እስራኤል የጦር ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያንን እመልሳለሁ አለች

ህዳር 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) እስራኤል የጦር ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንደምትመልስ ቃል መግባቷን ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ አመለከተ።
እስራኤል ይህን ያለችው ወደ አገሯ በስደት ከገቡት ኢትዮጵያውያን መካከል አራቱ የጦር ወንጀል የፈጸሙ በመሆናቸው ኢትዮጵያ ቅር መሰኘቷን መግለጿን ተከትሎ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከእስራኤሉ አቻቸው ናፍታሊ ቤኔት ጋር በስልክ መነጋገራቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ የጦር ወንጀል በመፈጸም መሪ ተዋንያን የሆኑ ወንጀለኞች ወደ ጎረቤት አገራት እንዳይወጡ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በተለያየ አጋጣሚ ወደ ውጭና ወደ ጎረቤት አገራት የወጡ ወንጀለኞች ሲገኙም ከአገራቱ መንግሥታት ጋር በመነጋገር ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።
በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ቀውስ ከተፈጠረ ወዲህ ማይካድራን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የጦር ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖችን ተጠያቂ ለማድረግ መንግሥት በትኩረት እየተንቀሰቃሰ እንደሚገኝ ይታወቃል።
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ፋኖ ልዩ ኦፕሬሽን ፈፀመ | የእነ አበባው ታደሠ አዲስ ኦፕሬሽን | ከባድ ግብግብ በማጀቴ!| የአማራ ድምጽ ዜና

2 Comments

  1. በምንም የሂሳብ ስሌት ትግሬ ቤተ እስራኤል ሊሆን አይችልም። ግን ወያኔ በ 27 ዓመቱ የስልጣን ዘመኑ የትግራይ ተወላጆች አይሁድ ናቸው ብላችሁ መዝግቡ እያሉ ሰዎችን ያስሩ፤ ያስፈራሩ አልፎ ተርፎም ተሳክቶላቸው ጥቂት የሚሆኑ የወያኔ ሰላዪች እስራኤል እንደተሻገሩ መረጃ አለ። ቤተ-እስራኤል የሚባሉ ሰዎች በተወሰነ ስፍራ የሚገኙና ለዘመናት ታሪካቸውን ጠብቀው የኖሩ ወገኖች ናቸው። የሚያሳዝነው ግን ወያኔ የእስራኤልንም የስለላ መረብ ማታለሉ የክፋቱን ጥልቀት ያመላክታል። እነዚህ አሁን በሴራ ከሃገር የወጡት የወያኔ ሰላዪችና ደም አፍሳሾች ለራሳቸው ሰላምን ያጡ ለእስራኤልም ሰላም የማይሰጡ እጃቸው በደም የተነከረ የጠባብ ብሄርተኞች ስብስብ ናቸው። ልክ የእስራኤል መንግስት እነዚህን ሰዎች አጣድፎ እንዳወጣቸው አጣድፎ ትግራይ ላይ ወስዶ ቢጥላቸው መልካም ነው እንላለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share