አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገላቸዋል ና ከተቆራኛቸው ድንቁርና እናፋታቸው ዘንድ ዘመኑ ና ጊዜው ግድ ይለናል ።

መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

እንኳን ለባዓለ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ። በዚህ ቀን የማሥተላልፍላችሁ መልእክት ፣ ከራሥ ጋራ ተነጋግሮ ፣ ጥፋትን አውቆ ፣ ራሥን ወቅሶ በንሥሐ ወደ ሰውነት ሥለመመለስ ነው ። ሉቃስ 3 ፤ 7_17

7 .  ስለዚህ ከእርሱ ሊጠመቁ ለወጡት ሕዝብ እንዲህ ይላቸው ነበር፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

8 . እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ በልባችሁም፦ አብርሃም አባት አለን ማለትን አትጀምሩ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንዲችል እላችኋለሁና።

9 .አሁንስ ምሳር ደግሞ በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።

10 . ሕዝቡም ፦ እንግዲህ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር ።

11 . መልሶም፦ ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፥ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ ይል ነበር ።

12 . ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት ።

13 .ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው።

14 ጭፍሮችም ደግሞ፦ እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው።

15 .ሕዝቡም ሲጠብቁ ሳሉ ሁሉም በልባቸው ስለ ዮሐንስ፦ ይህ ክርስቶስ ይሆንን? ብለው ሲያስቡ ነበር፥

16 . ዮሐንስ መልሶ፦ እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤

17 . መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል አላቸው ።

 

ፀጋዬ ገ/መድህን ሮባ ቀዌሣ ፣ ሥለ ባለ ጊዜው ወያኔ/  እህአዴግ  እንዲህ ብሎ ነበር ።

” ..ባለጊዜው  ተንሰራፍቶ ቁጭ ብሎ እግዛብሔርን አይፈራም ። ይዋሻል ይቀጥፋል ። … ”

ሥለ እምነትም እንዲህ ብሎ ነበር ።

በእርግጥ የክርስትና ኃይማኖት ባህላችንን አበልፅጓል ። እሥልምና ኃይማኖት ባህላችንን አበልፅጓል ። ከፈረኦን ኃይማኖት መንጭቶ የመጣው  የገዳ ሲስተም  ሃይማኖታችንን ባህላችንን  አበልፅጓል ። መዋጋት ያለብን ግን መከፋፈልን ነው ።ተቻችሎ መኖር አብሮ መቀጠል ነው ። እንጂ ፤ አትድረሱብኝ  ፤ አንተ የበታች ነህ ፤ እኔ ያልኩት ብቻ እያልን ፤ ቁልቁል ማሰብ የለብንም ። ይሄው አሜሪካንን እናያለን አይደል ? ግማሹ እግዛብሔርን አላውቅም ይላል ፤ ሌላውበሴጣን ያመልካል ። ቨወርቅ የተሰራ የሤጣን ቤተመቅደስ አላቸው ። በወርቅ በተሰራ ቤት ውሥጥ ይጮኻል ።  ሌላ ሰው እስካልነካ ድረስ ሄዶ ቢፈጠፈጥ ፤  ቢያጓራ ማንም ጉዳዩ አይደለም ። ለምን ? መብቱ ነዋ ! ዴሞክራሲ ነው ። እኩልነት ነው ።  ወንድሜ ሄዶ የፈለገውን ቢያመልክ  ፣ ምኔንን ይነካኛል  ? ለምን የፈለገውን አያመልክም ? … ”

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በወሎ ክፍለ ሀገራችን ህዝብ የኃይማኖት መቻቻልና ፣ ቢስሚላሂ እና በሥመአብ ብሎ ባርኮ በጋራ መአድን መቋደሥም ፣ ያወድሥ ነበር ። እንዲህ በማለት ።

ለዚህ ነው ፣ ሰው  ” የተማረ ይግደለኝ  ” ሲል  እኔ ” ወሎዬ  ይግደለኝ ። ” የምለው ። …በማለት ።

ሥለ ኢትዮጵያውያን አንድ ቤተሰብነትም ፣ ታሪክን እያጣቀሰ መሥክሯል ። ( ሰው ከ70 ሺ ዓመት በፊት ዘሩ አንድ ነበር ። የዛሬው ሰው ዲኤን ኤ ቢመረመር  የሥንት ና ሥንት አገር ዜጋ ቅይጥ መሆኑንን ተረዳ ። አንተ እኔ እንትን ነኝ የምትል ፣ ምናልባት ከደቡብብ አፍሪካ ወይም ከሰሜን አሜሪካ ፣ ከማዳጋሥካር ከቻይና ወዘተ የተደባለቀ ዘር የተገኘህ ነህ ይልህና ፣ ወይ ጉድ ትላለህ ።  ዕድሜ ለሣይንሥ ። የዲኤን ኤ ጥናት አያሌ እውነትን ይነግረናል ። ግና እኛ ገና ከድንቁርና ገና ነፃ አልወጣንም ። )

ፀግሽ እንዲህ ይልሃል ።

” እና ቤተሰብ ከሚጨራረስ እራሥን ማወቅና ማክበር ጠቃሚ ነው ።ለዚህም ነው ኦሮሞ ነኝ ማለትህ  ፣ አማራ አይደለሁም ማለት አይደለም ። አማራ ነኝ መለትህ  ፣ ተግሬ አይደለሁም ማለትህ አይደለም ። አማራ ሲል ሓም_ ሓራ ( አዲስ ሔም ) ማለት ነው ።…

…ይህ ነው አማራ ፣ ከየትም ይምጣ  ፤ ግማሹ ከወላይታ  ነው የሄደው  ። አብዛኛው ኦሮሞ ነው ።  ገሚሱ ከመሠረቱ የመጣው ከአማራ ሳይንት ነው ።ከወሎ ላሊበላ ነው ። አገዎች ናቸው ። በዚህ ሁኔታ ነው ከ800 ዓመት በፊት ቋንቋው ሲጀመር የተከሰቱት ።

ሕዝብ በግዕዝ ማምለክ ፣ በግዕዝ መዝፈን በግዕዝ እሥክስታ ማድረግ ፣ በግዕዝ የፍቅር ደብዴቤ መፃፍ ተከለከለ ። ገበሬው ደግሞ ሌላ ሥራ የለውም ። ጎመኑን በምን ይግዛ ?  በግዕዝ ካልተገለገለ ? ” የእግዚአብሔርን ተግባር ታበክታለህ ” ተብሎ ተከለከለ ።ሲከለከል የአመፅ ንቅናቄ ነው ዐማርኛን የፈጠረው ። በዚህ መልኩ ነው  ያደገው ። ከሰማይ አልወረደም ። በኋላ ገዢዎች ከዱና ” አማርኛውም  የኛ ነው ” አሉ ። ፊደሉ የግእዝ  ፊደል ነው ። ከሳባዊያን ነው የመጣው ። ሳባዊያኑ ደግሞ የኢትዮጵያ ናቸው ። ” …

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህወሀትን ጣረሞት ተከትሎ ዶላር 65 ብር ገብቷል፣ መቀልበስ ግን አንችላለን

በሀብት ፣ በሥልጣኔ እና በኃይል የገዘፉ ካፒታሊሥት አገራት ሴራን በመግለጥ ኢትዮጵያዊውን አሥጠንቅቋል ። ፀግሽ ።

” …ቋንቋህን ብቻ አይደለም የሚወስዱት ። ባህልህንም አንተነትክንም ፣ መሬትህንም ነው ። ሳውዲ ዐረቢያን ከትናንት በስቲያ ነው የወሰዱት ። እንዲሁም ከሰላን የወሰዱት ትላንት ነው ። ጅቡቲንና ሱማሌን የወሰዱት ትላንት ነበር ። ኤርትራን ዛሬ ወሰዱ ።  ነገ ደግሞ ኢትዮጵያን ይወስዳሉ ። ይህ ሂደት ነው ። እና ኢትዮጵያን ማዳን ማለት መሠረቱን ማወቅ  እውነቱን ማወቅ ማለት ነው ። “እውነትን ታወቃላችሁ እውነትም ነፃ ታወጣችኋለች ። ” ነው የሚለው መፅሐፍ ቅዱስ ። እውነቱን እናውቃለን ። ሁላችንም ኩሽ መሆናችንን እናውቃለን ። በሂደት ውሥጥ  ብዙ ባህሪያትንና ሃይማኖቶችን  ፣ እምነቶችን ፣ባህላቶችን እንደተላበስንም እናውቃለን ።

(  ኢትዮጵያ ታሪክ ወይሥ ተረት ኤርሚያሥ ሁሴን ያሰናኘው ባለ ገፅ 527 መፀሐፍ ። ከገፅ 177 እስከ  180  አንብብ ። )

ከላይ የጠቀስኳቸው የፀግሽ ኳርኳሪ ሃሳቦች ናቸው ። እንድነቃ ፣ እንድንባንን ፣ ራሳችንን ወደ ውሥጥ እንድንመለከት የሚያደርጉን ። ብዙዎቻችን ከየት እንደመጣን አናውቅም ። ወዴት እንደምንሄድም አናውቅም ። ባለማወቅ ጨለማ ውሥጥ ነን ። ከፕሮፊሰር  እሥከ እልም እሥካለው ጀዝባ ፣ እኔ ማን ነኝ ? ከየት ነው ጥንታዊ አፈጣጠሪ ፣ ለምን ያህል ጊዜ በህይወት በዚህ ምድር እቆያለሁ ? በቆይታያሥ ምን እና ምን ሠርቼ ለማለፍ እፈልጋለሁ ?  ሞት እንደሆን የእኔም እጣነው ። የትላንትናዎቹ ቅድመ ዓያቶቼ ዛሬ እንደሌሉ ሁሉ ፣ እኔም ነገ  ለልጅ ፣ ልጅ ልጆቼ ታሪክ ነኝ ። ብሎ አያሥብም ። አንዳንዱ ሰውን ፣ ከሰው አጋዳይ ምሁር በአደባባይ ስለ ዘረኝነት ሲሰብክና ፣ ቆዳውን ሲያዋድድ ሥታዩ እና በአንደበቱ የሚወጣውን በትላትል የተሞላ የጥላቻ ተውከቱን  ሥታሥተውሉ  ሁለተኛ የእርሱ ንግግር ፣ በማንኛውም ሚዲያ መሥማት ትጠላላችሁ ።

የአገሬ ምሁራን ሆይ ፣ ትልቁ ዕውቀት ያለማወቅን ማወቅ መሆኑንን ታውቃላችሁ ። ነገር ግን ዛሬም ለማወቅ ካልተጋችሁ ና ባላችሁ የአካዳሚ እውቀት ከተቸከላችሁ ፣ ያው ያላችሁም ይወሰድባችኋልና ንቁ ። ለማወቅ ዛሬም  አረፈደም።

እናንተ የአገሬ ፖለቲከኞችም በቀይ ፣ በቢጫ ና በአረጓዴ ቀለም ላይ ጦር አትሥበቁ ። የቀለሙ ትርጉም በግልፅ በህገ መንግሥቱ ላይ ተፅፏል ። ኮኮቡም የራሱ ትርጉም አለው ። ባለኮኮቡን ባንዲራ ፣ ወይም ልሙጡን ባንዲራ ያዘ ፣ ያ ሰው ለኢትዮጵያ ያለውን ክብር እንጂ ለዘር እና ለዘውግ መቆሙን አያመለክትም ። ይኽንን ባንዲራ በመያዙ የሚጠላው ካለ ኢትዮጵያን የሚጠላ ብቻ ነው ። ያዘው የአማራን ባንዲራ አይደለም ። ትላንት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እያውለበለቡ ለኢትዮጵያ ክብር ሲሉ በጀግንነት የሞቱት ፣ ይህንን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕወሓት ሪከርድ በመስበር ቄሱን በሽብር ወንጀል ከሰሰች

የሰው ታሪክን በቅጡ ተረዱ ። ሰዎች ከእውቀት ካልራቁ ና የአጠቃላይ ዕወቀት ደሃ ካልሆኑ በሥተቀር ፤ ወይም እሥከምሞት ጊዜ ድረሥ እኔ እና ቤተሰቤ እየተቀማጠልን ፣ ሌላው ዜጋ እየተቸገረ ና በችጋር አለንጋ እየተገረፈ ይኑር ፣ የሚል የሥግብግብነትና የሥሥት መንፈሥ እሥከሌላቸው ጊዜ ድረሥ እንዲሁም ዓለም የኪራይ ቤታቸው መሆኖን ጠንቅቀው እሥከተረዱ ጊዜ ድረሥ ከሁሉም ሰው ጋር በሰላም ኖረው ፣ ለማለፍ እንጂ ፣ በሚያልፍ ቀን ለዘር ማንዘሮቻቸው የሚተርፍ ቂም ና ቁርሾ ትተው አያንቀላፉም ።

እናም በዚህ በዕለት ጥምቀት ፣ ሁላችንም ከእውነተኛው የሰው ልጅ ታሪክ ጋር እንታረቅ ። ያለማወቃችንን ከተገነዘብን ፣ ሁላችንም አንድ እና ያው ነን ። ሰው እንባላለን ። በአንድ የኳስ መመልከቻ እሥቴዲዮም ተቀምጦ የሚታይ በሺ የሚቆጠር ህዝብ ። በጥምቀት አደባባይ  ታቦታቱን አጅቦ  በመውጣት ፣ አሥፓልቱን የሞለው ህዝብ ፤ ሰው ነው ። ቋንቋው ቢለያይም ያውና አንድ ነው ። በተፈጥሮው ካያችሁት አንዱ የሚያደርገውን ሌላው ሰው ሁሉ በተመሳሳይ ያደርጋል ። ባዮሎጂካል ሂደቶቹም ያውና አንድ ናቸው ። ለመኖር የሚያደርገው ዘወትራዊ ክንውንም ምንም ልዩነት የለውም ።  እሥቲ እያንዳንዱን ተመልከቱት ? አንዱ ከአንደኛው በምን ይለያል ? በኑሮ ምቾት በተፈጠረ ፣   በቆዳ ቀለም ፣ እኛ ለእኛ ካወጣነው የቁንጅና መሥፈርት በሥተቀር አንዳችም አንዱ ከሌላው ፈፅሞ አይለይም ።  አንዷ ከሌላይቱም ፈፅማ አትለይም ። እና ሰዎች ሁላችን አንድ ነን ። ወንድምና እህት ነን ። ሴት ልጅም ጌጣችን ነች ። እንዲህ ቢሊዮን እንድንሆን ያደረገችን ። የምድር ታሪክ ሁሉ የሆነው በሴት ነው ። ያለ ሴት መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ታሪክ እውን መሆን እንዳልቻለ ተረዳ ። ኢየሱስም ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ነው የተወለደው ። ድንግል በድንግልና ወለደችው በመጠቅለያም ጠቀለለችው ። 6 . በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ 7 . የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።    ( ሉቃስ 2 ፤ 6_7 )

መለካም በዓል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share