የተገንጣይነት የወያኔ ፕላን‼

ወቅቱ የዛሬ 26 አመት ገደማ ነው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሳይጀመር ማለት ነው

የወቅቱ የወያኔ ባለስልጣናት ኤርትራን ከኢትዮጵያ ገንጥለው መላው ኢትዮጵያን የመቆጣጠር የረጅም ጊዜ እስትራቴጂካዊ እቅድ ነደፉ። አንደኛውና ዋነኛው እቅዳቸው ትግራይ ውስጥ የሚኖሩ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ኤርትራውያን አብረው ከኢትዮጵያውያን ጋር ተጋብተው ተዋለዱ በደም ተሳስረው የሚኖሩ ኤርትራውያን ላይ ግፍና መከራ በማድረስ የተገንጣይነትና ኢትዮጵያን ጠልነትን እኔ ኤርትራዊ እንጂ ኢትዮጵያዊ አደለሁም እንዲሉ ከፍተኛ ስራዎችን ሰሩ።

ልብ በሉ እዚህ ጋር ወያኔ ኢትዮጵያን ሙሉ ለመጨበጥ የግድ ተቀናቃኙን የህዝባዊ አርነት ኤርትራን የሚመራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ብዙም የተገንጣይነት ዝንባሌ ስላሌለው ስልጣናችንን ሰለሚጋራን ትግራይ ላይ ያለውን በመቶ ሺ የሚቆጠር ኤርትራዊ ስቃዩን በማብዛት ለመገንጠል ለህዝበ ውሳኔ እንዲጠቅመን ኢትዮጵያ ጠል እናድርገው ነበር እቅዳቸው።

ቀጣዩ ፕላን ሁለት የትግራይ ህዝብን ከኤርትራ ወገኑ በመለየትና በመሰብሰብ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ልትገነጠል ትችላለች ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከተገነጠለች አብዛኛው በትግራይ ያለው ዘመናዊ ቢላቤቶችና ንብረቶች ኤርትራውያን መሸጥ መለወጥ ስለማይችሉ እነሱ ወደ አገራቸው ስለሚሄዱ ከተገነጠሉ የእናንተው ነው ብለው በጦርነት ከ17 አመት በላይ ስቃዩን ሲበላይ የነበረ የሚላስና የሚቀመስ ያጣ ህዝብን ወስደው በአንዴው የቤትና የንብረት የእልም ቅዠት ውስጥ ከተቱት።

ከዛ በኃላ ኢህሀዴግ ወያኔ መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ የሽግግር መንግስት ከመሰረተ በኃላ እነዚህ ምስኪን ኤርትራውያን የኤርትራን የመገንጠል ህዝበ ውሳኔ ሪፍረደም ከሰጡ በኃላ እንደ ከብት በመረብ በኩል ከአሁን በኃላ ኤርትራውያን እንጂ ኢትዮጵያውያን ስላሎናቹ መኖር አትችሉም ተብለው ልጅ፣ከእናቱ አባት ከልጁና ከሚስቱ ተነጣጥሎ አንድ ፌስታል ንብረት ሳይዝ በዛው በመረብ በኩል በኢትዮ ኤርትራ ድንበር በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ያፈሩትን ሀብት ጥለው ኑሯቸውን ከ0 ለመጀመር ኤርትራ ገቡ።
በዚህ ወቅት የተዋለደውና በደም የተሳሰረው የኢትዮ ትግራዋይና ኤርትራውያን ተቃቅፎ ደም እንባ ሲላቀስ የነበረ ሲሆን ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ እና የትግራይ ክልል በመግለጫ በመጎሻሸም ቀጥለዋል

በቅዠት አለም ውስጥ ወያኔ ሰብስቧቸው የኤርትራውያንን ንብረት ትወርሳላቹ ያሏቸው በደስታ ቋምጠው ለመውረስ አሰፍስፈው ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን እንዳሰቡት አልሆነም ወያኔ ሊበላ,,,በሉ ንኩት ብሎ ከፍተኛ የወያኔ ታጋይ ቤተሰቦች የነበሩ የወያኔ ዘመድ አዝማዶች እንዲወርሱና እንዲኖሩበት ቀጭን ትዕዛዝ በመስጠት ተፈፃሚ እንዲሆን አድርጓል።

ዛሬም ወያኔ እያደረገ ያለው ትግሬ ኢትዮጵያ ጠል እንዲሆንና ለህዝበ ውሳኔው ምቹ እንዲሆንለት ኤርትራ ላይ የሰራውን ታክቲክ በመድገም ኤርትራ ጠል የሚያዋስኑትን አማራና አፋር ጠል አድርጎ እድሜ ልኩን በጦርነትና፣በርሀብ፣በልመና የምትተዳደር ሰው ጠል አገር ትግራይን የመመሰረት እቅድ ነውና ፕላኑ።
የትግራይ ህዝብ ዝምታም ለዚህ ተግባሩ ምቹና መደላደል ሆኖለት እንደ ፈለገው እየጋለበ ይገኛል።

እውነታው ይህ ነው አዲዮስ።

ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው ገፅ

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share