May 17, 2007
13 mins read

ለስላሳ ከንፈር ቁጣን ታበርዳለች

በሺዎች የሚቆጠሩ ትዳሮች ውስጥ ባልና ሚስት በቤት ውስጥ የጎሪጥ የመተያየታቸው ነገር ይታያል:: የአብዛኞቹ ትዳር ውስጥ ፍቅር በፍቅረኛነት ዘመን ያለቀ ይመስል አንድ ት ውስጥ አንድ ሶፋ ላይ ተቀምጠው ጀርባና ፊት መሰጣጠት የተለመደ ሆኗል:: ሁለታችሁም ከሥራ ገብታችሁ አንቺ ወደ ጓደኞችሽ ደውለሽ ስልክ የምታወሪ ከሆነ እሱም ጋዜጣ ይዞ ተቀምጦ የሚያነብ ከሆነ ፍቅራችሁ ውስጥ መሰለቻቸት የገባ አይመስላችሁም?

አብሮ ተቻችሎ መኖር እጅግ ከባድ ነገር ቢሆንም ይህንን የሚወጡ ባለትዳሮች ከጀግናም በላይ ጀግና አድርገው ሳይኮሎጂስቶች የሚጠሯቸው ለምን ይመስላችኍል?? የሀገሬ ሰው ”ባል እና ሚስት ከአንድ ባልዲ ይቀዳሉ“” ብሎ የተረተውም ከላይ ያልኩትን ሀሳብ ያወፍርልኛል:: ባልና ሚስት ከአንድ ባልዲ ይቀዳሉ ሲባል ሁለቱን አንድ አይነት ሀሳብ ያስባሉ  ማለት ብቻ ሳይሆን: በአይን ተነጋግረው ይግባባሉ: በአይን ብቻ ፍቅር ይሰራሉ: የሚፋቀሩ ከሆነ ቢጣሉ እንኳን የትም ዞረው ይገናኛሉ የሚሉትንም ያጠቃልላል:: የትዳር አጋሩን  ሀሳብና ፍላጎት የማይረዳ ካለ እርሱ ከትዳር አጋሩ ጋር በአንድ ባልዲ ውስጥ እንዳለ ውሀ አይደለም ማለት ነው::

በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ወይም ሰላማዊ ትዳር ላለመምራት እክል ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች የታወቁ ቢሆኑም ብዙ ጊዜ ልብ ብለን እነዛን ነገሮች ለማስተካከል ስለማንሄድ ችግሩ አፍጦ መጥቶ ጋብቻን እንደ ከርቸሌ (እስር ቤት) የምንቆጥር ብዙ ነን:: ከጭንቀት እና ፍርሀት: ረዥም ሰአት ከመስራት: ከድካም: የሰው ወሬ ከመስማት: ያለሆነ ነገር በአእምሮ ፈጥሮ ከማሰብ የተነሳ የትዳር አጋርን ጣል ጣል የማድረግ ነገር ይመጣል:: “”ረዥም ሰአት የሚሠራ: ፍርሀት እና ጭንቀት ያለበት እንዲሁም የሚደክመው ሰው ችግሩን ቀስ ብሎ ከማስረዳት ይልቅ ቁጣ ቁጣ ይለዋል::“” የሚሉት የስነ ልቦና ባለሙያዎች “”ንግግሩ ሁሉ የፍቅርና ትህትህናን የተሞላ ሳይሆን የንቀትና በጣም የጮኸ ስለሚሆን የትዳር አጋርን ሊበጠብጥና ወደ አልተፈለገ ንትርክ ሊመራ ይችላል::“” ይላሉ:: እነዚህ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ለዚህ እንደመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርቡት ባልና ሚስት ረዥም ሰአት የሚፈጅ ሥራ መስራት እንደሌለባቸው ነው:: ሁለት ሙሉ ሰአት ሥራ የሚሠራ አንድ ወገን ለ16 ሰአታት ከሚስቱ ተለይቶ በሥራ ላይ ተወጥሮ ውሎ በ17ኛው ሰአት እቤቱ ሲገባ አልጋው ነው የሚናፍቀው ወይስ ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ የፍቅር ጨዋታ መጫወት?

አብዛኞቻችን በትዳር ውስጥ ችግሮች እንዴት እንደሚፈጠሩ  በልምድም ልናውቀው ስለምንችል ወደ መፍትሄዎቹ ብናመራ የተሻለ ይሆናል::

ታደምጣታለህ ወይ?

የትዳር አጋርህ ላንተ ልክ እንደ ሴት አያትህ ናት ይላሉ የስነልቦና ባለሙያዎች:: አያቶች ለልጅ ልጆቻቸው እድሜያቸው በገፋ ቁጥር ብዙ ማውራትን እና ብዙ መምከርን ያበዛሉ:: ስላሳለፉት ነገርም በብዛት ያወራሉ:: አያቶች ዝም ብሎ ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጣቸውን እንደሚወዱት ሁሉ የትዳር አጋርህም እንደዚያው ናት:: ምንም ዝምተኛ ሚስት አገባው ብትልም ሚስት ከባሉዋ የምትደብቀው የላትምና ያሳለፈችውን ውሎ ስትነገርህ ማዳመጥ አለብህ:: ወሬው የሚያስጠላ ቢሆን እንኳ በአጽንኦት እየተከታተልክ መሆንን ለማረጋገጥ ”እህ“” “”አሀ“”  “”ከዛስ?” እያልክ በማዳመጥ ልታበረታታት ይገባል:: ከትንሽ ጀምሮ ሚስትህን የምታደምጣት ከሆነ ጸብ ቢፈጠር እንኳ የመደማመጡ ባህልን ስላዳበርክ በአጭሩ እሳትን ማብረድ ትችላለህ::

እርሷ ስትናደድ ምን ታደርጋለህ?

እርሷ ተናዳ በነገር ልትቆሰቁስህ ትችላለች:: ጮክ ብላ እየተናገረች ታቆስልሀለች:: በዚህ ወቅት አንተም እንደ እርሷ እሳት ትሆናለህ? መልስህ አዎ ከሆነ ተሳስተሀል:: አንዲት ሴት ልጅ ጮክ ብላ በንዴት ከተናገረች “”የጎደለኝ አለና ስማኝ“” እያለችህ መሆኑን ማስተዋል አለብህ:: የጎደለባትን ነገር ለማስተካከል መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ አብረሀት ብትጮህ እና ብትለፋልፍ: ቃላት ብትወራወር ትርፉ ራስን ማዋረድ ነው:: ቃላት በተወራወርክ ቁጥር የሚያደማ ቃል ትነጋገሩና ቁርሾ ማሳደር ይሆናል:: ነገርን ከመፍታት ይልቅም የባስ ትልቅ ጦርነት በቤትህ አወጅክ ማለት ነው:: ለዚህ ነው በተለመዶ “”ትዳሩን መምራት ያልቻለ ሰው ለሀላፊነት አይበቃም“” የሚባለው:: ስለዚህ ለማዳመጥ የፈጠንክ ለመልስ የዘገየህ ሁንላት:: ይባስ  ብለህ እንደውም እርሷ በምትበሳጭበትና ጮክ ብላ በምትናገርበት ወቅት ንዴት ውስጥ ብትሆንም ዓይን ዓይኑዋን እና ከንፈር ከንፈሯን ብቻ ተመልከት  ይላሉ የስነ–ልቦና ሊቆች:: እርሷ በንዴት ውስጥ ሆና አንተ ዓይን ዓይኑዋን የምትመለከታት ከሆነ ንዴቷ እየበረደ ከመሄዱም በላይ ያሳለፋችሁትን መልካም ጊዜ በዛች ቅጽበት ውስጥ አስታውሳ እርሷም ታጋሽ ባል አለኝ ብላ እንድትኮራብህ ታደርጋታለህ:: ትንሽ በረድ ካለች በሗላ ደግሞ ከንፈሯ አተኩእርህ በመመልከት ከአንገት በላይ ከእርሷ ጋር አንድ ለመሆን ፍላጎትህን አሳያት:: ለስለስ ያለ የከንፈር ለከንፈር መሳሳም ቁጣን አብርዶ እቤትህ ውስጥ ሰላምን እንደሚፈጥርልህ ሁልጊዜም አስተውል::

ስልክ ባታነሳስ?

አንተ ሥራ ቦታ ነህ እንበል:: እርሷ እቤት ውስጥ ነች ወይም ከቤት ውጭ ወጥታለች:: ባለቤትህ ናፍቃህ ወደ እርሷ ቴሌፎን ስትደውል የስልክ ጥሪ ባትመልስ ምን ታደርጋለህ? እንደ የስነልቦና ሊቆች አጠቋቆም ከ100  አስር የሚያህሉት እንኳ ሚስታቸው ቴሌፎን አለማንሳቷን በጥሩ ጎኑ አይመለከቱትም:: አብዛኛው ወንድ የሚያስብው “”ስልኩን ከሌላ ወንድ ጋር እያወራችበት ነው: ወይኔ በእኔ ላይ ደርባ ይዛብኛለች“” ብሎ ነው ወዲያው የሚያስበው:: ምናልባት በኔት ወርክ ምክንያት እየጠራ እርሷ ጋር ላይሰማ ይችላል: የቴሌፎን ባትሪ አልቆባት ይሆናል: ምን አልባት ስልክ ማውራት የማትችልበት ቦታ ይሆናል: ወይም ሥራ ቦታ ውጥረት ውስጥ ትሆናለች ብሎ የሚያስብ ከስንት አንድ ነው:: አንተም ለአጋርህ ስትደውል ስልክ የማትመልስ ከሆነ ወዲያውኑ በመጥፎ ጎኑ የምትመለከተው ከሆነ አመለካከትህ መልካም ስላለሆነ ለመቀየር ሞክር:: እድሜ ለቴክኖሎጂ “”የድምጽ መልእክት ማስተላለፊያ“” (Voice massage) ተፈጥሮልናልና ይህን ተጠቀምበት:: ስልኩ ጠርቶ የማይነሳ ከሆነ “”የእኔ ፍቅር… (እንደዚህ  ያሉትን ቃላት በጸብም ሆነ በፍቅር ጊዜ አትርሳ) የእኔ ፍቅር ናፍቀሺኝ ደውዬልሽ ነበር:: ሆኖም ስልክ ማናገር በማትችይበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እገምታለው:: ስለዚህ በሗላ እንደዋወላለን::  እወድሻለው“” የሚል አይነት ትህትናንና ፍቅርን የተላበስ መልእክት አስቀምጥላት:: እንደዚህ ያሉት መልእክቶች ሚስትህ አንተ እንደምትጠረጥረው ከሌላ ወንድ ጋር እንኳ ሄዳ ቢሆን ትህትህናን እና አስተዋይነትህን አይታ ራሷን ትሰበስባለች:: “”ባለቤቴ ራሱን ስለሚያምን እኮ ነው እኔን የሚያምነኝ“” ብላ እንድታስብ ታደርጋታለህ::   አለበለዚያ ግን ለምን ስልክ አታነሺም እያልክ የምትጮህ ከሆነ: የስልክ ጥሪ አለመመለሱዋንም በመጥፎ መንገድ የምታየው ከሆነ “”ራሱን የማያምን ሰው ሰውን አያምንም“” የሚለውን ብሒል እውን እንዲሆን ታደርጋለህ::

የፍቅረኛነት ዘመንን የሚያስታውስ ትዝታን ትፈጥራለህ ወይ?

በፍቅረኛንት ዘመንህ ታሳያት የነበረህን የሰጪነት (የለጋስነት) ባህርይ ትዳር ውስጥ የሚከለከል እንዳይመስልህ:: ትዳር እስር ቤት አይደለም:: እንደውም በፍቅረኛንት ዘመን ከነበርክበት ጊዜ በበለጠ አሁን ከአጋርህ ጋር በነጻነት የምትገናኙበት ጊዜ ነውና ይበልጥ ለጋስነትህን ማሳደግ ይኖርብሀል:: ምንም እንኳ በፍልስፍና ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች “”ሴቶች  ፍላጎታቸውን አይደለም ወንድ ራሳቸውም አያውቁትም“” ቢሉም እንደፍላጎቷ ሁንላት:: በመንገድ ላይ ስትሄዱ የልብስ መሸጫ ሱቅ አጠገብ ስታልፉ “”ይህ ልብስ ያምራል“” ብትልህ እንድትገዛላት ፍላጎቷን እያሳየችህ ነው:: ገንዘብ ባይኖርህ እንኳ አብረሀት ልብሱን አድንቅ እንጂ “”አንቺ ደግሞ ሁሉም ያምርሻል“” ብለህ ፍላጎቷን ኩም አታድርገው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop