January 18, 2022
5 mins read

የኢትዮጵያ ባንዲራ-የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ዓርማ ነዉ – ማላጂ

Amharaአገራችን ኢትዮጵያ እንደ አገር ከተመሰረተች ጀምሮ በቀስተ ደመና መልክ (ቀለም) የሚታወቀዉ አረንጓዴ ፣ ቢጫ  እና ቀይ  ቀለም የህዝብ እና የአገር መገለጫ የማንነት እና የሉዓላዊነት አሻራ እና ምልክት ነዉ፡፡

ይህ የኢትዮጵያ እና ህዝቦች ሰንደቅ ዓላማ ታሪካዊ ፣ጥንታዊ እና ሁለመናዊ ህብረ ቀለም ኢትዮጵያዊ ከመሆኑ ባሻገር ተፈጥሯዊ ፣ ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ይዘት እና ዕዉነት ያለዉ ነዉ ፡፡

ይህ የጥንታዊት ኢትዮጵያ  ጥቁር ህዝብ የነፃነት እና የኩራት መለያ የሆነዉ ሰንደቅ ዓላማ ከኢትዮጵያዊነት በላይ ለአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት እና የድል ተምሳሌት በመሆኑ ወንድም የአፍሪካ ህዝቦች ባንዲራ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ የሚጠቀሙ ስለመሆኑ ማሳያ ቤኒን፣ ጋና፣ጉኒያ…… በቂ ምሳሌ ነበር ነዉ ፡፡

ይህ የኢትዮጵያን የነፃነት እና አንድነት መገለጫ ባንዲራ  ስርዓት መጥቶ በሄደ ቁጥር  የድርጅት መልክት/ ዓርማ በመቀየር እና በመለዋወጥ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ አንይ ማለት ጤናማ ኢትዮጵያዊነት እና ህዝባዊነት አለመሆኑን ለዘመናት ከእኛ በላይ ዓለም ጠግቦታል፡፡

ከፖለቲካ ተቋማት እና ድርጅት ፅ/ቤት  ዉጭ ለሚደረግ የሠንደቅ ዓላማ መኖር የጶለቲካ ድርጅት እና የመንግስት አስተዳደር በተለዋወጠ ቁጥር ይህን ያዙ ፤ ያን አዉግዙ ማለት ቢቆም ዘላቂ መተማመን እና ብሄራዊ መስተጋብር ሊኖር የሚያስችል ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ የህይወት እና የደም ዋጋ የተከፈለበትን የ ፭ ሽ ዘመናት የነፃነት እና ሉዓላዊነት ሠንደቅ ዓላማ ቢሸከም ቀርቶ  ጠቅሎ ቢጎርሰዉ ማንንም  ሊያስደስት እና ሊያኮራ እንጂ ሊያሳፍር አይገባዉም ፡፡

በህይወት እና ደም የተገኘን ማንነት ማክበር እና ማስከበር የኢትዮጵያዊነት ኩራት እንጂ ስጋት ሆኖ አያዉቅም፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የራሳቸዉን ከተግባር የተጣላ ታሪክ ለማንበር በቁማቸዉ ሀዉልት የሚያሰኛቸዉ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የቆየ የማንነት አሻራ የሚያቅለሸልሻቸዉ የጥላቻ እና ክህደት ጅምር ሀሁ….ዛሬ አልተጀመረም ፡፡

ባንዲራ ጨርቅ ነዉ……..የቤተክረስቲያን……..የነገስታት…………እያሉ የዋረዱ፣የወረዱ ፣ የረገጡ፣ ያቃጠሉ……..ለምን ይሆን አዉድ ዓመት ባባተ ቁጥር ጣሉ የሚሉት አታንሱት የሚሉት፡፡ መቸ ነዉ እኛ አገር በምክነያት እና በዕዉነት  የምንቀሳቀሰዉ ፡፡

እኛን ብቻ  ተከተሉ ክፉ የጥላቻ  እና የምቀኝነት ዘመቻ መጋኛ የምንላቀቀዉ መቸ ነዉ ፡፡

ለመሆኑ የአንድ አገር ብሄራዊ ሠንደቅ ዓላማ ከፖለቲካ አስተሳሰብ እና ከግል መሳሪያ አልፎ በነፃነት ዜጎች የእኛ ብለዉ አስከተቀበሉት በነፃነት የሚኖሩበት ፡፡

ዛሬ በአንድም ተቋም በክብር ወጥቶ እና ወርዶ በማይከበር ሠንደቅ ዓላማ ዜጎች በግል፣ በጋራ እና በዕምነት ተቋማት በአዉድ ዓመት ቀርቶ በዕለት ቢያከብሩት ሊያስመሰግን እና ሊያኮራ እንጂ ሊያሳስብ አይገባም፡፡

የዕምነት ተቋማት የቆሙባትን አገር  እና የሚከተላቸዉን ህዝበ አማኝ  የማንነት እና የነጻነት  ዓርማ ከፍ ማድረግ  የሚያስከብር እንጂ የሚያስነዉር አይደለም ፡፡

ስርዓተ መንግስት ሆነ ድርጂት ቀሪ ሲሆን አገር ፣ህዝብ እና ትዉልድ ዘላለማዊ ናቸዉ ለዚህም አብሮ የሚኖረዉ ከኢትዮጵያ ጋር የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎም የአፍሪካ የነፃነት  ምልክት የኢትዮጵያችን ዓርማ ( አረንጓዴ ፣ቢጫ ፤ቀይ ) ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ከታሪክ በመማር ከጥላቻ እና ከበታችነት ጉዳጓድ መዉጣት እንጂ በክፋት እና ምቀኝነት መነታረክ አይደለም ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop