መነሻና መዳረሻችን የሕዝባችን ክብርና ጥቅም ማስከበር ነው!

ሳንወድ ተገድደን ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ጋር የገባንበት ጦርነት ሁሉን አቀፍ ጦርነት ነው፡፡ ጦርቱ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ወዘተ… ቀውሶችን ማዕከል ነው፡፡ በዚህ ጦርነት በጠላት ጀርባ ታዝለው የገቡ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችና አጋሮቻቸው እጃቸው ረዝሞ ታይቷል፡፡ በዚህም ይህ ጦርነት ከትህነግ አሸባሪ ቡድን ጋር ብቻ እየተደረገ ያለ አለመሆኑም ታውቆ ያደረ ሀቅ ነው፡፡

በህልውና ጦርነት ትህነግ ሳተላይት አሸባሪዎችን ጥቅም ላይ አውሏል፡፡ እነዚህ የጥፋት አጋር የሆኑት ተላላኪዎቹ ማለትም አሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣ የጉሙዝ ታጣቂ፣ የቅማንት ታጣቂ፣ የአገው ሸንጎ ወዘተ… ታጣቂዎች ጋር የጥፋት ሕብረት ፈጥሮ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ስለመውጋቱ በተደጋጋሚ የተገለጸ እውነታ ነው፡፡ ከዚህ አለፍ ሲልም፤ ከግብፅና ሱዳን ጋር በግልፅ፣ እንዲሁም ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን ሀገራት በግልፅና በስውር እየተደረገ ያለ ጦርነት ስለመሆኑ አይደለም እኛ ኢትዮጵያዊያን መላው ዓለምም ቢሆን ግንዛቤ የወሰደበት ሀቅ ነው፡፡

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ የከፈተብን ጦርነት የፈጠረው አደጋ በመላ ኢትዮጵያውያን ላይ ስለመሆኑ አንዳች አጠያያቂ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው ይሄን አውዳሚ ጦርነት በመመከት ዙሪያ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በጋራ የተረባረቡበትና ከሞላ ጎደል በአገራችን ላይ ተደቅኖ የነበረውን የህልውና አደጋ በጋራ ታግለው ለመቀልበስ የቻሉት፡፡ ስለሆነም የተገኘው ድል የሁላችንም ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ የተረጋገጠበት፣ በሂደቱም ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን ያጠናከርንበት፣ በሁሉም ዘርፍ በጋራ ከቆምን የማንወጣው ችግር እንደማይኖር ያስመሰከርንበት፣ በተለይም በዚህ ጦርነት ዲያስፖራው ከመቼውም ጊዜ በተለየ ለሀገሩ ያለውን ቀናዒነት ያረጋገጥንበት ሆኖ ታይቷል፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ ጦርነት ኢትዮጵያዊ አንድነት፤ ታሪክ የማይዘነጋው ድልና ህዝባዊ ተሳትፎ የተንጸባረቀበት ቢሆንም፤ እንደማንኛውም ተግባር በሂደቱ የተስተዋሉ ውስንነቶች ነበሩ፡፡ በመሆኑም መላ ኢትዮጵያዊያን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ስለተጎናፀፉት ድልና በሂደቱም ስለተስተዋሉ ድክመቶች፤ እንዲሁም ስለቀጣዩ የትግል ምዕራፍ ዙሪያ መምከርና የጋራ አቋም መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ክልል የጦርነት ውሎ፣ ሐሙስ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ/ም - ግርማ ካሳ

በዚህም መሰረት ከአመራሩ ጀምሮ ወደ ሕዝቡ የሚደርስ የውይይት መድረኮች በሁሉም የአገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ በወሳኝነት ውይይቶቹ ከከፍተኛው አመራር እስከታችኛው አመራር ድረስ የደረሱና የተጠናቀቁ ሲሆን፤ በቀጣይም በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ መላ ሕዝቡ የሚወርድ ይሆናል፡፡

ለዚህ ውይይት የሚሆን ሰነድ በማዕከል ደረጃ ተዘጋጅቶ የወረደ ሲሆን፤ ክልሎች ደግሞ የቀረበላቸውን ሰነድ መነሻ አድርገው ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ተነስተው የራሳቸውን ክልላዊ የማወያያ ሰነድ አዘጋጅተው ወደ ውይይት ገብተዋል፡፡ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤትም በዚሁ አግባብ ከማዕከል የወረደውን መነሻ የውይይት ጽሁፍ መሰረት አድርጎ፤ የአማራን ህዝብ፣ ክልላዊ መንግሥትን እና መሪ ፓርቲው በዚህ ጦርነት የነበራቸውንና ዛሬም እያሳዩ ያለውን ተሳትፎ፤ በሂደቱ የተስተዋሉ ችግሮችና በቀጣይም ሊከተሏቸው ስለሚገባቸው አቅጣጫዎች በሚገባ ተንትኖ ወደ ውይይት ገብቷል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ወገኖች መስሏቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ ምንጊዜም ቢሆን የአማራን ህዝብ፤ መሪ ድርጅትና መንግሥት በተለያዩ አጀንዳዎች በመጥመድ በሴራ ፖለቲካ አገር በማመስ የጠላት አጋር የመሆን ዓላማ ያላቸው መሆኑ፣ ‹ውይይት እየተካሄደበት ያለውን ሰነድ አዛብተውና ከአውዱ ውጭ ኤዲት አድርገው› በማህበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩና መሪ ድርጅታችንና የክልሉን መንግሥት ሲያብጠለጥሉ እየተመለከትን ነው፡፡

ይሁን እንጂ “ከሐዋሳ የውይይት መድረክ የተገኘ ሰነድ ነው” ተብሎ እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ በተለይም በአማራ ክልል ውይይት እየተካሄደበት ካለው ሰነድ የተለየ ከመሆኑም በላይ፤ አሁን እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ የአማራ ህዝብ በዚህ ጦርነት የከፈለውን ዋጋና የነበረውን አስተዋጽኦ የሚያሳየውን ክፍል ሆን ብሎ ቆርጦ በማስቀረትና ከአውዱና ከይዘቱ ውጪ ‹ኤዲት› በማድረግ እየተሰራጨ ያለ ሰነድ መሆኑን አረጋጠናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሀገር ጥለው መሰደዳቸው በሰበር ዜና ተሰማ !!

ይህ ጉዳይ ጠላቶቻችን ሆን ብለው የአማራን ህዝብ ለማስቆጣትና ክልሉን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ አስበው እየሰሩ ስለመሆኑ በቂ ማሳያ ነው፡፡

በመጨረሻም የአማራ ክልል ሕዝብና መንግሥት እንዲሁም መሪ ድርጅቱ ብልጽግና ከትግራይ ወራሪ ጋር በተካሄደው ጦርነት ከባድ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ሕዝባችን አርበኝነት ውርሱ ስለመሆኑ በተግባር አስመስክሯል፡፡ ይህንን እውነታ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡ ሀገራዊ ሰነዱም ይሄን እውነታ በተገቢው ለታሪክ ይሆን ዘንድ ከትቦታል፡፡ በአንጻሩ በሂደቱ የታዩ ስህተቶችና የወደፊቱ የትግል አቅጣጫዎችም በተለይም በክልላዊ ሰነዱ በተገቢው ተመላከተዋል፡፡ ይሄን እውነታ በእስከዛሬው ውይይት የተሳተፉ

ሁሉም ወገኖች የሚያረጋጡት ሲሆን፤ እስካሁን በውይይቱ ያልተሳተፉ ወገኖችም በቀጣይ በሚኖሩ መድረኮች ስለሚሳተፉ እውነታው በመድረክ ሲቀርብ ያኔ ሀቁን ይረዱታል ብለን እናምናለን፡፡ የዚያን ጊዜ ሁላችንም ጠላቶቻን ምን ያክል እንደማይተኙልን የተሟላ ግንዛቤ ይኖረናል፡፡ ዛሬም ሆነ ነገ ለአማራ የማይተኙ ደመኛ ጠላቶች እንዳሉብን አምነን በጠላት የሴራ አጀንዳዎች እንዳንጠለፍ የወትሮ ዝግጁነት ሊኖረን ይገባል፡፡ በዚህ አጋጣሚ እንደመሪ ድርጅት መነሻና መዳረሻችን የህዝባችን ክብርና ጥቅም ማስከበር ብቻ እንደሆነ ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

መነሻና መዳረሻችን የህዝባችንን ክብርና ጥቅም ማስከበር ነው!

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

ባህር ዳር-ኢትዮጵያ

ጥር 06/2014

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share