February 16, 2014
9 mins read

ሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤ/ክ ለሰላምና ለአንድነት ከቆሙ ምእመናንን የተላለፈ ማብራሪያ

02/14/2014
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

በቤተክርስቲያናችን የውስጥ ጉዳይ የመጨርሻ ውሳኔ ሰጪ አካል የቤተክርስቲያናችን ጠቅላላ ጉባዔ ብቻ ነው።
በቅርቡ በፍርድ ቤት የተሰጠውን የአስቸኳይ እገዳ ይጣልልን ጥያቄ ላለመቀበል የወጣውን ትእዛዝ አስመልክቶ ማብራሪያ።

የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ እንደመጨረሻ ውሳኔ ቆጥሮ መፈንጠዝ የሕግን አካሔድ አለማወቅ ስለሆነ ብዙም አያስደንቅም። ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትእዛዝ በቀረቡት የክስ ጭብጥ ሃሳቦች መሠረት ሊተካ ወይንም ሊጠገን የማይችል ጉዳት የሚያደርስ ሁኔታ ስለሌለ አስቸኳይ እገዳ ይጣልልን ተብሎ ለቀረበው አቤቱታ የተከበረው ፍርድ ቤት ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢና የማይተካ ጉዳት ያመጣል ብሎ ስላላመነበት አስቸኳይ እገዳ እንዲደረግ የቀረበውን ጥያቄ ብቻ አልተቀበለውም። ወደ ዋናው ጉዳይ ገብቶ ያሉትን መረጃዎችና ምስክሮች መርምሮና አዳምጦ ብይን ለመስጠት ለማርች 10 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህም ሒደት ጠቅላል ጉባኤ ባስቸኳይ እንዲካሔድ ፍርድ ቤቱ እንደሚያዝ ይጠበቃል። ምክንያቱም በቦርድ አባላት ባጠቃላይ የተሰራውን ማንኛውንም ሥራ መርምሮና አዳምጦ ውሳኔ የሚሰጠው አካል ጠቅላላ ጉባኤ ብቻ ነው።
ጠቅላላ ጉባኤ የቤተክርስቲያኑ የማንኛውም ጉዳይ የመጨርሻ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው። አሁን የተፈጠረው የቤተክርስቲያናችን ችግር ደግሞ ቤተክርስቲያኑ ሕግ ጽፎና አጽድቆ በዛ ሕግና መመሪያ መሠረት ብቻ ቤተክርስቲያኑን እንዲመሩ በመረጣቸው ነፃ የቦርድ አገልጋዮች መካከል በመሆኑ በመካከላቸው የተፈጠረውን ችግር ይዘው ሕግ ወደሰጣቸውና ወደመረጣቸው አካል መምጣት ሲገባቸው በሕገወጥ መንገድ ያለ አባላቱ ፈቃድ በቤተክርስቲያኑ ስም ጠበቃ ይዘው በኅዝብ የተመረጡትንና የጸደቀላቸውን የቦርድ አባል ከቦርድ አባልነት ተሰናብተዋል በማለት ያለጠቅላላ ጉባኤ ፈቃድ ሕገወጥ ድርጊት ፈጽመዋል። ስለዚህም ይህንን ሕገወጥ አካሔ አይተው ቁጥራቸው ወደ 400 /አራት መቶ/ የሚሆኑ አባላት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ጥያቄ አቅርበዋል።

ከላይ እንደተገለጸውና በመተዳደሪያ ደንቡም እንደተቀመጠው የሁሉም ነገር ውሳኔ ሰጪ አባላት ናቸውና በቶሎ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራቱ አማራጭ የሌለው ነው። በሕግ ፊት ተቀባይነት ያለው የቤተክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ የእንግሊዝኛው ቅጂ አንቀጽ 4 Article IV a), b) and c) እንዲህ ይላል፦

እንግዲህ የአባላት መብት እዚህ ድረስ ሆኖ ሳለ በሕገወጥ መንገድ ከቦርድ አባልነት አሰናብተናል ማለት ከሕግ በላይ ነን እንደማለት ነው። እናም ሕጉን ጽፎ የሰጣቸው፣ መርጦ የሾማቸው ኅዝብ መሰብሰብና ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ይጠበቅበታል። ኅዝቡ ወስኖ ያላስቀመጠው ሰው በማንምና በምንም መንገድ የኅዝቡ ተወካይ/ሊቀመንበር/ቃል አቀባይ ሊሆን ከቶውንም አይችልም!!! ጠቅላላ ጉባዔው ሰፍሮና ለክቶ ከሰጣቸው መተዳደሪያ ደንብ ውጪም የአስተዳደር ቦርድ አባላት በራሳቸው ሕግ እንዲያወጡና እንዲሰሩ ፍቃድ አልተሰጣቸውም። የሚሰሩበት ሕግ እንኳን ቢያጡ ወደ ሕግ አውጪው ዘንድ ቀርበው ሕጉ እንዲሻሻል ይጠይቃሉ እንጂ እነርሱ በአድመኝነት በተስማሙበት አዲስ አሠራር ጠቅላላ ጉባዔው አይመራም ቤተክርስቲያኑም በሕገወጦች ሊመራ አይገባውም። ስለዚህ በአባላት ተቀባይነት ያላገኘ ሊቀመንበርም ሆነ ሌላ በአባላት ስም ምንም አይነት ነገር ማድረግ አይችልም።

በፍርድ ቤቱ የተሰጠውም ትዕዛዝ በቦርዱ አባላት የተወሰደው እርምጃ ትክክል ነው ወይንም አይደለም የሚል ሳይሆን ጊዚያዊ እገዳ ለመጣል በቀረበው ከስ መሠረት በቂ ሁኔታዎችና ማስረጃዎች ስለሌሉ ጉዳዩ በመደበኛ የፍርድ ሒደትና ክርክር መቀጠል ስለሚችልና የማይተካ ጉዳት የሚያደርስ ነገር ስለሌለ ቀጠሮ ሰጥቶ ነው ችሎቱን የገታው። ጉዳዩ በዝርዝር በሚታይበት ጊዜም በመጨርሻ የሚሰጠው ብይን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታው ወደዚያው የሚመራ እንደሆነ ይታመናል። እናም ወደድንም ጠላንም ጠቅላላ ጉባኤ መደረጉ አይቀሬ ነው። ጠቅላላ ጉባኤንስ ለምን መፍራት አስፈለገ? እውነትን የያዘ የሚያስፍራው ነገር የለም። የተፈጠረው ችግር ራሱ ቦርዱ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ የሚያስገድደው በመሆኑ ሊቀመንበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራታቸው ተገቢ ነበር። ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ ከኅዝቡ ፈቃድና ፍላጎት ውጪ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የኅዝብ ተመራጮች ግን ከኅዝብ ሸሸተው መኖር
ይችሉ ይመስል ሰላማዊ የሆነች ቤተክርስቲያናችንን እንድትበተበጥ አድርገዋል። በመሠረቱ የዲሴምበር 15ቱ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ በነጠላ ሲቆጠር ኮረም አልሞላም በሚል ሽፋን ውጤቱን ላለመቀበል ተራራ ቢፈነቀልም ኮረም ለመሙላት ቀረ የተባለው አርባና ሃምሳ ሰው ባጠቃላይ ኮረም አልሞላም ለሚሉት አካላት ቢደመር በእለቱ የተሰጠውን ውሳኔ ምንም አይለውጠውም ነበር። ውደፊትም ቢሆን ደበርሰላምን ወደ ወያኔ ለመቀላቀል የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ጉም እንደመዝገን መሆኑን ሁሉም የተረዳውና የማያዳግም ትምሕርት ያገኘበት ስለሆነ ይህ ሐሳብ ያላችሁ እርማችሁን ልታወጡ ይገባል እንላለን።

ቤተክርስቲያናችን የእግዚአብሔር መመስገኛ፣ የጽድቅ መውረሻ፣የአንድነት መገለጫና የታላቋ አገራችን ኢትዮጵያ መታሰቢያ እንጂ የሕገወጦችና የአድርባዮች ዋሻ አትሆንም።
መድኃኔዓለም ኅዝቡንና ቤቱን ይጠብቅ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop