የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ኢትዮጵያ የራሷን ችግር በራሷና በአፍሪካ ኀብረት ማዕቀፍ ስር መፍታት ትችላለች ሲሉ ድጋፋቸውን አሳይተዋል።በዋነኝነት ድጋፋቸውን ያሳዩ ሀገራት ሩሲያ፤ ቻይናና ሕንድ ናቸው።
የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሀገራት የሆኑት ሩሲያ ቻይናና ሕንድ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ሌላ ማንኛውም ሀገር መግባት እንደሌለበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መዳፈርም እንደማይገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በሀገሪቱ ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት እንደሆነና ለዚህም ደግሞ ብዝሃነት መኖሩ በራሱ ችግር እንደማይሆን አብራርተዋል።
“የኢትዮጵያ መንግሥት እየተፋለመ ያለው በትግራይ ሕዝብ ስም ለዘመናት የሀገርን ሀብት ሲዘርፍና ሰዎች ላይ ብዙ እንግልትና ሞት ሲያደርስ ከኖረው ከሕወሓት የሽብር ቡድን ጋር ነው” ያሉት አምባሳደር ታዬ፤ ለዚህም ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ እንደሆነና ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ኢትዮጵያ ይሄንን ችግር አልፋ ድጋሚ ቀና ብላ እንደምትሄድ አብራርተዋል።
***************
(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከትምህርት ማቆም አድማው በተጨማሪ የረሃብ አድማ ጀመሩ

1 Comment

  1. No way for US peace keeping force in Ethiopia!! The war and peace keeping process is fully under the control of Ethiopian forces & people. Take care America, this is not neo-colonization period!!!!!!!!!! Watch every one & the world communities, like Russia, China, AU countries and others.

    Long live to Ethiopia!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share