March 12, 2022
1 min read

የብልጽግና ፓርቲ ኮንግረስ አብይ አህመድን ፕሬዝዳንትአድርጎ መረጠ

275661939 508294267491561 5477151793991036021 n

አንደኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ብልጽግና ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ፕሬዝዳንት አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ አደም ፋራህን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።
አንደኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ብልጽግና የፓርቲውን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ምርጫ እያካሄደ ነው።
በዚህም መሠረት
ለፕሬዝዳንትነት በሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ የተጠቆሙት
ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ናቸው።
በጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ዑሞድ ኡጅሉ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት የተጠቆሙት
አቶ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰን ለምክትል ፕሬዝዳንትነት የተጠቆሙት
አቶ አደም ፋራህ ናቸው።
በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት የተጠቆሙት
አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው።
በአሁኑ ሰአት ለጉባኤተኛው ድምጽ መስጫ ወረቀት እየተሰጠ ነው።
ውጤቱን ይዘን እንመለሳለን።
(ኢ.ፕ.ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop