የሚኒስትሮች ምክር ቤት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ውሳኔ

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ቀሪ የሚሆንበትን ጊዜ በሚመለከት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
ሕውሃት እና ግብረአበሮቹ በሃገራችን ህልውና እና ሉአላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀኑ በመሆኑ እና ይህን አደጋ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስራ መከላከል የማይቻል ሆኖ በመገኘቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014ን ያወጀ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 ፀድቆ በስራ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑ እና ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 አንቀጽ 11(2) በተደነገገው መሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች ከተቀየሩ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስርዓት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር ይቻላል ብሎ ካመነ የስድስት ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው በመሆኑ የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በጥልቀት ተወያይቶ በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
//
#PMOEthiopia
ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝብ የአስተዳደር ውሳኔን የመቀበል ግዴታ የሚኖርበት እንደ ዜጋ ሂደቱ ላይ የመሳተፍ እና የማወቅ መብቱ በአግባቡ ሲከበርለት ብቻ ነው!

2 Comments

  1. Is this the cabinet ( executive branch ) of the country ( the people) or r a cabinet that deceivingly changed itself from being the cabinet of TPLF/ EPRDF to the cabinet of OPDO/ OLF/ Prosperity and made things much more deeply horrible ? Needless to say that the latter is the right answer unless we want to deceive ourselves.

    It is self -evidently true that this body of dirty politics has passed its decision and has sent it to another body of dirty politics called parliament or house of people’s representatives or another bunch of politically stupid and morally bankrupt cadres.

    And it goes without saying that the third branch of government ( the judiciary) does play a very , very and very horribly disastrous political orchestration .

    I strongly argue that unless this tragically constitutionalized and structured political system that has caused and keep causing an extreme danger not only to the prevalence of human and democratic rights but also to the very lives of the people is forced either to come to the terms of the real sense of democratic change or else to face its own demise by any means appropriate , it will destroy the very social, historical , cultural and moral fabrics of the people to the extent of making things impossible to put together back !

  2. “የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ቀሪ የሚሆንበትን ጊዜ …የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው” “ቀሪ” የሚያበቃበትን ቀን ለማለት ነው?
    አዬ የዘንድሮ ጋዜጠኛነት!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share