ብልጽግና ታሟል …ጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም ከአዋጊ ወደ አምባሳደርነት

ከ2ሳምንት በፊት ሙሉ የጄኔራልነት ማዕረግ የተሰጣቸውን ጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም ከአዋጊ ወደ አምባሳደርነት እንዴው በምን መስፈርትና ሳይንስ ነው 360 ድግሪ የተከረበተው??
አንዲት ሀገር እኮ አንድ የጦር ጀነራል ለማፍራት እና ጀኔራል ለማድረስ እስከ 40 አመት ኢንቨስት ማድረግ አለባት ብለው በአንደበታቸው ከነገሩን 2 ሳምንት እንኳን አልሞላውም….።
አምባሳደር ለመሆን ደግሞ ዓለማቀፋዊ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ እውቀትና ክህሎትን ይጠይቃል…።
እንዴት ትናንት የሙሉ ጀነራልነት ማዕረግ ሹሞ በሥራ ላይ ያሉ የጦር ጀነራሎችን ዛሬ ከካበተ ሙያና ሥራቸው ገሸሽ ተደርጎ ምንም እውቀትም ሆነ ልምድ ወደሌላቸው አምባሳደርነት ይሾማሉ
ያሳዝናል ወያኔ/ኢህአዴግ የሚባል መርገምት ሥልጣን ላይ ከተቆናጠጠ ጀምሮ ኢትዮጵያ ታሪኳን እና ክብሯን የሚመጥን እንዲሁም ተለዋዋጭ እና ውስብስብ የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴና ነባራዊ ሁኔታዎችን ነቅቶ የሚከታተል፥ ለኢትዮጵያ ህዝቧ ሁሌም በተጠንቀቅ የሚቆምና የሚሟገት የሠለጠነ ባለሙያ ለአምባሳደርነት በቅቶ አያውቅም፤ አምባሳደርነት ከነ አክሊሉ ሃብተወልድ ጋር ወደ መቃብር ከወረደ ሰንበትበት ብሏል…።
የንጹሀን ግድያ፣መፈናቀልና እልቂትም ሊነጋ ሲል ይጨልማል ሆኖ ነው ለብልጽግና ጊዜ ይሰጠው፤ ልዩልዩ የአገልግሎት ቦታዎች በሚመጥነው ባለሙያ እየተተኩ( The Right Person on the right Position) ስራናሰራተኛ እየተገናኘ፣ተቋማዊ ሪፎርም እየተደረገ ሀገራችንም ህዝባችንም የለውጥ አመራር ተቋዳሽ ይሆናል ብለን ተስፋ ስናደርግ፤ ጭራሽ ከወያኔው ዘመን ብሶ አረፈው?!ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም ከማለት ውጭ ምን እንላለን….!!!
መጥኔ ለሃገሬ….
ይሁን መቸም የፈለገው ቢሆን ወያኔ በስንት ጣሟ አልልም…።

አፈትላኪ ዜናዎች


ጀነራል ባጫ ደበሌን እና ዶ/ር ስለሺ በቀለን ጨምሮ 27 ግለሰቦች በአምባሳደርነት ተሹመዋል። በዚህም መሠረት፡-

1/ አቶ ተፈራ ደርበው
2/ አቶ ደሴ ዳልኬ
3/ ዶክተር ስለሺ በቀለ
4/ ጄኔራል ባጫ ደበሌ
5/ ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም
6/ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ
7/ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ
8/ አቶ ረሻድ መሀመድ
9/ አምባሳደር ጀማል በከር
10/ አቶ ፈይሰል ኦሊይ
11/ አቶ ኢሳያስ ጎታ
12/ አቶ ፀጋአብ ክበበው
13/ አቶ ጣፋ ቱሉ
14/ ደክተር ገነት ተሾመ
15/ አቶ ዳባ ደበሌ
16/ አቶ ፍቃዱ በየነ
የባሉሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት
እንዲሁም:
1/ አቶ አሳየ አለማየሁ
2/ አቶ ኃይላይ ብርሃነ
3/ አቶ አወል ወግሪስ
4/ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት
5/ አቶ አንተነህ ታሪኩ
6/ አቶ አክሊሉ ከበደ
7/ አቶ ሰይድ መሐመድ
8/ አቶ ዮሴፍ ካሳዬ
9/ አቶ ዘላለም ብርሃን
1ዐ/ ወ/ሮ ፍርቱና ዲባኮ
11/ አቶ ወርቃለማሁ ደሰታ
በአምባሳደርነት የተሾሙ መሆኑን ከፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ሆዳም አማሮቹ ም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን እና ሕላዊ ዮሴፍ ሲዋረዱ ተመልከቱ (Video)

3 Comments

  1. ወይ ጊዜ የተደናበረ ዉ ጠቅላይ ሚኒስትር የባሰ ድንብርብሩ ወጥቷል። ይህ ነገር በድንገት የሆነ ነገር አይደለም። ኢትዮጵያን መቀመቅ አዉርዶ ኦሮምያ የምትባል አገር ለመትከል ይመስላል። ግፈኞች እና አመፀኞች የስራቸዉን ማግኘታቸው አይቀርም።

  2. የሁለቱ ጄኔራሎች ከመለዪ ለባሽነት ወደ አምባሳደርነት ሙያ መሾም ግር ቢያሰኝም እንግዳ ነገር ግን አይደለም። እንግዳ ነገር የሚያደርገው የተሾሙበት ሃገር ከታወቀ በህዋላ ነው። ምን አልባት ሃገሪቱ የምትሸምታቸው ወይም የምትበደራቸው የጦር መሳሪያዎች ካሉ እነዚህ ጄኔራሎች በሙያቸው ሊያግዙ ይችላሉ። በሌላ መልኩ ደግሞ ወታደራዊ አታሼ በመመደብም ሙያው ሊሰራ ይችል ነበር። ግራም ነፈሰ ቀኝ ወሃ ቅዳ ውሃ መልስ የብልጽግና ዋና መለያው ሆኗል። በእኔ እምነት ሁለቱም ጄኔራሎች አሁን በወያኔና በሱዳን/ግብጽ በሌሎችም ተጋላቢ ሃይሎች እየተቃጣባት ላለው ግጭት ማለፊያ አመራር ይሰጣሉ ብዬ እገምታለሁ። አምባሳደርነቱ በቅርቡ ከተጫነላቸው ኮኮብ ጋር አብሮ ይሄድ ይሆን? የሚሆነውን ጠብቀን ከማየት ሌላ ምንም አማራጭ የለንም። ነገስ ምን እንሰማ ይሆን?

  3. The very illness of this ruling circle so called Prosperity has been very known for three decades . In other words, it was and is chronically ill and it will continue to be so ill as long as we keep playing the politics of good for nothing . Its chronic illness has caused and will keep causing a huge and tragic consequences to the the very existence of the country or the people .

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share