ሞሳድ የበላው ነጭ ድመት – ሱሌማን አብደላ

2021 ሊገባ ትንሽ ቀናቶች ቀርተውታል። በታሪካቸው በግብፅ መንግስት ትልቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ፕሬዚዳንት ሰልቫኬር ይሄ አቀባበል ምን መልዕክት እንዳለው አላወቁም። ከጁባ የበረረው የፕሬዝዳንቱ የግል አውሮፕላን በካይሮ ቤተመንግሥት ሲደርስ የአበባ ጉንጉን ይዞ የተቀበለው ሲሲ፣ እንኳን ደህና መጣህ አቡኒል (የናይል አባት ) አለው። በጌጥና በመአዛ ያበደው የሲሲ ቤተመንግሥት በሰልቫኬር ፎቶና የእንኳን ደህና መጣህ መልዕክት አሸብርቀዋል።

የሲሲ ፊት ፈገግ ይላል። ሰውየው ትንሽ ግራ የሚያጋባ መስተጋብር አለው። ድመትም ይሁን ሌላ አራዊት ወደቤተ መንግስቱ ከመጣ መሳቅ ይወዳል። ምናልባት ባህሪው ነው ወይስ ትህትናው

በባዶ የሚያስቀው.? የጆቢራ ገደሉ እብድ ይወቀው።
አዲስ አበባ በችግር ቀለበት ለመጠመድ የሴራ ቀለበቷ እየተሰራላት ነው። አሞራው ሞሳድ ግን የካይሮን ቤተመንግሥት የሆነ ነገር አይቶበት መዞር ይዟል። ከጁባ የተነሳው የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን ጋር አሞራ የለም ማለት አይቻልም። ነገሮች በደንብ ተጠንቶባቸዋል። ሲአይኤ ግን ምንም እንዳልሰማ መስሎ ምናልባት እየተከታለው ይሆናል። ከኬኒያ ዝሆኖች ጀርባ ግን አንድ ሀይል አለ።

እቅዱ ትንሽ ከበድ ያለ ነው። ቢሊዮን የግብፅ ዶላሮች እንዴት ነው ከጁባ ወደ ትግራይ ክልል መግባት የሚችሉት የሚለው ዋናው ነጥብ ነው። ሁለተኛው ነጥብ አዲስ አበባ የሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢምባሲን በቦንብ ማውደም ነው። ይህ እቅድ ሲሰላ ህወሓት ብሎም የግብፅ እና የኬኒያ ቆሪኪ ተጫዋቾች አሉበት። መጀመሪያ ገንዘቡ የወጣው ከግብፅ ወደ ጁባ ነው። የጁባ መንግስት ይሄንን ቢሊዮን ዶላር እንዴት ተቀብሎ ማስተላለፍ እንዳለበት ምክር ሊሰጠው ነበር ወደካይሮ የተጋበዘው። ዶላሩ በግብፅ የኢንቨስትመንት ባለሀብቶች ስም ቀድሞ ወደ ጁባ ገብቷል። ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጁባ ከተማ ጓዳ የገባው ያለ ደቡብ ሱዳን መንግስት እውቅና ነው።
አሞራው ሞሳድ ግን ይቺን መረጃ ከጭልፊት ተቀብሎ ወደ እስራኤሉ ጠሚ ቤኒያሚን ኔታኒያሁ አሳውቋል። ነገሮች ”
ከሀ እሰከ” ፐ መስመር እስኪዙ አሞራው ሞሳድ ሲከታተል ነበር።
.
ቢሊዮን ዶላሮቹ እንዴት መግባት አለባቸው የሚል ሀሳብ ሲብሰለሰል የኢትዮጵያ ቀጫጭን ደህንነቶች ይሄንን ወሬ የሚሰማ ሰፋ ያለ ጆሮ የላቸውም ነበር። (ይቅርታ ግን የአገርን ልጅ ማሳነስ አይሁንብኛ)
.
የግብፅ መንግስት ከሰልቫኬር ጋር በጉዳዩ ላይ መከረ ነገሮች ተቃያየሩ ። ሰልቫኬር ይሄንን ነገር ሰሙ። ተደናገጡ ምናልባት በዚህ በሚያስፈራ የጥቁር ቀይ አይናቸው ተገላምጠውም ሊሆን ይችላል ብቻ
በሄዱበት አውሮፕላን ድንገት ተነስተው ወደ ጁባ ተመለሱ። እዚህ ላይ ነገሮች ተቀያየሩ። አሁን የጁባ ጭልፊትና የቴላቪቭ አሞራዎች መነጋገር ጀምሩ። ሰልቫኬር በግብፅ መንግስት የደህንነት ሀላፊ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ አልተቀበሉትም። እንደውም ጥቁሩ ሰልቫኬር ተናዶ በደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ የግብፅ ባለሀብቶች ጠቅለው እንዲወጡ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጣቸው።
.
ባለሀብቶቹ ወጡ። የገባው ዶላር ከደቡብ ሱዳን ወደ ሰሜን ሱዳን ተመለሰ። ከሰሜን ሱዳን ወደ ትግራይ በነቡረሀን በኩል ሊገባ ትዕዛዝ ተሰጠተው። ጣሳው ቡረሀን እሽ አለ። መቸም ቡረሀን ታዞ እቢ እሚለው ነገር ቢኖር ስልጣኑን ብቻ ነው። እዚህ ላይ ሲደረሱ ቀጫጭኖቹ የኢትዮጵያ ሰላይዎች ነገሩን ደረሱበት። ግራ ተጋቡ። በካርቱም ጎዳናዎች ላይ ሰማያዊ ጅስ የሚለብሱ ጥቁር መነፀር የሚያደርጉ የቡና ሱሰኞች ወይም የኢትዮጵያ ሰላይዎች ተበራከቱ። በነገራችን ላይ የውጭ አገር ሰላይዎች የኛን ደህንነቶች ሲጠሯቸው የቡና ሱሰኞች ብለው ነው። እኔም ለዛ ነው ቃሉን የተጠቅምኩት።
በወቅቱ የኢትዮጵያ የደህንነት ሚኒስቴር አቶ ተመስገን ጥሩ ነህ ነበሩ። ነገሩን ሲሰሙት ለአባመላ ወዲያ አሳወቁ። አሞራው ሞሶድ ከጁባ ጭልፊቶች ጋር የነበረውን ፍቅር አቋርጦ በቀጫጭኖቹ የኢትዮጵያ ሰላይዎች አናት ላይ ከፍ ብሎ መብረር ጀመረ። አብረው የሚሰሩት የኤርትራ አሳዎችም ሰሙ። ምስራቅ አፍሪካን ያነጋገረ ነገር ሆነ።
ጥርሱ መጠጥ ያለው የኤርትራው አፈወርቂ ይሄንን ነገር ሰማ። ጎበዝ ነቃ በል የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ። ኢሳያስ ክፉ ነው። ክፋትን በደንብ ያውቃታል። ከ10 የአለማችን ክፉ ሰዎች መካከል ዘንድሮም በዝርዝሩ ውስጥ አለ። አትገረም ክፋት ስልህ መጥፎነት አይደለም። ኦኔውን ነው የምልህ
.
አሁን የሲሲም EGE ሰላይዎች የኢትዮጵያም የቡና ሱሰኞች የኤርትራም አሳዎች” የቴላቪቭ አሞራዎች በካርቱም የባህር ዳርቻ በሚነፍሰው ቀዝቃዛ አየር ስር ተደብቀው አብረው ቡና እየጠጡ ነው። ቢሊዮን ዶላሩ ከሱዳን ሊነሳ ሞተር እየቀረ ነው። የኬኒያ ዝሆኖች ብሩን ተቀብለው ለማስተላለፍ፣ ቀጠሮ ይዘዋል። ብሩ ከካርቱም ነስቶ በኤርትራ ባህር ላይ በግብፅ መርከብ ሊሻገር መርኳ ዘይት እየቀረች ነው። እዚህ ላይ ቀጫጭኖቹ የኢትዮጵያ ሰላይዎች” መረጃው ሊቋረጥባቸው። ቢሊዮን ዶላሩ” ከየት ወደየት ሊሄድ ይሆን እያሉ እንደ ጆቢራ ገደሉ እብድ ብቻቸውን እያወሩ ነው።
.
ዶላሩ ከካርቱም ተነሳ። ከዶላሩ ጋር አብሮ መብረር የሚችለው አሞራው ሞሳድ ብቻ ነው። የግብፁ EGE አብሮ መዞር ከጀመረ ወራቶች ሆነውታል። አሞራው ሞሳድ ነገሩን ለእስራኤል መንግስት ካሳወቀ ቆይቷል። የእስራኤል መንግስት ለጓዱ የዛይድ ልጅ አዲስ አበባ የሚገኘው ኢምባሲው በአሸባሪዎች ፈንጅ ቀለበት ሊገባ መሆኑን
ሹክ ይለዋል።
ቀጥሎም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ደወሉ። ግን ማን እንደደወለ አልታወቀም። ብቻ የእስራኤል ቁልፍ የመረጃ ሰው ለኢትዮጵያ የአንድ የመንግስት ቁልፍ ሰው ደውሏል። ቢሊዮን የግብፅ ዶላር በቀይባህር ዳርቻ ላይ ቆመው አሻጋሪውን መርከብ እየጠበቁ መሆኑን አሳወቀ። እንዲህ ነውዴ ነገሩ አለ ሃበሻ ይሄንን ሲሰማ። አሞራው ሞሳድ ሁሉንም አዳረሰ። የኤርትራ አሳዎች መረጃ ደርሷቸዋል።
መርኮቧና የኬኒያ ዝሆኖች የግብፁ EGE የት አቅጣጫ እንዳሉ እንዲጠቁም ለአሞራው ሞሳድ ትዕዛዝ ተሰጠው። ድሮም መብረር የሚወደው አሞራው ሞሳድ በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ዝቅ ብሎ መብረር ጀምረ። በኤርትራ የባህር ክልል ውስጥ እንደ ነጭ ድመት ኩርትም ብለው በአንዲት ትንሽየ መርከብ ውስጥ የሚሄዱ ሰዎችን አየ። ምክክር ተጀመረ። የሬዲዮ እና የስልክ ጥሪዎች ተበራከቱ።
አሁን ሦስቱም እየመከሩ ነው። የኤርትራ አሳዎች የዱባይ የባህር ሰላይዎች የኢትዮጵያ የቡና ሱሰኞች የእስራኤሉ ነጭ አሞራ ( ሞሳድ) ሆነው ከወሰኑ ቡኋላ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደቀስት የሚወረወሩ የባህር ሀይሎቹን ትዕዛዝ ሰጠ። አሞራው ከላይ አሳው ከታች ሆነው የግብፅ ቢሊዮን ዶላር ወደ አስመራ አቀና።
..
ሞሳድ የበላው ነጭ ድመት የሚለው አስገራሚ መረጃ ታሪክ በዚህ ተጠናቀቀ
.
ሱሌማን አብደላ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዛሬዋ ኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ሳይንሳዊ ዕውቀት ጋር አለመተዋወቅ፣ የንቃተ-ህሊና አለመኖር፣ ጥያቄ ለመጠየቅ ያለመቻል ችግር ነው! ለአቶ ኤፍሬም ማዴቦ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ዋናው ችግር ምንድነው? ብሎ ለጠየቀውና “መልስም ለመስጠት ለመኮረው” የተሰጠ ትችታዊና ሳይንሳዊ ሀተታ መልስ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share