የትግራይ ፓርቲዎች ና የጁንታው አመራሮች – ናትናኤል አስመላሽ

የጁንታዉ አመራሮች አዲስ አበባ ያለው ካፒታላቸው፣ ሃብታቸው እና ፎቃቸው ለማስመለስ ብቸኛው መንገድ ጦርነት ነው ብለው፣ ወደ ስልጣን ለመምጣት መከላከያን ከጀርባ በመውጋት ጦርነት መክፈታቸው ይታወቃል።

በተምቤን ጫካዎች የነበረ የጁንታ አመራር፣ ትግራይ ሃገር ናት ከማለት ኢትዮጲያ ሃገር ናት ወደ ማለት ተሸጋግረዋል፣ ስለሆነም የትግራይ ዳያስፖራ ትግራይ ሃገር መሆን አለባት የሚለው መፈክሩ ዉሃ በልቶታል፣ ከዚህም አልፎ፣ ለሃገረ ትግራይ ነው የምንታገለው ሲሉን የነበሩ፣ ተለጣፊ ፓርቲዎችም ህልማቸው ቅዠት ሆኖ ቀርተዋል።

ጁንታው አዲስ አበባ መግባቴ ነው ብሎ፣ በትግራይ የነበረውን አንድ ለአምስት ጥርናፌ አጠናክሮ ጨርሰዋል፣ በጦርነቱ ጊዜ ጫካ የገቡ ተለጣፊ ፓርቲዎች ቁማር ተበልተዋል። እንሱን ያላካተተ የፖለቲካ ምደባ ተደርጎ አልቀዋል።

በአለም አቀፍ ህግ መሰረት ትግራይ ሃገር ለመሆን የምትፈቅደው ኢትዮጲያ ብቻ መሆንዋ የገባው ጁንታ፣ አቦይ ስብሓት እንድሉት አይጦች (የትግራይ ተለጣፊ ፓርቲዎች) ማለት ነው ምንም አያመጡም ብለው፣ አዲስ አበባ ያለውን ሃብታቸው በድጋሚ ለመዛቅ ቋምጠዋል።

ህወሓት ታቦት ሊገነባለት ይገባል ያለው [150 ሚልዮን ባለሃብት] ጀነራል ምግበይ፣ በትግራይ ውስጥ ከዚህ ቦሃላ ህውሓት ብቻ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ውሳኔዎች እንደሚያሳልፍ በግልፅ ተናግረዋል። የጀነራል ፃድቃን ቡድን ትናንትና በሚዲያ ቀርቦ፣ ከድል ቦሃላ ህወሓት ብቻውን የመወሰን መብት የለውም ብለዋል።

የትግራይ ተለጣፊ ፓርቲዎች ያልገባቸው ፖለቲካ ግን አለ፣ ጁንታው የሚዋጋው አዲስ አበባ ጥሎት ለመጣው ሃብትና ንብረቱን ነው፣ እናንተ የምትታገሉት በትግራይ ሰላም፣ ዴሞክራሲ ና መልካም አስተዳደር ለማስፈን ነው፣ ይህ በትግራይም በኢትዮጲያም እውን የሚሆነው በህወሓት መቃብር ብቻ ነው። ለአዲሱ የትግራይ ትውልድ፣ ዴሞክራሲ ያልሰጠ ጁንታ ለኢትዮጲያ ና ለኢትዮጲያውያን መብት ና ዴሞክራሲ ይሰጣል ማለት ቅዠት ነው፣ አዲሱ የትግራይ ትውልድ፣ አሮጌውን የትግራይ [የጁንታው] ትውልድ ታግሎ ካልቀበረ ድረስ ለውጥ አይመጣም፣ ጌታቸው ረዳ ና ትርፍራፊ የጁንታ አመራር ህልሙ እንጦጦ መሆኑን ነግሮናል፣ አሁንም ድል ለመከላከያ ሞት ለቀሪው የጁንታ አመራር!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ኦህዴዶች ሐውልት የማቆም መብት የላቸውም፤ ሰዎቹ ምርኮኞች ናቸው" - ዶ/ር ሞጋ ፉሪሳ የኦፌኮ አማካሪ ም/ቤት አባል

1 Comment

  1. እንደ እውነቱ ከሆነ ማንኛውም የትግሬ ሀብት የተዘረፈ ነጥልፍልፍ የማፊያ ኔት ዎርክ ስራ በመሆኑ ከመወረስ ውጭ ተስፋ የለውም ። አጭሩ ጥያቄ ከየት አመጣችሁት ታክስ ከፍላችሁዋል ማለት ነው ለዚህ ጥያቄ መልስ የለም ገንዘቡ ለተዘረፈው ለኢትዮጵያ ህዝብ ገቢ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share