ወንድሜ እኮ ነው! አ ይ ከ ብ ደ ኝ ም :: ትርጉም ነቢዩ ተክሌ

ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ታሪክ በጃፖን አገር የሆነ እውነተኛ ክስተት ነው :: ልጁ በጃፓን በጦርነቱ ወቅት : የሞተውን ወንድሙን በጀርባው አዝሎ አብሮት ካለው ወታደር ጋር ረዥም የእግር ጉዞ ያደርግ ነበር::
ወታደሩ ክስተቱን አስተውሎ ልጁን በጉዞው እንዳይዝልበት በማሰብ በቃ “ወንድምህ ሟቷል : ቅብረውና ጉዟችንን እንቀጥል” ብሎ ይጠይቀዋል :: ልጁም መልሶ ወንድሜ እኮ ነው! ለእኔ አይከብደኝም ሲል መለሰለት:: ወታደሩም ልጁ ለወንድሙ ያለውን እውነተኛ ፍቅር ተመልክቶ እንባውን አፈሰሰ።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ምስል በጃፓን አገር የአንድነት ምልክት ሆኖ ይኖራል::
ምንም እንኳንታሪኩ በጃፓን አገር የሆነ ቢሆንም :የዚህ ፎቶ እውነተኛ ታሪክ ለእኛም የወንድማማችነትና የእህታማማችነት እውነተኛ ፍቅር ምልክት ነው!
“ወንድምህ ለአንተ አይከብድህም ምክንያቱም ወንድምህ ነውና… እህትህም ለአንተ አትከብድህም እህትህ ናትና:: ከዚህ እውነት ውጭ ተፈጥሮአዊ አይደለም ስለዚህ:-
ቢወድቅ አንሳው::
ቢደክም ደግፈው::
ቢቸግረው እርዳው::
ፍትህ ቢነፈግ ስለፍትህ ድምጽ ሁንለት::
እርሱን በመሸከም ድከም::
እርሱን ለመደገፍ ጥረት አድርግ::
ስህተት ቢያደርግ ይቅር በለው::
ቢስት መልሰው !
ሰዎች ጀርባቸውን ቢያዞሩበት አንተ ግን በጅርባህ ተሸከመው ::
ለአንተ አይከብድህም :ወንድምህ ነውና :: ይህን በማድረግ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማለህ!!
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕወሓቱ ሱር ኮንስትራክሽን ግየንባታ ማሽነሪዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች በባህርዳርና ጎንደር ታገቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share