በአፋር ክልል የሚገኙት መጋሌ እና አብአላ የተባሉ አካቢዎች በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ

የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አሕመድ የአብአላ ከተማ ህወሓት በሚመራቸው ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር መግባቱን መረጃ እንደደረሳቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ኪልበቲ በተባለው ዞን አብአላ እና መጋሌ ወረዳዎች በኩል ህወሓት ጦርነት እንደከፈተ ገልጿል። የአፋር ክልላዊ መንግሥት በከባድ መሣሪያ የታገዘ ባለው እና በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በሚካሔደው ጦርነት “በርካታ ንፁሀን” መጎዳታቸውን በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነት ማቆሙን ካሳወቀ ጀምሮ ቂልበቲ ረሱ ተብሎ በሚጠራው ዞን ሁለት አካባቢ በሶስት ወረዳዎች ጦርነት ሲካሔድ እንደቆየ የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አሕመድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። አቶ ጋአስ የአብአላ ከተማ በዛሬው ዕለት በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መግባታቸውን የሚጠቁም መረጃ እንደደረሳቸውም ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በህወሓት ተያዘ ስለተባለው አባላም ሆነ ስለደረሰው ጉዳት የኢትዪጵያ መንግሥት የሰጠው መግለጫ የለም።
የቪዲዮ ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  የጄኔቫው ተቃውሞ - ዓለም ስለአማራ ህዝብ መከራ የሰማበት መድረክ | የራያው ጥቃት የአብይ አህመድ ፕሮጀክት ነው፥

2 Comments

  1. Instead of bowing to pressure from the US and west, the Abiy government should discharge its responsibility of protecting citizens. The government`s policy of deterrence is not working against the TPLF and an all out miliarty operations is needed for peace and stability in the country. Action not rhetoric now.

  2. ዛሬም በፊትም ተናግረናል። ወያኔ እያለ በምንም መንገድ የሃበሻይቱ ምድር ሰላም አይኖራትም። ጠ/ሚሩና የጦር አበጋዞቹ በአዲስ አበባ ይህን ያን ሲሉ ወያኔ በትግራይ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ለመሆኑ የሚያናፍሰውን የፈጠራና ምድር ተጎታች ወሬ ማዳመጥና ማየት በቂ ይሆናል። ሲጀመር ወደ መቀሌ ላለመግባት የተወሰነው ውሳኔ ለወያኔ ጊዜ የሰጠና በተሻለ ቁመና ላይ እንዲሆን ያስቻለ ነው። እንዴት እቃው የተዘረፈበት፤ ከብቱ የተነዳበት፤ እህሉ ታጭዶ የተወሰደበት ወገን እቃውን ለማስመለስ ሌቦቹ ያሉበት ድረስ መግባት ይከለከላል? ሴራው አጥንት የዘለቀ ነው የምንለውም ለዚሁ ነው። የአማራንና የአፋርን ህዝብ ብሎም የኤርትራን መንግስት ለወያኔ ሾተላዪች መተው ከጊንጥ ጋር አብሮ እንደመተኛት ይቆጠራል።
    ድንፋታ በአማራ ክልል፤ ድንፋታ በአፋር ክልል፤ ድንፋታ በፌዴራል መንግስቱ በኩል ጉረኛ ከመባል ሌላ ምንም ያተረፈው ነገር የለም። ጀግና ሥራው ሁሉ በተግባርና በልቡ ነው። የሚመሰክሩለትም ከጎኑ ብርድና ሙቀቱን፤ ረሃብና ጥማቱን ተጋፍጠው ከጠላት ጋር ግንባር ላይ የተሰለፉት ብቻ ናቸው። በቅርቡ በአዲስ ዘመን ከተማ የቀብር ስነ ሥርዓቱ የተከናወነው የብርጌድ መሪ ሞት የሚያሳየው ጥልቅ ሚስጢር አለ። የብርጌድ መሪ እስኪሰዋ ደረስ የሚያደርስ ፍልሚያ እንደነበረ ነው። ይህ ደግሞ የወያኔን ቁርጠኝነትና የክፋት ጥግ ደርቦ የሚያመላክት ነው። እኔ ወያኔዎች ሲማረኩም ሆነ እጃቸውን ሲሰጡ ተገደን ነው የሚሉት የውሸት ጋጋታ እንጂ አምነውበት እንደሚፋለሙ ከሚፈጽሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች መረዳት ይቻላል። የጠ/ሚሩ መንግስት ለወያኔ በጉልበትና በእጅ ተጎንብሶ እንኳን ማረኝ ቢላቸው ታንክ በላዪ ላይ ከመንዳት አይመለሱም። እነዚህ የትግራይ አረመኔዎች ለሰው ልጅ ስብዕና እንደሌላቸው የበረሃና የከተማ ታሪካቸው አስረግጦ ያስረዳል። ጠ/ሚሩ መወሻከቱን ትቶ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ ትግራይን መቆጣጠርና ወያኔን ማጥፋት እስካልቻለ ድረስ ዛሬም ነገም ወያኔ በአፋርና በአማራ ክልል ብሎ በጎረቤት ኤርትራ መተናኮሱና እኛን ስሙ ማለቱ አይቀርም።
    አሁን እንሆ ዳግም ተመልሶ የአፋርና የአማራ ክልልን ወሮ መያዙ የቱን ያህል ልቡ እንዳበጠ ያሳያል። ሲናገሩም “ሸዋ ድረስ ደርሰን የወጣነው ለሰላም ስንል ነው ይሉናል”. ይህ ውሸት ነው። ያው የጠ/ሚሩ መንግስት ትግራይን ለቀን የወጣነው የጽሞና ጊዜ ለመስጠት ነው እንዳለ የፓለቲካ ቱልቱላ። ሁለቱም ሲጨፈለቁ ይዋሻሉ። ሲሞትባቸው ገደልን ይላሉ። ሰው እንዴት ነው አሸባሪ ብሎ በፈረጀው አንድ ድርጅት ይህን ያህል ግፊትና መከራ የሚወርድበት? ዋ በህዋላ ቋሚ ነገር አይኖርም። ሃገሪቱን የሶሪያና የየመን ምሳሌ ትሆናለች። ተው እናንተ ኦሮሞዎች የእድሜ ልክ ፓለቲከኞች አዲስ አበባ ላይ ተቀምጣችሁ እሳት አታቀብሉ። ለህዝባችን አይጠቅምም። 60 ዓመት ሙሉ እንዘጥ እንዘጥ አላችሁ የት አለ ፍሬው? ሰው እንዴት መንገድን ቀይሮ ህይወትን አያያትም? ስታሳዝኑ። አሁን ማን ይሙት በኦሮሞ ልጆች ላይ ያኔና አሁን ስንት ግፍ የፈጸመው ወያኔ ጋር የኦነጉ ሸኔ አብሮ መሰለፍ ነበረበት? የሃበሻው ፓለቲካ የውሻ ፓለቲካ ነው የምንለው ለዚሁ ነው። ሲነካከሱ መኖር። ተነክሶ የሞተውን ትቶ ተነክሶ የዳነውን ሌላው ነክሶ የሚገድልበት የመበላላት ፓለቲካ።
    አፍሪቃን ነጮቹ የጨለማው አህጉር ቢሉት የሚያስደንቅ አይሆንም። ጸለምትነቱ ከምድሪቱ ሳይሆን ከሰዎቹ ባህሪ ጋር ነው። እንሆ አሁን በጊኒ፤ በማሊ እንዲሁም በቡርኪና ፋርሶ መፈንቅለ መንግስት ተደርጓል። ሁሉም የፈረንሳይ ቋንቋ ተናጋሪዎችና እልፍ ችግር ያለባቸው ሃገሮች ናቸው። አለቃ እንሁን ያሉት ግን ጠበንጃ አንጋቾች ወታደራዊ ሃይሎች ናቸው። አያሳዝንም? ጠበንጃ ያነገተ ሃይል የሰው ልጆችን መብት ሲያስጠብቅ በታሪክ ታይቶ አይታወቅም። የጸደዪ የዓረብ ግርግርና ለውጥ መሻት ያመጣው አል ሲ ሲን በግብጽ፤ በቱኒዚያ አሁንም ድረስ ግርግር፤ በሊቢያ የወሮበላ ጥርቅም፤ በሌሎችም የአረብ ሃገሮች ግድያና አፈናን ነው። የተለወጠ ነገር አንዳች የለም። ለውጥ እንዳይኖር ከህዋላ የሚነድን የውጭ ሃይሎች ቀን ተሌት ይሰራሉ። ይህ ዓሊ የማይባል ነገር ነው። ዛሬ የመን ላይ የሚዘንበውን ቦንብ የሚያዘንቡት ሳውዲዎች በዓለም ላይ ካሉ መንግስታት ውስጥ ጨካኝና አረመኔዎች ናቸው። የሚደገፉትና የሚታጠቁት ግን በምዕራባዊያን ሃገራት ነው። ምንም አይነት የወንጀል ክምር ሳውዲ ብትሰራ አሜሪካ ትንፍሽ አትልም። ጥቅሟ ከነዳጅ ጋር እንጂ ከሰው ልጆች መብት ጋር አይደለም። ለዚህም ነው ለትግራይ ህዝብ ያለቀሱ መስለው ሲንጣጡ የአዞ እንባ እንደሆነ የምናውቀው። አሁን በአፋር ክልል ተያዙ የተባሉት ስፍራዎች በጥናት ወያኔ የያዛቸው እንጂ በዘፈቀደ የተያዙ አይደሉም። ስለሆነም በዚህ ግንባር ያለውን ክስተት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ግንባሮች ጦርነት እንደሚከፍት እርግጠኛ መሆን አለብን። ወያኔ የሚያርፈው የሚያሰልፈው ሰራዊት ሲያልቅበት ብቻ ነው። ያኔ እጅ ወደላይ ሳይል ነገሩ ይገታል። ውጊያው ቀጣይ ነው። ምንም የሚያቆመው ሃይል አይኖርም። ድርድርና የሰላሙ ጥሪም የዓለምን ህዝብ ለማታለያ የሚጠቀምበት እንጂ ለትግራይ ህዝብ እያለ ያለውን በራሳቸው ቲቪና ሬዲዮ ላይ ማዳመጥ ይቻላል። ክተት ሰራዊት ነው ጥሪው። ይህ የሞት ጥሩንባ ወያኔ እስካልጠፋ ድረስ ህዝባችን እረፍት አያገኝም። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share