እስከ መቼ ከትል ያነስን ቦንደኞች? – በላይነህ አባተ

 

ለገሰ ዜናዊ በወቅቱ በነበረው የአረቦች አመፅ ምክንያት በእስራኤሎችና በምዕራባውያን ትዕዛዝ
እንደዚሁም ሲወለድ በተነከረበት የአማራ ጥላቻ የአማራን ጥቅም ለመንጠቅ ዓባይን ተሱዳን ደጃፍ
ሊገድብ “ሕዳሴና ቦንድ” እያለ ቃዠ፡፡ የመለስ ቅዠት እንደ ዛር ተኮፍሷችሁ የሰይጣን ቁራጩ ለገሰ ቦንድ
እንዲሳካ ስንክሳር እሚያካክል ጥሑፍ የጣፋችሁ ሆዳምና ዘልዛላ “ምሁራን”፣ የቦንድ ስብሰባዎችን
ለማዘጋጀት መቀመጫችሁን ያማታችሁ አዘጥዛጮች፣ ቦንድ ለመግዛት ሆዳችሁን እንደ ቅንቡርስ
እየገፋችሁ ያረጠረጣችሁ ህሊና ቢሶች፣ ልማት፣ ህዳሴና ተሃድሶ እያላቸው ያክላላችሁ ዘፋኞችና ሌሎችም
ቦንደኞች! የቦንድ ገንዘባችሁ ወገኖቻችሁን እንደ ደን ከማስጨፍጨፍ በተጨማሪ ለገዳዮቹ ማሳከሚያ፣
ሰርግ መደገሻ፣ መዝናኛና ለሌሎችም ቅንጦቶች መዋሉን ከእነዚህ በህሊናቸው ከተገዙ ወይዛዝርት
ውይይት ተረዱ፡፡ (የወይዛዝርቱን ውይይት ይህንን ተጭነው ወይም ቆርጠውና አጣብቀው
ይመልከቱ) https://ethsat.com/2017/08/esat-menalesh-meti-formeremployee-

metec-exposing-corruption-august-2017/ ወይዛዝርቱ እውነት አልተናገሩም
እያላችሁና ከተሞክሮዋ ትምህርት ከቀሰመችው የአባ የሻነው ትል እያነሳችሁ እንደ ልማዳችሁ
አትንዘላዘሉ፡፡

አባ የሻነው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትል ታሪክ ደጋግመው ይተርኩልን ነበር፡፡ አባ የሻነው “ተትሏ
እንማር!” ይላሉ ራሳቸውንም እንደተማሪ በመቁጠር፡፡ “ትሏ ዛፍ ለመውጣት ስትሞክር ወደቀች፤ አንድ
በሉ፡፡ እንደገና ሞክረች ግን ነጠረች፤ ሁለት በሉ፡፡ አሁንም እንደገና ስትንጠለጠል ዘጭ አለች፤ ሶስት በሉ፡፡
ዘጭ ታለችበት ተነስታ እንደገና ተንጠለጠለች፤ ግን ተመልሳ እርፉቅ አለች፤ አራት በሉ፡፡ እርፉቅ ታለችበት
ተነስታ አሁም ግንዱን በትንሹ ወጣች፤ ግን እንደገና ተንደባለለች፤ አምስት በሉ፡፡ ተተንደባለለችበት ተነስታ
ተበፊቱ የበለጠ ርቀት ዛፉን ወጣች፤ ግን ተመልሳ ነጠረች፤ ስድስት በሉ፡፡ ተነጠረችበት ተነስታ ለሰባተኛ
ጊዜ ስትሞክር ሰማይ የደረሰውን ዛፍ ምንም እንከን ሳይገጥማት ወጣችው” እያሉ ይተርካሉ ጨረቃ
የመሰለ ፈገግታ እያሳዩና ሻሽ የመሰለ ጺማቸውን እያፍተለተሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሚናወቻቸውን የተለዋወጡት አቡነ ኤርምያስና አቶ ታየ ደንድአ

ከትረካው በኋላም አባታችንና መምህራችን አባ የሻነው “በሰባተኛው ዙር ትሏ ለምን የተሳካላት
ይመስላችኋል?” ብለው ሲጠይቁ “በሰባት ስላሴ ስለሚውል፣ ተስፋ ስላልቆረጠች …ወዘተርፈ” እያልን
እንመልሳለን፡፡ እርሳቸውም “እርግጥ ነው ተስፋ ያልቆረጠን ስላሴም ይረዳል!” ብለው የምንሰጠውን
መልስ ሳያጣጥሉ “ትሏ የተሰካላት ተልምዷ ትምህርት በመውሰድዋና ያደናቀፏትን መንገዶች ትታ
ሌላውን በመከተልዋ ነው” ብለው ተልምድ የመማርንና የተለያዬ መንገድ የመከተልን ጠቀሜታ
ያስተምራሉ፡፡

የአባ የሻነው ትል ያህል ተልምድ መማር ተስኗቸው ስለ ቦንድ እጃቸው ውሀ እስቲቋጥር የጣፉት፣
ላንቃቸው እስቲደርቅ የሰበኩት፣ ልሳናቸው ጥርቅም እስቲል የዘፈኑትና መቀመጫቸውን እስቲያልባቸው
ያረጠረጡት ህሊናቸውን የሸጡ አለዚያም የተንዘላዘሉ የለገሰ ቦንድ ካድሬዎች ናቸው፡፡ አለዚያማ ሰይጣንና
ለገሰን እንኳንስ ቆመው ሞተውስ ከዘልዛላ በቀር ማን ያምናቸዋል?
የሚያዝ የሚጨበጥ ጭራ የሌለው ለገሰ፤ የሰፈሩን ባንክ በመዝረፍ ባደባባይ ውንብድናውን የጀመረው
ለገሰ፤ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የመንደሩን ጎረምሶችና ኮረዳዎች እንደ ሳር አሳጭዶ አገራችንን የባህር
1/29/22, 10:30 AM እስከ መቼ ከትል ያነስን ቦንደኞች (በላይነህ አባተ) | አባይ ሚዲያ
amharic.abbaymedia.info/archives/34063 2/3

መተንፈሻ የነሳት ለገሰ፣ በርሃብ የረገፈውን ሕዝብ ስንዴ እየሰረቀ ኬሻውን ባሸዋ የሞላው ለገሰ፤ ለፖለቲካ
ፍጆታ የቀዬውን ሕዝብ በቦንብ ያስጨረገደው ለገሰ፣ አማራን ለማዳከምና ለማጥፋት ድንጋዩን ብቻ
ሳይሆን ጠጠሩን፣ አሸዋውንና አፈሩን የፈነቀለው ለገሰ፣ በአያቶቻችን ደምና አጥንት የከበረውን መሬታችንን
ለሥጋና ለነፍስ አባቱ ሱዳን የሰጠው ለገሰ፣ ሕዝብን በቋንቋ ጎራዴ ያቃላው ለገሰ፤ ስንቱን ባልታወቀ ወህኒ
ያሰቃየው ለገሰ፣ ስንቱን እያሰደደ ባባህር ያስበላውና በጭራቆች ያሳረደው ለገሰ “ቦንድ” ብሎ ሲጮህ
ቦንደኞቹም ተከትለው እንደ ገደል ማሚቶ “ቦኦ…ንድ…ቦኦ..ንድ” እያሉ አስተጋቡ፡፡ ሳጥናኤል
የእግዚአብሔርን ቃል እየተናገረ እንደሚያታልለውም ለገሰ “ራዕይ፣ ታድሶ… ህዳሴ” እያለ ጫቱን እየቃመ
ሲጀነጅን ቦንደኞቹም ተከትለው “አዎ ልማት፣ ተሃድሶ፤ ህዳሴ! ያገር ጉዳይ! የሕዝብ ጉዳይ!” እያሉ
ተሽኮረመሙ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአማራነት ተደራጅቶ መታገል - አንዱ ዓለም ተፈራ፤  

መሽኮርመሙ ከሞቀ ውሀ እንደ ገባ ጨው ፍርክስክስ አርጓቸው ነፈሰ-ገዳዩንና ከሀዲውን ለገሰን
እንቃወማለን እሚሉት ሁሉ የቦንድ ካድሬ ሆነው ቁጭ አሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ሕዝብ እንደ ጫካ ሲጨፈጨፍ
ድምፃቸው ተሰምቶ እማይታወቅ ተሽኮርማሚ ዲዳዎች በጥሑፍና በራዲዮ ቦንድ፤ ታሐድሶ፤ ህዳሴ
በሚሉት ቃላት አፋቸውን ፈቱ፡፡ ስንቶቹ ከንቱ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ከስማቸው ዳር ፒኤች ዲ፣ ኤም ዲ
ወዘተርፈ እሚሉ ማእረጎች እያስቀመጡ ድጓ እሚያካክል ዝባዝንኪ እየጣፉ አንባቢን አባተሉ፡፡ ስንቶች
አቀንቃኞች “ህዳሴ፣ ራዕይ፣ ተሃድሶ፣ ልማት” እያሉ መስክ ግጦ እንደ ጠገበ አለሌ አክላሉ፡፡ ስንቶቹ ዘፋኞች
ሙሴ የተሻገረውን ባህር የሸጠውን ለገሰን “ባህር አሻጋሪው ሙሴ!” እያሉ በሌለ ባህር አፋቸውን እንደ
ሰማይ ከፍተው ተሕዝብ፣ ተእግዚአብሔር፣ ተህሊና፣ ተእውነትና ተታሪክም እስከ መጨረሳው ተቀያየሙ፡፡
ስንቶች ከርሳሞች የለገሰን ቦንድ ለመግዛት እንደ ቡችላ ጅራታቸውን ወትፈው ተንጦሎጠሉ፡፡
ይህ ብዕራቸውን እንደ ሰሃራ ያደረቁለት፣ አፋቸውን እንደሰማይ የከፈቱለት፣ እንደ አሳላፊ ወገባቸውን
የሰበሩለት፣ እንደ ቡችላም የተንጦለጦሉለት የቦንድ ገንዘብ ለነፍሰ-ገዳዮች ቅንጦት ሲውል ለምን ብሎ
የሚጠይቅ የመለስ ቦንድ “ምሁር”፣ ካድሬ ወይም ቦንድ ከፋይ ቡችላ የት አለ? ሕግና ሥርዓት በሌለበት
አገር ልማትም ሆነ ቦንድ የማይሰራ መሆኑን ተረድቶ ጸጸቱን በአደባባይ የገለጠ ቦንድ ሰባኪ “ምሁር” የት
ይገኛል?

ይኸንን እያየን ለገሰ በቅዠቱ እሚመራው የነፍሰ-ገዳዮችና የዘራፊዎች ቡድን ላገር ያስባል፣ ለግድያና ለዘረፋ
የዘረፈውን ሥልጣን በምርጫ፣ በእርቅና በሽምግልና ይመልሳል እያልን እንደ አህያ ጅራት ተመንዘላዘል
የተቆጠብን ስንቶቻችን ነን? የአባ የሻነው ትል ተስድስት ልምዶች ስድስት ትምህርቶች ስትቀስም እኛ
በወልቃይት አማሮች የተጀመረው መታረድ በደኖን፣ አርባ ጉጉን፣ ጉራፈርዳንና መተከልን ጎብኝቶ ጎንደርና
ባህርዳርን ካዳረሰበት አርባ ዓመታት ልምዶች ስንት ትምህርት ቀሰምን? የአባ የሻነው ትል በሰባት
ሙከራዎች ሰባት መንገዶችን ስትሞክር እኛ በአርባ ዓመታት ውስጥ ስንት መንገዶችን ፈትሸናል?
“የህዳሴ ግድብ፣ የከተማና ገጠር ልማት፣ የብሔሮችና የሲኖዶስ እርቅ፣ አገራዊ ወይም ኤፍሬም ይሳቃዊ
ሽምግልና” በሚሉ የለገሰ የጫት ጅንጀናዎች እየተሽኮረመምን ስንት ተጨማሪ ዓርባ አመታት ተመሳሳይ
መንገድ ልንከተል አስበናል? እስከ መቼስ ከትል ያነስን ቦንደኞች ልንሆን ተረግመናል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ልብ የሚነካ ግጥም፡ 'የህጻኑ ጥሪ' መታሰቢያነቱ ለ እስክንድርና በግፍ ለታሰሩ ወላጆች (በድምጽ)

ዓባይን ማን መቼ ይገድበው? http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/06/Abay.pdf
1/29/22, 10:30 AM እስከ መቼ ከትል ያነስን ቦንደኞች (በላይነህ አባተ) | አባይ ሚዲያ

amharic.abbaymedia.info/archives/34063 3/3
?ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ (ምን አለሽ መቲ) እና ወ/ሮ ቤተልሄም ግርማ የቀድሞ የሜቴክ ሰራተኛ ድርጅቱ ውስጥ ስለሚካሄደው

ሙስና አጋለጡ።https://ethsat.com/2017/08/esat-menalesh-meti-former-employee-

metecexposing-corruption-august-2017/
ሐምሌ ሁለት ሺህ ዘጠኝ ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share