ፅንፈኝነት ሰላምንም ሆነ ፍትህን እውን ሊያደርግ አይችልም!!!

ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት ተፈፅሟል::

በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተንቀሳቃሽ ምስል ሲዘዋወር በቆየው እጅግ አሰቃቂ ድርጊት ንፁሃን ዜጎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ሲደረግ ታይቷል።
ይህ ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት ባህል፣ እሴትና ከማንኛውም የሰብአዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው።
ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትህን እዉን ሊያደርግ አይችልም:: በመሆኑም ሊኮነንና ሊወገዝ ይገባል::
መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸዉ ምንም ይሁን ምን መንግስት ይህን አይነት ፍፁም ከሰብአዊነት የራቀና ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ህገ ወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከልም ከክልሉና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ ይገኛል።
የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን መንግስት ከዚህ በኋላ አይታገስም።
ስለዚህ እነዚህ በወንጀል ስራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት በጥብቅ ያሳስባል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Amhara PP
ተጨማሪ ያንብቡ:  UN: 9 million need aid in drought-hit East Africa

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share