January 22, 2022
36 mins read

የትግራዮ ሕወሃት ” የላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ትርክት። – ተዘራ አሰጉ

TPLF 7እየ መሸ እየ ነጋ፣ ሰዓታት ቀንን ፣ ቀናት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታት እየተፈራረቁ ይነጉዳሉ። “ውሃ እያሳሳቀ ይወስዳል “ እንዲሉ የወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት ወደ እናት ምድራቸው ጎንደር አቤቱታ ቢቀርብ ፣ የሕግ ያለህና የመንግስት ያለህ ቢባል “ጆሮ ዳባ” ተብሎ ለ28 ዓመታት ምላሽ ባይሰጠውም፣ በጉልበት እንደተወሰደው በጉልበት ተመልሷል።

ክብርና ሞገስ ለጀግናው ወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ።በማንአለብኝነት የጎንደርና የአማራ ፅጋና በረከት ለመውሰድ መቋመጥና አስሩን መዘላበድ “የላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ “ አይነት ህሳቤ ነው።

“የዝብሪት ቤት ሳይዘጋ ያድራል” እንዲሉ የወልቃይት ፣ጠገዴና ጠለምት ለም መሬቶች የሚገባውን ያህል ታርሶ ለሃገርና ለወገን ሳይጠቅም በዕልህና ብግትርነት እንዲሁም “የኔ ነው፣የኔ ነው” በመባባል እና ባለቤት ባልሆነው የትግራይ ዘራፊ ቡድን በግፍ በቀኝ ግዛት ተይዞ የሚገባውን ያህል ጥቅም ላይ አለመዋሉ ያሳዝናል።

ይህ ትውልድ ሊገነዘበው የሚገባውና ፍራቻው እንደ እስራኤል እና ፍልስጥኤም የይስሃቅ እና የያዕቆብ የአብረሃም ልጆች የኢትዮጲስ ልጆች ሳቫና(ትግሬ) ከለው(አማራ) ነገዶች በግጭትና በጦርነት በመሬት የይግባኛል ፍጭት፣ስግብግብነትና የህውሃት የመስፋፋት ሃባዜ እየተፋጁ ዘመናቸውን እዳያሳልፉ ምክራችን እንለግሳለን።

ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የአማራና የጎንደር ሕዝብ ከቅድመ አያቶቹ ፣አያቶቹና ከአባቶቸ የወረሰውን ትዕግስት ተላብሶ ጥያቄውን አቅርቧል ። የሕወሃት ቡድንና ስግብግብ ምሁራን የሚያነሱት እንቶፈንቶ “ሊበሏትን ያሰቧትን አሞራ ዥግራ ናት ይሏታል

እንዲሉ” ” ጠ” በ”ፀ” እየቀየሩ ፣ እነ አዳርቃይን“አዲአርቃይ”፣ጠገዴን ፀገዴ፣ ጠለምትን ፀለምት፣ ወ. ዘ.ተ. እያሉ የቋንቋ መወራረስ እና ግእዝ፣ትግረኛና አማረኛ የሚያመሳስላቸው የልሳነ ቋንቋ /Dialect/ ተምሳሎትን ዘንግተው ጀሮአችን ያደነቁሩታል።

ከዛም አልፎ ዐፄ ፋሲል” የጉድ ሃገር እንዲሉ የ”ጎ” ን ፊደል የከተማ የዕራይ የታላቅ ዋና ከተማነት ተከትለው እነ “ጕርጎራን” ፣

“ጉዛራ” ፣ “ጎመንጌ” ላይ ከትመው የነበረ ቢሆንም ከዛም አፄ ፋሲል ከባዕታዊያን የተነገራቸው ትንቢት እውን ሆኖ “ጎንደርን” በዘላቂነት ለከተማነት እንደመረጡ ታሪክ እንደዘገበውና እየታወቀ ለነገሩ “ ጣናም የእኛ ነው” ብለው የለ። የትግራይ ዣቫረሞች

“ጎንኅ -ህደር” በማለት እኛ ነን የጎንደርን የከተማ ስም ያወጣነው ብለውናል።

እነ ስጥ እንግዲህ፣ እነ አያልቅባቸው፣ እነ ቆርጦ ቀጥል በጦርነቱ ሲለበለቡ እንደ ጅግራ ሾሃቸውን ይዘው ብቅ አሉ። ሁሉ ኢትዮጵያዊ ትግሬ ነው አሉ። “ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር የለችም” እንዳላሉ እነ እስስት “የሁሉ ኢትዮጵያዊ ዘር ቢሳብ የትግሬ ደም አለበት” አሉ። ይሄን ለኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫውን እንዲያደርግ እየጠየቅኩ ፣ ጀሮ የማይሰማው የለም፣ እነቆረቆር” ወልቃይት ከ 40 ዓመት በፊት የትግራይ ነበር” ይሉናል።

እነ ሙት ወቃሽ “ዐፄ ኃይለሥላሴ ናቸው እራያና ወልቃይትን ወደ አማራ ጎንደርና ወሎ ተቆርጦ እንዲገባ ያደረጉት” ይሉናል። ከኢትዮጵያ ውልደት ጅምሮ እንዲያው ይቅርቡን ስናይ በአፄ ሴሲኒዮስ፣በአፄ ፋሲል፣ በአፄ ቲዎድሮስ፣ በአፄ ሚኒሊክ፣ በጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም ዘመን ወልቃይት የማን ነበር?። እግዞነ ፣ የጉድ ሃገር ፣ እንዲያው የውሸት ቋት አይደላችሁ!!

እስኪ ይህን መሰረት አድርገን እኛ አማሮች መምህራቸው ነንና ትንሽ ታሪካዊ ጭብጡን አጠር አርገን እንተንትንላቸው።

ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የጎንደር አማራ አካል ስለመሆናቸው የታሪክ ማስረጃዎች ታሪክ፤ቱፊትና አባቶቻችን በአደራነት አስረግጠው እንደነገሩን ከላይ የተዘረዘሩት የወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት ግዛቶች የጎንደር አካል እንጂ የትግራይ ሆነው እንደማያውቁ እንዲሁም በነዚህ ቦታዎች የሰፈሩት ህዝቦች የጎንደር አማራ እንጂ ትግሬዎች በጭራሽ እንዳልሆኑ በሚከተሉት አምስት ርዕሶች ለይተን እንመልከት:

የወልቃይትና የትግራይ የቋንቋ መስተጋብር

ከላይ የተዘረዘሩት ወረዳዎች ሕዝቦች አካቶ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማለት የጠገዴ ፤ የጠለምት ፤ የበየዳ ፤ የቋራና የጎንደር አማረኛ ነው። ወልቃይት ፤ ጠገዴ፤ ጠለምት እና ራያ ከትግራይ ጎረቤት በመሆናቸው የተነሳ ከተከዜ ወድያ ያለው ህዝብ አማረኛን ፤ ከተከዜ ወዲህ ያለው ህዝብ ትግረኛን ቋንቋን ይንተባተቡበታል ፡፡ ይልቁንም የወልቃይት ህዝብ እና መሬቶች በገፍ ጥጥ የሚመረትባቸውና መዘጋዎችም (ወልቃይት፣ጠገድቸዎችና ጠለምቶች)ጥጥ ማምረት የተካኑበት ሙያ ስለሆነ የትግራይ ተወላጆች በጥጥ መልቀምያ ወራቶች በየአመቱ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ስለሚጎርፉ አማሮቹ ለመግባባት ሲሉ ትግረኛውን እንደለመዱ እንዲሁም ጥቅሙን ያወቁ ትግራዊያን የወልቃይት ልጃገረዶችን እያገቡ እዚያው መቅረት ስላዋጣቸው አማራዎች ወልቃይት ጠገዴዌች ትግራኛውን ቋንቋ በመጠኑ በማሻሻል ትግረኛን እንደጎልዳፋ ሁለተኛ ቋንቋ አርገው እስከዛሬ ድረስ ይጠቀሙበታል፡፡

2)የአይማኖት ልዮነት

እብራዊያን በኢትዮጵያ ኗሪ ከመሆናቸው በፊት የኩሽ ነገዶች ሁሉም እምነታቸው የነበረው በግብፅ፣የሲዶን፣የባቢሎንና የፋርስ ጣዖታት ነበር። እስራኤላውያን ወደ ኢትዮጵያ ከዘለቁ ጀምሮ በተለይ ታቦተ ፂዮን እንደ ክብረ ነገሥቱ አተራረክ ደብረ-ሣህል / ደብረ -መከዳም ተብሎ በሚጠራው – ዛሬ ግን ጣና ቂርቆስ በሚባለው ቅዱስ ቦታ ካረፈች ወዲህ ጀምሮ ከተከዜ እስከ በሸሎ እንዲሁም እስከ ፈጣም ወንዞች የነበረው የአገውና የቤጋ(የቤጃ) ኩሽ ሕዝብ የእብራዊያን ዕምነት ሲቀበሉ ፣ ከተከዜ በስተስሜን የነበሩት የኩሽ ነገድ ልጆች( የበለው ልጆች ) ግን አክሱም ክርስትናን እስከትቀበለችበት ወቅት ድረስ ከጣዖት አምልኳቸው

ስይላቀቁ ቆይተዋል ። የሴም ዘር የሆኑት ነገደ ሳባ ከተከዜ በስተስሜን በሚገኘው ምድር ገብተው አጋዚያን ተብለው በኩሽ ልጆች ከሰለጠኑ በኃላ እነዚህ ሳባዊያን የእብራዊያንን እምነታቸውን እስከ ዘመነ አብርሃ-እፅብሐ ድረስ ቀጥለውበታል። እንብረም የተባለው ኦሪታዊ ሊቀ-ካህንም አክሱምን ወደ እብራዊያን ዕምነት ለማስገባት ሲል በአክሱም ከተማ ሲኖጎግ ከፍቶ ደብረ-ሣህል ድረስ እየዘለቀ መስዋእት ያቀርብ እንደነበርና አብርሃ አፅብሃንም ወደ ኦሪት ለማስገባት ይጥር እንደነበረ ታሪክ ይናገራል። አክሱም በ330 ዓ.ም. ክርስትናን ስትቀበል የደብረ-ሣህሉ ሊቀ-ካህንም እንብረም ከአብርሃ-እፅብሐ ጋር በውዴታ አብሮ ተጠምቋል። እንዲያውም የአባ ሰላማ ፍርምኒጦስ አጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል ።

የአሁኑን አያድርገውና ቀደም ባለው ዘመን ትግራዊያን ክርስትናን ሲከተሉ ወልቃይት፣ጠገዴ፣ ላስታ፣ ቡግና ወ.ዘ.ተ. የኦሪት ሃይማኖትን ይከተሉ ነበር።

3)የአስተዳደር ክልል ልዩነት

ወልቃይት ሆነ ጠገዴ ወይም ጠለምት በአክሱም ፣ በላስታ፣በሳይንት ሆነ በጎንደር ዘመነ መንግስት አንድም ግዜ እንኳ የተከዜ ወንዝ የተፈጥሮ ደምበር ተጥሶ የትግራይ አካል የሆነበት የታሪክ ወቅት የለም። ይህን እውነታ ለመረዳት ከጎንደር ዘመነ መንግሥት በፊት እንስቶ እስካሁን የታወቁ የውጭ ሃገር ጎብኝዎች በተለያየ ክፍለ ዘመናት ኢትዮጵያን እየተዘዋወሩ ከጎበኙ በኋላ ስለብሄረሰቦችና ስለ ውስጥ አስተዳደር አከላለል ከተበዋል ፅሁፎችና ካርታወች መካከል የሚከተሉትን እንመልከት ።

የቅጥፈቶች አካል የሆነው የትግራይ የታሪክ ተንታኞች እነ ካህስይ( መፅሃፍ አለን የሚሉት የሱን ቁንፅል) ክትብ እያነበነቡ ነው። ደጃች ውቤ ጎንደር ደረስጌ (በየዳ) ላይ መቀመጫቸውን አድርገው ከተከዜ ማዶ እስከ ቀይ ባህር ያለውን ደርበው ፣ የትግሬውን የደጃች ሳባጋዲስ ልጅ አግብተው ገዙ እንጂ የትግራይ ፀሃፍት ለማደናገር ደጃች ውቤን የትግራይ ተወላጅ ናቸው በማለት ነጥብ ሊያስቆጥሩ ቢሞክሩም መሰሬ መሰረተ ሃሳባቸው ከእውነት የራቀ እና የሚያስተዛዝብ ከመሆኑ ባሻገር ፣ ደጃች ውቤ በአባታቸውም ሆነ በእናታቸው ጎንደሬ መሆናቸው የተረጋገጠ ነው። ከሁሉም የሚያስደምመው ደጃች ውቤ ትግራይ ምድር ላይ ሆነው ከተከዜ ደቡብ ያለውን አገር አስተዳደረዋል የሚለው የበሬ ወለደ የለመደባቸውን ቅጥፈት ከታች በማስረጃ አጣቃሽነት የተከተበው (Footnote) እንደሚያሳየው እነ ፕርኪንስ(Parkince) በሚገባ በበመፅሃፋቸው አስረግጠው ከትበውታል።

በአፄ ቴዎድሮስ ፣ በአፄ ዮሃንስ፣በእፄ ምኒልክ ሆነ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስታትም ከተከዜ በስተደቡብ ያለው እንድም ምድር በትግራይ ዐፄዎች ትገዝቶ አያውቅም። ይልቁንም በትግሬው ደጃች ገብረ ስላሴ ሽፍትነት ምክንያት ደጃች አያሌው ብሩ ወልቃይትን እያስተዳደሩ ሽሬንና አክሱምን በ1822 ዓ.ም. ለራስ ስዩም እስኪሰጥ ድረስ ከ1829-1822 ለሁለት ዓመታት ከሰሜን ግዛታቸው ጋር ደርበው ዳባት ላይ ከትመው አስተዳድረዋል።

ይህን የከተብኩት ወልቃይት፣ጠገዴና ከፊል ጠለምት ከአራባ እመት ሆነ ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ የጎንደር አማራ አካል እንደሆነና እንደነበረ መረጃዎችን በአጭሩ ለምግለፅ ነው። ብዙ በመፅሃፍ ተጠርዘው የተዘገቡ ማስረጃወች አሉ።

_————————

. F.Alvarez (1520-1527)- “Portugise Embassy to Abyssinia “- Refers the map depicted in his book.

.James Bruce, (1768-1773)-“Travels in Ethiopia “ ,3rd volume page 248-252

-Dr.Reverend Michel Rassel, “ Nubia and Abyssinia “ -Refer the map of Ethiopia at his book preface

-Mansfield Parkins , (1968) , “Life in Abyssinia”, 1st Volume-See the the earliest map of Ethiopia in his book preface

-Mansfield Parkinson ,(1968), “Life in Abyssinia “ ,2nd Volume ,,Page 106

ማስረጃወችን በመጨረሻው ገፅ ይመልከቱ።

የባህልና የቅርስ ልዩኑት ፣

ወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት ፣ ወገራና ጯሂት የአማርኛ ዘፈን፣ለቅሶ፣(ወይታ)፣ፉከራ፣ቀረርቶ(ሽለላ) እና እንጉርጉሮ የመፍለቂያ የታወቁ ቦታወች ናቸው። የጎንደር ዘፈን በፋሲለደስ ባህላዊ ኪነት የሚቀርቡት እስክስታና ውዝዋዜዎች ሁሉ አብዛኛው ከነዚህ ወረዳዎች የመነጩ ናቸው። የወልቃይት ፣ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ በትግርኛ መዝፈን፣ማልቀስ፣መፎከር፣ማቅራራትና ማንጎራጎር ከቶ አይቻለውም።

በትግራይ እና በወልቃይት ጠገዴ ያለውን የቅርስ አተያየት እንድምታ በተመለከተ በጉዲት የተፈጠረውን ልዩነቶች ወደጎን አድርጎ ከጎንደር መንግሥት ምስረታ ወዲህ የአክሱምን ቅርሶች እንደ ራሱ በባለቤትነት ስሜት የሚመለከታቸው ቢሆንም ጎንደሬው ወልቃይቴ በራሱ የዕንፀት ጥበበኛነት ክህሎት እና በጣና ሃይቅ በሚገኙት ገዳማት ፣ ከቋጥኝ ድንጋይ በተፈለፈለው የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም ውብ እና ግሩም ሆነው የእየሩሳሌም አምሳለ ሕንፃዎች መስለው በተገነቡት የጎንደር ቤተ መንግሥታትና አብያተ ክርስቲያናት በኩራት ይደመማሉ ።

የፍላጎት ልዩነት

ሕውሃት ወልቃይትን ሙሉ በሙሉ ፣ ጠገዴንና ጠለምትን በከፊል ወደ ትግራይ በማንአለብኝነት ወደ ማካለሉ ተቻችሎና ተግባብቶ አብሮ በወንድማማችነት የመኖሩን ህላዌ እና ቀደም ትብዕል የጣሰ ከመሆኑ ባሻገር ተከዜን ያህል የተፈጥሮ የድንበር

ማካለያ አሻራ እያለ በምንእብ ባወጣው ተቀባይነት በሌለው ካርታው ማካለሉና መለጠፉ ሕግ ወጥነትን የሚያሳይ እንጂ ማንም ሆነ ማን የኒዚህን ወረዳዎች ሕዝቦች ጎንደሬነትና አማራነት ማንም ሊፍቀው እይችልም። የእነዚህ ወረዳዎች ሕዝቦች ጎንደሬዎች እና የጎንደር መሰረቶች እንጂ ትግሬ መባልን የማይሹ እና የሚያንገፈግፋቸው መሆኑን ሕወሃት ሊረዳው የግድ ይላል።

የወልቃይት ፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ይሄን ቁርጥ አቋሙን በተላያዩ ጊዜዎች እና መድረኮች እንደሚክተለው በቆራጥነት አሳይቷል :

ሀ)በሕወአት ምሥረታ የመጀመሪያ ክብረ በዓል ከወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት 12 የሚሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ወደ መቀሌ ተጉዞው ነበር። ለበአሉ በተዘጋጀው ግብዣ ላይ የሕወአት ባለሥልጣን ንግግር ሲያደርጉ “ወልቃይት ጠገዴ ወደ ትግራይ -ክልል-፩ በመጠቃለላቸው ደስታቸውን እንዲያስተላልፉላቸው ሕዝቡ ወክሎ የላካቸው መልዕክተኛ በመካከላችን ተግኝተዋል” በማለት ሲያብራራ 12ቱ ተጋባዦች በአንድ ላይ በቅፅበት ከግብዦው ቦታ በመነሳት ግብዣውን ጠቅጥቀው በመውጣት በእግራቸው በመጓዝ ወደ ወልቃይት በቅሬታ ተመልሰዋል ።

ለ)የወልቃይት ፣የጠገዴና የጠለምት ሕዝብ ጉዳዩን በሰላም መንገድ ለመፍታት በተለያዩ ጊዚያት ደጋግሞ መልክተኞችን ወደ ባህር ዳር ፣ጎንደርና እዲስ አበባ ልኳል ነገር ግን ጥረቱ ውጤት ለማግኘት ባለመቻሉ እኛን ለማይወክለን የትግራይ ክልል ግብር ኣንከፍልም ፣የብሔራዊ አገር አቀፍ ምርጫ ምዝገባ ተካፋይ ለመሆን በክልል ፩ ስር ሆነን ለመመዝግብ እንሻም የሚል የጋራ እቋም በመያዝ ለበላይ አካል ወደ አዲስ አበባ በሚያዝያ ወር 1986 ደብዳቤ ለመላክ መገደዳቸው ይታወቃል፣ ተዘግቧልም።

ሁሉም አማራ አካባቢ ያሉ በጎጃም፣በወሎና በሽዋ የሚከወኑ የአማራ ባህላዊ መቸቶች በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ይንፀባረቃሉ።

የወልቃይት ፣ጠገዴንና ጠለምት ሕዝብ የሕውሃትን ስግብግብነት፣ የመስፋፋት መሻትና አባዜና እርኩስ ዓላማቸውን በመረዳቱ “አትደረሱብን፣አንፈልጋችሁም” እያለ ይዋጋችውና ያንኮታኩታቸው ነበር።

ነገር ግን መሰሪው ሕወሃት በውጊያ አልቻለው ሲል በ1972 ዲማ(የአያቶቼ አፅመ እርስት ነው”) የወልቃይት፣ጠለምትን ሕዝብ ለስብሰባ ጠርቶ በደካማ ጎናቸው በመግባት “ከእባብ እንቁላል ምን ይገኛል” እንዲሉ ያደረጉት የክህደት ስራ ገራሚ ነበር።

የወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት ሕዝብን ሲደልሉ “ እናንተና እኛ ወንድምማቾች ነን፣ መሬታችሁን አንፈልግም፣ ዋናው ጠላታችን የደርግን ስርአት በጋራ ካስወገድን በኋላ በወንድምነታችን በሰላም እንኖራልን” ብለው ቃል ከገቡ በኋላ ፣ የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ሕይዎቱን ስውቶ ከሥልጣን ዕርካብ ካቆናጠ ጣቸው በኋላ ፣ ከዳቸው። ከዚያ አልፎ ትንፋሽ ሲያገኙና ኃይላቸው ሲፈረጥም ወልቃይት ፣ ጠገዴና ሰቲት ሁመራ “የእኛ ነው በሚል የስስታምነት፣የመስፋፋትና የኢኮኖሚ የበላይነት መሻት” ወደ ትግራይ አካለው ለ27 ዓመታት ገደሉ፣ አፈናቀሉ። የራሳቸውን ሚኒሻ በገፍ/Demography / ለመቀየር የሕዝባቸውን ቁጥር በወልቃይት፣ጠገዴ በማስፈር ግፍ ፈፀሙ።

የነኮለኔል ደመቀ “በቃን ከሕውሃት ጋር” ማለት እነሱ እንደሚደሰኩሩት መሰረተ ቢስ ክስና ተራ ውንጀላ ሳይሆን በሕውሃት በመካዳታቸው ምክንያት እንደሆነ ፍትው ያለ የአደባባይ ሚስጥርና እውነታ ነው።

የዘመኑ የአብያችን ተደራዳሪዎች ይህን መሰሬ አቋማቸውን እንዲያስቡበት እየጠቆምን ያደረጉት የክህደት ክዋኔ የአማራና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቀው ይገባል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቀው የሚገባው ለሕውሃትና መሰሎቹ ጥቅም ሲባል አማራን ሳያካትት የተረቀቀውና የፀደገው ሕገ-መንግሥት ለሕዝብ ውይይት ለይስሙላ ሲቀርብ ወንድም የሆነው የሶማሊያ ተወካዮች “በአማራ ሕዝብ የነበረን መሬት ወደ ትግራይ ከማካተት በፊት ለምን የሕዝብ ውሳኔ /Referendum/ አይደረግም” ብለው ሃሳብ አቅርበው ነበር።ይህን ሃሳብ ግን አሻፈረኝ ብለው የወልቃይት፣የጠገዴንና የጠለምት ሕዝብ ከምድረ ገፅ የማጥፋትና ቁጥር የማሳነስ ግፋቸውን ቀጠሉ። “የእኛ የትግሬዎች ነው” በሚል የእውሸት ትርክት በትግራይ ካርታ አካተው አወጡት።

ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቀው የሚገባው ነባራዊ ጉዳይ በደርግ መንግስት መውደቅ ማግሥት ወዲያውኑ የሕዝበ ውሳኔ/ Referendum/ ቢደርግ ኖሮ 99%ቱ የወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ “እኛ በጎንደር ክፍለ ጠቅላይ ግዛት ስንተዳድር የነበርን አማሮች ነን ፣ በነበርንበት ግዛት እንቀጥላለን” ይሉ እንደነበር ጥርጥር የለውም”

ሰጥቶ ተቀባይ ለምምስል የሚያደርጉት መፏገር፣

መቸም ሕውሃት ሲባል የተንኮል ቀንዲል ነው። ሰሞኑን የያዙት ዲስኩር ቅጥ ያጣ ሁኗል።

“እኛ ሕውሃቶች የመስፋፋት ህሳቤ አልነበረንም፣የልንምም፣ቢሆንማ ኑሮ በአፋር በኩል የነበረንን መሬት አብሮ ለመኖር ሲባል ወደ አፋር እንዲካለል አናደርግም ነበር “ ማለት ጀምረዋል።

ይህ አነጋገራቸው “የምጣዷን ብላ ፣ የእንቅቧን አጣች” እንዲሉ ይህን ያደረጉት ወልቃይት፣ጠገዴንና ጠለምት በምክንያታዊነት ነው የወሰደነው ለማለት እንደሆነ ማንም ፊደል የቆጠረ ያውቀዋል።

እነ ተንኮል ልብሱ ያሴሯት ሴራ ይልቁኑ በኤርትራ የሚገኘው የአፋር ሕዝብ ፣ ከኢትዮጵያ አፋር ሕዝብ እንዲለያይ የሰሩት ደባ የአፋር ሕዝብ ይቅር የማይለው ነው።

የድፍረታቸው ድፍረት የአምናውን ዕፀፃቸውንና ኢትዮጵያን እንደ ቅርጫ እንድትሸነሸን ማድረጋቸው አንሶ አዲስ ካርታ ለመሳል ሲዳድ ማየት “ ቀድሞ ነበር እንጂ ማጥኖ ማደቆስ” እንዲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ፣ ወሳኝም ፣ሃሳብ አቅራቢም የወያኔን ኢትዮጵያን የማካለልና የማዋቅር ሃሳብ አይቀበልም፣ ቋቅ ብሎታል የእናንተ እንቶ ፈንቶና መርዛማ ሴራ ለመስማት ጀሮ የለውም።

መቸም ሕውሃት በማደናገር /conisparecy/ ተወዳ ዳሪ የለውም።

ለራሱ ቀጣይ ሸፍጥ ሲል ያላደረጋቸው ነገር የለም። የአባይ ግድብ የአማራ ባለቤትነት ለመንፈግ ሲል ቤንሻጉል የሚባል አዲስ ክልል ፋጠረ።

የአማራ ወንድም የሆነውን የአገው ቅማንት ከወንድሙ የጎንደር ህዝብ ጋር አብሮ በሰላም እንዳይኖር መርዝ እረጩበት። ደጉን የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያ ጠል እንዲሆንና የመገንጠል ስሜት በሕሊናው እንዲያሳርፍ አደረጉት።

ይህ ሁሉ ሆኖ ከለይ የተዘረዘሩትን ብሄሮች ኢትዮጵያ ጠል እንዲሆኑና አልተሳካልትም እንጂ ወዳጅ አድርጎ የአላማው ማሳኪያ፣ የጥፋቱ ተባባሪ፣ እርስ በርስ ተቆርቋሪ “የአይጥ ምስክር ድንቢጥ” እንዲሉ የክፋት ጭቃ ሹም ሊያደርጋቸው በተለያየ ጊዜያት ሞከሮታል።

እነ “እፍረት የለሽ” በዚህ ችግር ላይ በወደቁበትና ወጣቱን ትውልዳቸውን ባስፈጅበት ጊዜ የሚዘገንን ህሳቤ ያቀርባሉ። “ሰላም እንዲወርድና ለድርድር መንገድ ይከፈት ዘንድ ወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምትና ሁመራ ሕውሃትና መንትዮቹ አማራን ሳያካትት ባፀደቁት የይስሙላ ህገ መንግስትና የክልል አከላል መሰረት/status quo ante/ ተጠብቆ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ወደ ክልል አንድ

ትግራይ ይመለስ” የሚል የተንኮል ማደናገሪያ አሳብ እያቀረቡ ይገኛሉ ።

“ዙር ዙር እምቦጭ” እንዲሉ የወልቃይት/ ወርቃዊት/፣ጠገዴና ጠለምትን ጥቅም በአለፉት 27 ዓመታት ምን ያህል እንደጠቀማቸውና መቀሌን አሽቆጥቁጦ፣ የደረቀና የገረጣ ፊታቸውን “ቅቤ እንደተቀባ ቅል” ስላብለጨለጨው በታሪክ የነሱ ያልሆነን መሬት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊና እንደዚህ ቀደሙ እየሰሩና እያረሱ መኖር ሲችሉ “በኛ ክልል ካልተካተተ” ማለቱ የጤናም አይመስልም።

ማንም እንደሚያውቀው የትግሬን ተንኮል እንደ ሽዋ የተማረ ሕዝብ ከሥር መሰረቱ የሚውቀው የለም። ትግሬ ለሽዋ ሕዝብ ያለው ጥላቻ ከልክ ያለፈ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ “ የሽዋ ንገሥታት ዘራቸውና ደማቸው ከትግሬ የተሳበ ነው” ሲሉ ለሰማ ለጀሮ ይቀፋል። በዚህ አጋጣሚ ሽዋወች ቢሰሙ “የዘር ማጣሪያ ምርመራ “DNA’ ይደረግልን እንደሚሉ ጥያቄ የለም። ወዴት ወዴት ህወሃት ስታቀነቅነው የነበረውን የሽዋ ነገስታትና ምሁራን ጥላቻ ረሳችሁት?።

ለነገሩ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ከላስታ አማራ ሳይንት ነገስታ ት ዘር የተሳበው ይኩኖ አምላክ ታሪክ ለዚህ መልሱን ይሰጣል። ወገኖች ታሪክ አንብቡ።

ሰሞኑን ደግሞ እነ ምስጥ ድርድር ሲባል አራጅ፣ፋሽሽት፣ገዳይ ሲሉት የነበሩትን ፕራይ ሚኒስተር አብይና ብልፅግናን መወረፍ ትተው የመለሳለስ አካኤድ እያሳዮ ነው። ምን ይሆን ከጀርባ ያሰቡት ሴራ? አንድ የሚሸት ጉዳይ እማ አለ። ወገን ተጠንቀቅ!!

ማጠቃለያ

ከዚህ ላይ ማወቅ ያለብን የትግራይ ምሁራን፣የሕውሃት አባላትና ደጋፊዎችና አክቲቪስት ተብየወች ተምታቶባቸዋል። ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የትግራይ ግዛት ስለመሆኑ የሃገር ውስጥ ሆነ የሃገር ውጭ ቅንጣት ያህል ማስረጃ የላቸውም።

ቀጣፊ፣መሰሬ፣የሃሰት ሊቅ ፣ መልቲ፣ ሌባ የሆነ ሰው ወንጀሉን በቃለ አሽሞንሙኖ ለመደባበስ ሲሞክር” ከድጡ ወደ ማጡ” እንዲሉ ይቅርታን፣ስላምና መፀትት ወደ ጎን ብሎ ሲዘላብድ ሌ ላ ያልጠበቀው ወንጀል ይፈፅማል።

የአማራና የትግራይ ሕዝብ ወደ ኋላ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሆነ በኋላ ለኢትዮጵያ ያበረከቱት አስተዋፅኦ አይካድም።

አማራው /ኢምራይት/ አክሱም የገነባ በህንዱ ንጉስ ራህማ፣ በየመኖችና በግብፆች እንዳይጎዳ መስዋዕት የከፈለ ፣ የአስተዳደር፣ የውትድርና የዲፕሎማሲውን ስራዎች እየከወነ እክሱም ላይ ለአክሱምና ኢትዮጵያ ገነው እንዲወጡ መስዋት የከፈለ ነገድ ነው።

ትግሬው ደግሞ በአዶሊስ፣ በቀይብሃር ደሴቶች ንግዶችን የሚያጧጡፍ ነገድ ነበር። በዚህ የተነሳ ከየመኖች ጋር የተዳቀለ ነው።

የሁለቱም ቋንቋቸው ግእዝ ነበር። አማራው የውትድርናውንና የአስተዳደሩን ስራ በሚስጥር ለመከወን ሲል ግዕዙን አማረኛ አደረገው። ትግሬዎች ደግሞ ንግድን ለማጧጧፍ ሲል ግዕዙን ትግርኛ አደረገው።

ከዚያም የአክሱም ዘውግ ሲዳከም አማራው ወደ ወገኑ ቤጃ፣ ላስታ ፣ ቡግና፣አማራ ሳይንት፣ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት ፣ቋራ እያለ ወደ ሽዋም ዘለቀ።

ትግሬውም ንግድ ቢቀዘቅዝም አክሱም ላይ እንደሰፈረ ቀረ።

ገረፍ ገረፍ አድርጌ እውነታውን ላስጨብጣችሁ ሞክሪያለሁ “ የአቅሙን የወረወረ ፈሪ አይባልም” እንዲሉ።

የተረፈውን ጥልቅ የታሪክ ሂደትና እውነታ ለማወቅ ከዚህ በታች ያለውን መፅሃፍ እንዲያነቡ እመክራለሁ።

“The Tears of Welkait,Gonder and the Amhara people.

The Contribution and plight of the Amhara people in Ethiopian history and Civilization” Fitaye Assegu Abetew.

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop