ላይ ማባከናቸው፣ ከነርሱም ብዙዎቹ የሕዝብ ሃብት የመዘበሩና የሚመዘብሩ፣ ለመመዝበርም ሁኔታዎች የሚያመቻቹ ፣ ከተጠያቂነትና ከሕግ የበላይነት ውጭ  መሆናቸው  በእጅጉ ያሳስበናል።

በየጊዜው ለሰላምና ለፍትህ ለዜጎች እኩልነት እየጮኹ ባሉ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲካ መሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ወከባ፣ እንግልት፣ እስርና ግድያን አጥብቀን እንቃወማለን።

አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች፣ ከህወሃት ጋር ይሰሩ የነበሩ ናቸው:፡ ሆኖም ከአራት አመት በፊት በሕዝብ ትግል፣ ተፈናጠው ፣ ከሕወሃት የተለየን ነን ብለው በመቅረባቸው፣ በብዙዎች ዘንድ ታምነው ነበር፡፡ የለውጥ ተስፋም ታይቶ ነበር።

ነገር ግን ከተጠበቀው፣ ከታሰበውና ተስፋ ከተደረገው በእጅጉ የተቃረነ ሁኔታ ነው የተፈጠረው። በሕወሃት/ኢሕአዴግ ዘመን ከነበረው እጅግ በባሰ አደገኛ ሁኔታ ላይ  ነው ኢትዮጵያ የምትገኘው፡፡ ከአራት አመት በፊት መጣ የተባለውም ለውጥ ሙሉ ለሙሉ ተቀልብሷል ማለት ይቻላል።

በመሆኑም እስከአሁን እያደረግን ያለውን በተጠናከረ መንገድ እያደረግን፣ ታማኝነታችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደመሆኑ፣ ለሕዝብ ድምጽ መሆናችንን እንቀጥላለን። ሕዝብ እውነትን እንዲያውቅ፣ መረጃዎችን እንዲያገኝ ነጻና ገለለተኛ በሆነ መልኩ እንሰራለን።

አልዩ ተበጀ  የzehabesha.com መስራች እና ዋና አሳታሚ 

Terms & Conditions

1 Comment

  1. አቶ አልዩ፦
    መልእክትህ በጣም ገላጭ ስለሆነ እናመስግናለን፡፡ የረዥም ጊዜ የዘሀበሻ ደጋፊና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ግን የዘሀበሻ ወቃሾቹ ከሆኑት ውስጥ አንዱ እኔ ነበርኩ፡፡ አሁን በርእሰ አንቀጹ በተገለጸው መሰረት ቢያንስ ኢትዮጵጵያዊነትን ገድሎ አገሪቱን ኦሮማዊት ለማድረግ ከኦነግና ወያኔ ጋር ድብቅብቅ ያለ ሴራና አሻጥር እየሾረበ ያለውን የኦሮሙማውን ቁንጮ አብይ አህመድንና ቡድኑን በይፋ በማጋለጣችሁ አቋማችሁን ተረድተናል፡፡ተግባብተናልም፡፡
    እውነቱን ፍርጥ ለማድረግ ካስፈለገም ከጥቂት ሆዳሞች በስተቀር አብይ አህመድና ኩባንያው ጸረ ኢትዮጵያ ስለሆኑ ራቁታቸውን ይቀራሉ፡፡በህዝቡ ትግልም ይንኮታኮታሉ፡፡
    ከሰላምታ ጋር
    መኮነን በረደድ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share