በሲዳማ 146 ከፍተኛ አመራሮች ከሃላፊነት ተነሱ

የሲዳማ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም ያላቸውን 146 ከፍተኛ አመራሮች ከሃላፊነት አነሳ፡፡
ፓርቲው ለ238 አመራሮች ደግሞ ማስጠንቀቂያ ተጥቷል።
ፓርቲው ከሃላፊነት የማንሳትና የማስጠንቀቂያ ውሳኔውን ያሳለፈው “ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ሃሳብ የፓርቲው የአመራርና አባላት የሥልጠና እና የግምገማ መድረክ ትናንት ባጠናቀቀበት ወቅት ነው ።
የብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ የመድረኩን መጠናቀቅ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ከፓርቲው ስነ ምግባርና አስተሳሰብ ያፈነገጡ አካሄዶች፣ አስተሳሰቦችና ተግባሮች ፓርቲው ተሸክሞ እንደማይጓዝ ከጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ሃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
በመድረኩ በአገልግሎት አሰጣጥ ዳተኝነት፣ ግለኝነት፣ ጥቅመኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ስንፍናና ሌሎች መሰል ህዝብን ያማረሩ ችግሮች እንዳሉ በግልፅ ተገምግሟል ብለዋል ።
በተለይም በገቢዎች፤ በንግድና በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚስተዋሉ የሌብነት፣ የጉቦኝነትና መሰል ህዝብን ያማረሩ ብልሹ አሰራሮችን ፓርቲው እንደማይታገስም አቶ አብርሃም ገልጸዋል።
በዚህ መሰረት በተጠቀሱት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እጃቸው ያሉባቸው 384 የአመራር አካላት ተለይተው ፖለቲካዊ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ብለዋል።
ፖለቲካዊ ውሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል 146ቱ ከአመራርነት እንዲነሱ ሲደረግ፤ ለ238ቱ ደግሞ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ነው አቶ አብርሃም የጠቀሱት፡፡
በተጨማሪም ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንዲቻል የስነ-ምግባር ጉድለታቸውን የሚያጣራ ከዐቃቤ ህግ፣ ከፖሊስና ከሌሎች አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል ብለዋል።
በዘላቂነት ችግር ፈቺ የሆነ የስራ ዕድል ለዜጎች መፍጠር፤ የወጣቱን አቅም፤ ዕውቀትና ክህሎት መጠቀም የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በመድረኩም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚያካሄደው የፓርቲው የመጀመሪያው ጉባኤ ክልሉን የሚወክሉ አባላት ምርጫ መካሄዱንም ጨምረው ገልጸዋል።
ዘገባ ፡ – ሸዋንግዛው ወጋየሁ ለዶቼ ቬል / DW /
ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport፡ አትሌት መሰለች መልካሙ ወደ ሮተርዳም ማራቶን ተመለሰች

2 Comments

  1. እንዲህ አይነቱ ሹም ብር በተለያየ አካባቢ ተካሂዷል ኦሮሚያ የተባለውን ክልል እንዲህ ያለ ብወዛ መች ይካሄድበት ይሆን?

  2. ሸመልስ አብይን ይበውዝ እንደሆን እንጅ አብይ ሽመልስን ለመበወዝ አቅምም ስልጣንም የለውም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share