ቻይናን አርሂቡ እንበላት – በስንታየሁ ግርማ

በኢትዮፕያ የሚኖሩ ቻይናዉንን በየሳምንቱ በተወሰኑ ቦታወች በነፃ ቡናችን እንዲጠጡ ማድርግ፤

በስንታየሁ ግርማ (sintayehugirma76@gmail.com)

“ቡና የሰለጠነው ዓለም ተመራጭ መጠጥ ነው!” ቶማስ ጀፈርሰን – የአሜሪካ መስራችና ሶስተኛው ፕሬዚደንት በአንድ ወቅት የተናገሩት

ቡና ኢትዮጵያ ለአለም ያስተዋወቀችው ምርጥ ስጦታ ነው፡፡ ቡና የኢትዮጵያ ብራንድ ነው፡፡ ከቡና የተሻለ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቅ ምርትና አገልግሎት ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ቡና ኢትዮጵያውያንን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የሚያስተሳስር ማህበራዊ ካፒታል ነው፡፡ ማህበራዊ ካፒታል ለሃገር ብልፅግና ዴሞክራሲ መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ የማህበራዊ ካፒታል መበልፀግ በበኩሉ ለሃገር ብልፅግና ተመልሶ ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡በዚህ ውድድር በበዛበት የሉአላዊነት ዘመን ሃገራት አንፃራዊ ብልጫቸውን በመለየት ምርትን (አገልግሎትን) ብራንድ በማድረግ ዜጎች ብራንዳቸውን ለማስተዋወቅ እንደ አንድ ሰራዊት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ከቡና የተሻለ ምርት ወይንም አገልግሎት የለም፡፡

ይሁንና በአለም በተዛባው የንግድ ስርዓት ምክንያት ኢትዮጵያ ከቡና መጠቀም የሚገባትን ያህል ተጠቅማለች ማለት አይቻልም፡፡ ለዚህ ደግሞ ከመፍትሄዎች መካከል በፍጥነት በማደግ ላይ ባሉት ሃገሮች በተለይም በወጣቶች ላይ አተኩሮ የኢትዮጵያን ቡና የማስተዋወቅ ስራ ጀምሮ አጠናክሮ እና በድግግሞሽ ማስቀጠል ነው፡፡መረጃዎች እንደሚያሳዩት ቡና ከነዳጅ ቀጥሎ ከፍተኛ ግብይት የሚካሄድበት ሸቀጥ ነው፡፡ በየቀኑ ከ3 ቢሊዮን ስኒ በላይ ቡና በአለም ይጠጣል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በአለም ተወዳዳሪ ቀርቶ አጠገቧ የሚደርስ ጥራት ያለው ቡና የሚያቀርብ ሃገር የለም፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ. በ2014 ታዋቂ የሆኑ የቡና ኤክስፖርተሮች ተጠይቀው ለኢትዮጵያ ቡና 25 ነጥቦች በመስጠት በአንደኛ ደረጃ ሲያስቀምጡት ኬንያ በግማሽ አንሳ በ12 ነጥቦች 2ኛ ደረጃ ኮሎምቢያ በ10 ነጥቦች 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

ዘ ኢኮኖሚስት እንደዘገበው ቻይና የሻይ ተጠቃሚ ሃገር ብትሆንም አሁን ቡና በመልመድ ላይ ናት ይላል፡፡ ይሁንና ዘ ኢኮኖሚስት ወጣት ቻይናውያን ቡና ከሚጠጡ በላይ በቡና መሸጫ ሱቆች ምስል ለመለዋወጥ አመቺ ሆኖ አግኝተውታል ይላል፡፡ ዘ ኢኮኖሚስት እንደሚለው የደቡብ ምእራብ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ በሆነችው ቹንዱ ሃንግ ሻይ የቡና መጠጥ አሰራርን ስትሞክር አግኝተናታል፡፡ ትምህርት የሚሰጠው ቡና ከሚቆላበት እስከ ቡና ጠጪዎች መስተንግዶ ክህሎትን የያዘ ነው፡፡ ከአውሮፓ ላኪ ማእከላት ስለ ክህሎቱ ማረጋገጫ አግኝታለች፡፡ በ20ዎቹና በ30ዎቹ የሚገኙ 7 ሴቶች የቡና መጠጥ መሸጫ ሱቅ ለመክፈት ሃሳብ ያላቸው ትምህርቱን እየተከታተሉ ነው፡፡ እስከ 1990ዎቹ (እ.ኤ.አ.) ድረስ ቡና በቻይና የሚጠቀሙት የውጪ ሃገር ዜጎች ብቻ ነበሩ፡፡ ያውም ማግኘት የሚቻለው በቅንጡ ሆቴሎች ብቻ ነበር፡፡ ሁኔታዎች መሻሻል ያሳዩት ለስታርባክስ በ1999 እ.ኤ.አ. በቻይና የቡና ሱቅ ሲከፍት ነው፡፡ ስታርባክስ ቡናን ለማለማመድ ወተት እና ስኳር ቀላቅሎ በመሸጥ ነበር የጀመረው፡፡ ይሁንና እንደ የአለም የቡና ድርጅት መረጃ መሰረት አሁንም ቢሆን በቻይና አማካይ የቡና ፍጆታ መጠን በአመት በአንድ ሰው 5 ስኒዎች ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአሜሪካ ወይንም በጃፓን ቡና ከሚጠቀመው ሰው አንድ ሶስተኛ ብቻ ነው፡፡ ይሁንና በመካከለኛ ገቢ ባላቸው ቻይናዎች ቡና መጠጣት ፋሽን እየሆነ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ እድር ላይ ጥያቄ አነሳህ ተብለው ታሰሩ

 በአሁኑ ሰዓት ስታርባክስ 3,800 የቡና መሸጫ መዳረሻዎች በቻይና አሉት፡፡ ይህ ደግሞ ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያደርጋታል፡፡ ስታቲስትዩ የተባለ የቢዝነስ ኢንተሊጀንስ ተቋምእንደሚለው ከሆነ የተቆላ ቡና ገበያ በቻይና በየአመቱ አስር በመቶ እያደገ ነው፡፡ በቻይና እስካሁን ከስታርባክስ ጋር የሚወዳደር ሃገር በቀል ኩባንያ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ላክን ኮፊ ቤጂንግን መሰረት አድርጎ ተመስርቷል፡፡ ከተቋቋመበት ከዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ እስካሁን 2,300 መዳረሻዎችን ከፍቷል፡፡ ሜይ 17, 2019 በወጣው የስቶኩ የጨረታ ገበያ 570 ሚሊዮን ብር ሰብስባ ዋጋውን ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር አሳድጓል፡፡ የላኪን አስገራሚ እድገት በቻይና የለውጥ ንፋስ እየነፈሰ መሆኑን ማሳያ ነው፡፡ ከእንግዲህ ቻይናውያን ቡናን እንደቅንጦት አያዩትም፡፡ ብዙዎቹ የላኪን ቡና መሸጫ ሱቆች ተጠቃሚዎች በአእምሮ ስራ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍል ናቸው፡፡ በጣም የስራ ጫና ያለባቸው በመሆኑ ትእዛዝ የሚሰጡት በኦንላይን ነው፡፡

የሻይ እና የቡና ገበያ በቻይና የተለያዩ ናቸው፡፡ የሻይ ቤቶች ከ40 ዓመት በላይ ቻይናውያን ይዘወተራሉ፡፡ በቡና መሸጫ ሱቆች ግን ከ40 ዓመት በላይ ያሉ ቻይናውያን እምብዛም አይገኙም፡፡ ወጣት ቻይናውያን የቡና መሸጫ ሱዎችን የሚጠቀሙባቸው ለማህበራዊ ትስስር ነው፡፡ ብዙዎቹ ቡና እየጠጡ ምስላቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ይለቃሉ፡፡

ከዘኢኮኖሚስት ዘገባ መረዳት እንደምንችለው በቻይና ገበያ ሰብሮ ለመግባት ብዙ እድሎች እንዳሉ የቡና ጠቀሜታን የሚያስረዱ ማስታወቂያዎችንና የፕሮሞሽን ስራዎች መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ጥናቶች እንደሚያስረዱት ቡና መጠጣት የእድሜ ጣሪያን በ15 ዓመታት እንደሚጨምር ተረጋግጧል፡፡ የእድሜ ጣሪያ ደግሞ የፍትሃዊ ሃብት ክፍፍል መግለጫዎች አንዱ ከሆነው የሰው ሃብት ልማት (human development index) አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ ቻይናውያን ቡናን በመጠጣት የሚያገኙትን ጥቅም (call to benefit) መሰረት ያደረገ መልእክት ቀርፀን ለቻይናውያን በማስተላለፍ ወደ ቻይና ገበያ ሰብረን መግባት ለነገ የማይባል ስራ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በመቀሌ የዳቦና የስንዴ እጥረት ተከስቷል

 አርሂቡ ቻይና!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share