በኢትዮጵያ አገረ ምስረታ ከሁሉም የሚቀድመዉ እና የሚልቀዉ የህዝቦች ህልዉና እና ነፃነት ከምድረ ዓለም በፊት ወይም አብረዉ የተፈጠሩ ፤የነበሩ ናቸዉ ፡፡ ነገር ግን በታሪክ ሂደት በኢትዮጵያ መጥቶ የሄደዉ ሁሉ ለስልጣን እና ጥቅም ሲል ዕዉነትን መካድ ፖለቲካዊ ባህል እና ልማድ አድርጎታል፡፡
በኢትዮጵያ አገራዊ ዳራ እና አዉድ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸዉን እና ያላቸዉን ኢትዮጵያዉያንን ለአለፉት ግማሽ ክ/ዘመን ፶ ዓመት የነበረዉ ማሳደድ ፣ ማግለል እና ለይቶ መግደል (ዘር ፍጂት ) በማንነት እና ኢትዮጵያዊነት ላይ በምንም መለኪያ ሊገመት አይችልም፡፡
በኢትዮጵያዊነት ፣የማንነት እና ነፃነት ላይ የማይጠረቃ የስልጣን አምሮት ለማርካት በህዝብ ንቀት እና ጥላቻ በኢትዮጵያን ሞት እና ዉድቀት ላይ በመረማመድ የሚኖሩ በኢትዮጵያ የአገረ መንግስት ታሪክ ተደርጎ የማያዉቅ ተደጋጋሚ ጥቃት፣ ዉርደት እና ሞት አድርሰዋል ፤ ደርሷል፡፡
ይህ አልበቃ ብሎ ታሪካዊ የኢትዮጵያ የዉስጥ ጠላቶች ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ በኢትዮጵያ ፣ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት በጠላትነት ሲፈርጇቸዉ እና በተቃራኒዉ ት.ህ.ነ.ግ. ከደደቢት ፤ ብአዴን ከበደነበት አንስቶ ለድል እና ለስልጣን ያበቃዉን የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራ ህዝብ ከፍተኛ ክህደት እና ሞት የተሴረበት ግን ጥዋት ገና ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም. ሲሆን “የኢትዮጵያ ህዝብ -ዓማራ አመድ አፋሽ ሆኗል”፡፡
የዓማራ ህዝብ ዉርደት ፣ ጥቃት እና ሞት ኢትዮጵያ ብሄራዊ ዉርደት እና ጥፋት መሆኑን አስቀድመዉ ያወቁት ፤የተደረዱት ኢትዮጵያዉያን በግንባር ቀደም ፕ/ር አስራት ወልደየስ ፣ ዶ/ር መኮንን ቢሻዉ….እና አሁንም ድረስ ተጠቃሽ ዘመን አይረሳሽ ጀግኖች የህልዉና እና የነፃነት ትግል ጀምረዋል ፤አዉረሰዋል ፤አስቀጥለዋል፡፡
ስለዚህም የህልዉና እና የነፃነት ተጋድሎ እንደ እንደ ዕድር አመራር ወይም የፖለቲካ ስልጣን ድምፅ እና አመፅ ሳይሆን የዓላማ ህብረት፣አንድነት እና ፅናት የሚጠይቅ ነዉ ፡፡
ለዚህ ነበር የዓማራ ህዝብ እንደሌሎች ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን አስቀድሞ አበዉ“ አስመሳዮች ሲሰባሰቡ ሰይጣን ራቱን ሊበላ ይታደማል ” እንዲሉ ትህነግ /ኢኃዴግ የሽግግር መንግስት ብሎ የግርግር እና ፉክክር አገር ማክሰም ጅምር የጥፋት ሀ…ሁ…ሲጀመር ዕምቢ ያሉት እነኛ ዕዉነተኛ የህዝብ ልጆች የግል ድሎት ከህዝብ እና አገር ህልዉና እና ነጻነት በታች ናቸዉ በማለት የጥፋት ስምምነት መድረክ ረግጠዉ ወጥተዋል …በዚያም በዕነረሱ መሰል የአገር ባለዉለታወች አስከ ሞት ዋጋ ከፍለዋል፡፡
የሚገርመዉ እናት ኢትዮጵያ ዛሬም ለሞቱላት ሳይሆን ለገደሏት መሆኗ ነዉ ፡፡ ከጥንት አስከ ዛሬዉ ዕለት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ፣ ስም እና ሉዓላዊነት እናት አገር ወይም ሞት ብለዉ ደረታቸዉን ለጦር ፤እግራቸዉን ለጠጠር ፣አንድያ ህይወታቸዉን ለሞት አስይዘዉ አገርን ከጥፋት ፤ህዝብን ከስደት እና ሞት ለመታደግ በትንቀንቅ ላይ ያሉትን በስጋት ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶችን በአለኝታነት መመልከት በአድርባይ ዕኩያን ዘንድ የሚታየዉ የክህደት እሽቅድድም በታሪክም ፤በትዉልድም የማይረሳ የክፋት እና ክህደት ሴራ ጉንጎና ቀጥሏል፡፡
የኢትዮጵያ አንድነትም ሆነ ልዑላዊነት ፤ የኢትዮጵያዉያን ህልዉና እና ነጻነት ለምንጊዜም የተጠበቀዉ እና ጠጠብቆ የሚኖረዉ በዕዉነተኛ የህዝብ ልጆች ተጋድሎ እንጂ በጠላት ፍላጎት እና ምኞት አልነበረም ፤አይደለም፡፡
የረጂሙን ትተን የትናንቱን የሶስት ዓመት የኢትዮጵያን ጦርነት ብናይ ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ በሚባል በጠላት ጥርስ ዉስጥ ከቅርብ እና ከሩቅ ሰትታኘክ ፈጥኖ የደረሰላት ኢትዮጵያዊ ለዚያም በግንባር ቀደም ዓማራ እና አፋር ነበር ፤ነዉ፡፡
የዓማራ ህዝብ አብራክ ክፋይ ወጣት / ህዝባዊ ሠራዊት-ፋኖ፣ ልዩ ኃይል፣ ታጣቂ ራሱን ፣ህዝቡን እና አካባቢዉን ፣ አገሩን ከወራሪ ጥፋት ለመታደግ ህዝብ የድረሱልን ጥሪ አድርጎለት ቀርቶ በአመነበት እና በተሰጠዉ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ግዳጂ ለመቆም ህዝብ የሠጠዉ ኃላፊነት ነበር ፤ነዉ፡፡
የክልሉ መንግስት እና ክቡር ርዕሰ መስተዳደሩ ባቀረቡት የክተት ጥያቄ ህዝቡ እና የህዝብ ልጆች በግናባር በመክተት የህይወት እና አካል መስዋዕት በመክፈል ደም እና አጥንት በመገበር ወገናቸዉን ብቻ ሳይሆን አገራቸዉንም ፤መንግስትንም ታድገዋል ይህንም መካድ የሚፈልግ ካለ ኢትዮጵያዊነት የሚኮሰኩሰዉ በኢትዮጵ ስም በጥገኛ እና አድር ባይ ፖለቲካ የሚመጻደቅ ነዉ ፡፡
የኋላ ዘመናትን በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ላይ በተለይም በዓማራ ህዝብ ማንት ፣ ነጻነት እና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተደረገዉን ክህደት እና ሸፍጥ ትተን ዛሬም በሶስት ዓመት ዉስጥ በግልጽ እና በይፋ የሆኑት ሠባዊ ፣ ህጋዊ እና ተፈጥሯዊ የህልዉና፣ ነጻነት እና መብት ጥቃቶች ፫ ሽ ዘመናት ያህል የሚቆጠር የመከራ ዘመናት ይቆጠራል፡፡
በዚህም የዓማራ ህዝብ በእናት አገር ምድሩ በተፈጥሮ ያገኘዉን ህልዉና እና ነፃነት ከእናት አገር ዳር ድንበር ጋር መሳ ለመሳ ለማስከበር ባልተደራጀ እና ዘመኑን ባልዋጃ በጨበጣ እና ልግጣ (ዱላ) ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ከታጠቁት የዉስጥ ከዳተኞች እና ቅጠረኞች በአልሞት ባይ ተጋዳይ ግብግግብ በመግጠም አገር እና መንግስት እንዲቀጥሉ እና አስትንፋስ እንዲያገኙ ጉልህ ሚና ነበረዉ አለዉ፡፡
ሆኖም የዓማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያን እየሞቱ የራሳቸዉን ፣የወገናቸዉን እና የአገራቸዉን ጥቃት እና ዉርደት ላለማየት በመደራጀት እና በዓላማ ፅናት በሁለንተናዊ መንገድ መታጠቅ እና ዘብ መቆም የድምፅም ሆነ የአመፅ ጉዳይ መሆን የለበትም ፤አልነበረበትም፡፡
የአፋር እና ዓማራ ህዝብ ሲሳደድ፣ ሲነድ፣ ሲዋረድ ፣ሲታረድ…..ማን ነበር የደረሰለት ….ዕኮ እንዴት ነዉ የዓማራ ህዝብ ከራሱ አልፎ ለዓለም መድን ሊሆን የሚችል አንድነት እና ህብረት ለመመስረት የጠላት ድምፀ ዉሳኔ የሚጠይቀዉ፡፡
የዐማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያን የምንለይ ካለን ራሳችንን ስንጠይቅ ኢትዮጵያዊ ብሄራዊነት ቀርቶ የግል ማንነታችን ከአፍንጫን የማይርቅ ለጥቅም እና ከንቱ ዉዳሴ የምንጨነቅ መሆናችንን ባይስማማንም ከጥፋተኝነት አያድነንም እና የህዝብን ጉዳይ ለህዝብ እንተዉ፡፡
የዓማራ ህዝብ ልጆች የዓማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያዉያን መሆናቸዉን በታሪክ እና ጊዜ ጅረት ደጋግመዉ በደም እንደ አለላ በቀላ ቀለም እና በታላቋ ኢትዮጵያ ሜዳ እና ሸንተረር የተፃፈ ገድል እና ድል ያላቸዉ መሆኑን ከ18ኛዉ ክ/ዘመን መባቻ እና በኋላ የነበሩት ወዳጂ እና ጠላት ዕማኞችን መጠይቅ ነዉ ፡፡
ከዓመት በፊት ሳይቀር በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ክህደት ፣ በሰሜት ጦር ላይ ሞት ፣ በዓማራ ክልል ወረራ በታወጀ ዕለት በህይወቱ ህይወት ፣ በደም እና አጥንት የአገር አንድነት ፣ የዓማራን ህዝብ ማንነት እንዲሁም የኢትዮጵያዉያንን ደህነት ያስጠበቁ የጎንደር ፣ የወሎ እና የአፋር ህዝብ ሲሆኑ ይህም ልዩ ኃይል፣ ታጣቂ እና ፋኖ(አማራ ህዝባዊ ኃይል…) እንደነበር እና እንደሆነ ነጋሪ አያስፈልግም፡፡
አገርን እና ህዝብን የታደገን ኃይል እና ህዝብ መካድ እና ማዋረድ ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ጠላትነት ከመሆን በምንም ሊለይ አይችልም፡፡
በዓማራ ህዝብ ላይ ለዘመናት“ ተጨፈን ላሞኝህ ” ሲሉ የነበሩት ዘሬም የሚሉት ፀረ ኢትዮጵያዉያን መሆናቸዉን ተግበራቸዉ ቀርቶ ማንነታቸዉ ይናገራል ህዝብም ያዉቃል፡፡
ትናንት የህዝብ እና የአገር ባለዉለታ የነበረዉን የዓማራ ልዩ ኃይል ሲያብጠለጥሉ የነበሩት ፤ ዛሬ የዓማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን የመከራ ጊዜ ደራሽ የሆነዉን ህዝባዊ ኃይል -ፋኖ- የሚያጠለሹ ኢትዮጵያዊነት ለመገልገል እና ለጠላት ለማገልገል እንጂ ህዝባዊነት እና ኢትዮጵያዊነት እርሾ የማይገኝባቸዉ የ፴ ዓመት የኢትዮጵያ እና ህዝቧ ነቀርሳዎች ነበሩ ፤ናቸዉ፡፡
የዓማራ ሆነ አፋር ህዝብ ሲደራጂ ፣ሲታጠቅ ፣ ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ ሲያዉቅ እንደ ዛር የሚያጮኃቸዉ ተዉ እንበላቸዉ ፡፡
የዓማራ ህዝብም ሆነ የአፋር ህዝብ በደም እና አይንት ያቆያትን ሀገር የመጠበቅ እና የማስለጠቅ ኃላፊነት አለባቸዉ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር፡፡
ለኢትዮጵያ አንድነት እና አገር ደህንነት መናጋት ለዓመታት ሳይታክቱ ሌት ተቀን በትብብር አገር ለማፍረስ የሚሰሩትን ጠላቶች በህዝብ እና አገር ሀብት ሲደራጁ፣ ሲታጠቁ እና ለዓመታት ሰባዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ሲያደርሱ ሲያጠቁ አይቶ እንዳለየ የሚያልፍ በህይወት ዋጋ የተተገኘን ብሄራዊ ድል ማሳነስ ከብሄራዊ ቀጥፈት እና ክህደት አይለይም፡፡
የኢትዮጵያ ህዝቦች እና የዓማራ ህዝብ ለማይቀረዉ ተጋድሎ እና ድል መሰባሰብ፣ መተሳሰብ፣ መዘጋጀት እና በዓላማ አንድነት እና ፅኑነት አገርን ለመታግ ዘብ መቆም ለመኢትዮጵያ ህልዉና እና ነፃነት መኖር መረጋገጥ ዋስትና ነዉ፡፡
እናም ሁላችንም ቢሆንም ባይሆንም ድምፅ እና አመፅ ለወንበር እንጂ ለአገር እና ህዘብ ክብር የሚበጀዉ የህዝብን ዕዉነተኛ የህልዉና እና ነፃነት ተጋድሎ መደገፍ እና ማቀፍ እንጂ ለከንቱ ዉዳሴ ነገረ ክህደት እና ጥፋት ማዉተፍተፍ የማይበጂ በመሆኑ ከታሪክ እና ከትናንት ልንማር ይገባል፡፡
“ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ሠላም፤ ነፃነት እና ህልዉና የሚረጋገጠዉ በተባበረ ክንድ ከሚገኝ ኃይል ብቻ ነዉ ፡፡”
ፋኖ ተሰማራ እንደ ራዛዉ በላይ ፤ እንደ ቸኮቬራ ፤
አፋር ተሰማራ እንደ ዉዱ ጀግና ራስ አሊ ሚራ ፣
ትግላችን ጎምርቶ ፈሬዉን እንድናይ ከነፃነት ትግል ከተጋድሎ መስክ ከተግድሎ አዝመራ ፡፡
ማላጂ
“አንድነት ኃይል ነዉ ”