የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሠላማዊ ሕዝብን በዲሽቃ ተኩስ ደበደበ!

March 11, 2022
Amharaበምዕራብ ሸዋ ዞን በዳሮ ወረዳ፤ ነዶ ወረዳና ጅባት ወረዳ የሚገኙ ዐማሮች የካቲት 11/2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ልዩ ኃይል በድሽቃ፣ በስናይፐርና በሞርታር ተደብድበዋል፡፡ በጥቃቱ አራት ሰዎች እንደሞቱ፣ ከቦታው ተፈናቅለው ደብረብርሃን የገቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
በሶስቱ ወረዳዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ሲሆን፣ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ሥልጣን በያዙ ማግስት ኦነግ/ሸኔ በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደጀመረ ደብረብርሃን የገቡት ተፈናቃዮች ይናገራሉ፡፡ ኦነግ/ሸኔ ወደ አካባቢው መጀመሪያ ሲገባ የታጠቃቸው መሳሪያዎች ብሬን፣ ስናይፐርና ክላሽ የነበሩ ሲሆን፣እስከ ሶስት መቶ ተዋጊዎችን የያዘ ኃይል ሆኖ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡
ይህ ኃይል በአካባቢው እንደደረሰ ዐማራን እየለየ እየገደለ፣ እያፈናቀለና ንብረት እያወደመ ቢቆይም ፣ መንግሥት ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በግል መሳሪያ እየገዛ ራሱን ከመከላከል አልፎ ኦነግ/ሸኔን ለማዳከም ችሎ ነበር፡፡ በዚህ የተቆጡትና በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ያሉት የኦነግ/ሸኔ ሰርጎ ገቦች፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ወደ አካባቢው በመላክ በህዝቡ ላይ ከባድ የቡድን መሣሪያ በሆነው ዲሽቃ ያልታጠቀውን ህዝብ አስመትተውታል፡፡ በዚህ ጥቃት ሰዎች ሞተዋል፣ በርካታ ጉዳትም ደርሷል፡፡
ከቦታው አምልጠው ወደ አዲስ አበባ ከገቡት 2 ሰዎች ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ዛሬ ምሽት በቪዲዮ ይለቀቃል፡፡ በዚህ የባልደራስ የፌስ ቡክ ፔጅ ላይ ይከታተሉት፡፡
//////
ምስል፣ ከኦሮሚያ ተፈናቅለው ዐማራ ክልል የተጠለሉ
#መረጃ #ሰበር –

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ 

1 Comment

  1. ካሁን በኋላ አገኘሁ ተሻገር ከዚህ በላይ ውርደት ሊኖር አይገባም ብሎ ነፍጥ አንግቦ የበደለውን ህዝብ ሊክስ ይችል ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አለ።ውርደት ክብሩም ከሆነ የሽመልስ ዘበኛ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

275303098 510126127175281 2578514359309836198 n
Previous Story

የትግራይ ወጣቶች በስደት ነው በሚል ወደ ራያ ቆቦ በገፍ እየገቡ ነው

Next Story

የትግራይ ኃይሎች በአፋር እና በአማራ ክልል በወረራ ገብተው.. ጭካኔ የተሞላበትና ስልታዊ የሆነ የአስገድዶ መድፈር በተናጠል እና በቡድን ፈጽመዋል፤

Go toTop