የራሱን የምኞት አገር ታላቋ እና አዲስቷ ትግራይ ለመመስረት ኢትዮጵያዊነትን ክዶ ባዕድነት ወዶ ለመለየት ህዝብን በመግደል እና አገርን በማኮስመን የሚመፃደቅ ነዉረኛ እና ቅጥረኛ ከኃዲ ጠላት እና ተከታይ ሁሉ ወገን ብሎ ዕድሜ ልክ ህዝብን ማታለል እና መደለል የሞኝ ዘፈን ኢትዮጵያዉያን እጂግ ብዙ ዋጋ አስከፍሏል ፤እያስከፈለ ይገኛል ፡፡
አንድም ቀን የትግሬ ነጻ አዉጭ ቡድን ሆነ ህዝቡ በግልፅ እና በቀጥታ የቀረዉ የኢትዮጵያ ክፍል አገሬ ፤ ህዝብም ወገኔ ያለበት ቦታም ሆነ ጊዜ እና አጋጣሚ የለም ፡፡
በትግሬ ህዝብ ነጻ አዉጭ የትግል ዘመን መተዳደሪያ ህግ ዋና ጠላት ኢትዮጵያዊነት/ ዓማራ፣ ፅዮናዉያን እና ምዕራባዉያን ኢምፔራሊስቶች…..ማለቱ እና በጠላትነት መፈረጁ የግማሽ ክ/ዘመን ጊዜ ያስቆጠረ የጥላቻ አሜኬላ ያስገኘዉ የጥፋት ፍሬ ነዉ ፡፡
የዓማራ ኢትዮጵያዊነት ስነልቦና እስካልከሰመ የኢትዮጵያን የግዛት ዳር ድንበር እና ህልዉና በማናጋት ታላቋን እና ጥንታዊት ኢትዮጵያን ማሳነስ እና ማፍረስ ብሎም “ የትግሬ ህዝባዊ / ሪፐፕሊክ መንግስት እና ”ሊቀለስ ዕዉን ሊሆን የሚችለዉ ጠላት በ1968ዎች የተስማማበትን የጥፋት እና ክህደት ቃለ መኃላ ሠነድ መሰረት አድርጎ ብዝኃ ኅዝብ የሆነዉን ኢትዮጵያዊነት /ዓማራ ማክሰም ነበር ፤ ነዉ ፡፡
ከዚህ አኳያ ጠላትን ወዳጂ እና ወገን በማለት ለሞት ድግስ ራስን አሳልፎ ለሰይፍ እንደመስጠት ራስን ማዘናጋት ነዉ ፡፡
የሚያጥላላን እና የሚያሳንስን ወዳጂ ብሎ ራስን መደለል ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ ራስን ማታለል የመከራ ጊዜ ማራዘም ነዉ ፡፡
በዚህ ዓለም ላይ ሳይዱን የምንወዳቸዉ እና የምንከተላቸዉ የሚጎዱንን ያህል የሚጎዳ ምንም ነገር አይጎዳም ፡፡
በኢትዮጵያ የተለመደዉ ክፉ ነገር ዕዉነተኛዉን እና መራሩን ሀቅ በጊዜዉ እና በቦታዉ አለመነጋገር እና አለመመካከር ሆድ እና ጀርባ ከመሆን ባሻገር እዉነተኛ ወዳጂ እና ጠላት በትክክል ለመለየት እና ለማመላከት አለመፈለግ እና አለመቻል በድግምግሞሽ ኅዝብ እና አገርን አይከፍሉት ዋጋ እያስከፈለ ነዉ ፡፡
ዕዉነተኛ ወዳጂ እና ጠላት መለየት ከፈለግን እና ከቻልን ዕዉነተኛ ማንነት እና የዐላማ አንድነት ይኖረናል ይህ በማይሆንበት ግን ማስመሰል እንጅ ማስተዋል ክዶን በዕዉነት ሽፋን በሀሰት አረም እንበላለን፡፡
በልማድ እና በአድር ባይነት እየተነዳን ጠፍተን ከምናጠፋ ስለማናዉቀዉ እንድናዉቅ ፤ ሀሰት ከመናገር ዝምታን በመምረጥ ከትናንት ዕኩይ እና ዕቡይ ታሪካችን ልንማር ይገባል፡፡
ዕዉነትን ባለመናገር የሚኖር የድል ትሩፋት የለም ከዚህ ይልቅ ዕዉነቱን እና ቁርጥ የሆነዉን መሪር ሀቅ መድፈር እና መኖር አለብን ፡፡
ስለ እኛ ማንነት እና ነጻነት የሚነግረን ፣የሚቸረን ሆነ የሚነሳን ከእኛ በላይ ለእኛ ማንም ሊደርስልን አይችልም ኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራን በማክሰም ኢትዮጵያን ማዉደም እና ታላቋን ትግራይን ለመከደም የኢትዮጵያ አስኳል እና ምሰሶ የሆኑትን እና የኢትዮጵያን ጉረሮ ለማነቅ የዓማራ እና አፋር ህልዉናን ማጎሳቆል እና ማሳከር ነዉ ፡፡
ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ህልዉና ህልዎት በወል እና በነፍስ ወከፍ ተገተልትሎ የዓማራን ህልዎት ማሳከር፣ ማደናገር፣ማግለል ፣ ማሳደድ፣ መግደል እና ማስገደል ጅምላ የማክሰም የዘመናት ስዉር ሴራ ኢትዮጵያን ከታሪክ እና ከምድር ገፅ ለማጥፋት የተደረገ እና እየተደረገ ስላለዉ ነጋሪ እና መካሪ አያስፈልግም ፡፡
ዕዉነቱን ከፊት ሆኖ የሚመራ ፣የሚያሰማራ እና የሚያኮራ ታሪክ ሰርቶ ለማለፍ ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊ እና ሠባዊ ፍጡር ሁሉ ዕዉነቱ የዓማራ ማህበረሰብ ህብረት እና አንድነት መሰረት ያደረገ አደረጃጀት መኖር የዘመናት የኢትዮጵያ የኋላ እና መጪ ታሪክ ዕዉተኛ እና መሪ ሀቅ ነዉ ፡፡
ዕዉነትን ለ27 ዓመት እና በላይ በሀሰት እና ዕብሪት የዓማራን ማህበረሰብ መግፋት እና ማጥፋት ዕቅድ ኢትዮጵያን የማጥፋት የመጀመሪያዉም የመጨረሻዉም የክህደት እና የጥፋት ሴራ ሲክዱ እና እየካዱ የነበሩት ዕዉነትን በመናገር ንስሀ የሚገቡበት ዛሬ ነዉ ፡፡
ከዚህ ዉጭ ዕዉነት ላይናገሩ ዝም ይበሉ የከዚህ በፊት ክህደት እና ጥፋት ይበቃል ፡፡ የሀሰት እና አድር ባይ አገልጋይ የጥቅም በሪያወች በህግ እና በመንግስት አሰራር ተጠያቂነት ባይኖርም ስለ ጥፋታቸዉ ፀፀት ሊሰማቸዉ ይገባል ፡፡
አገራችን እና ህዝቧም በመከራ እና ጭንቅ ጊዜ ዕዉነትን ተናጋሪ ፣ያየዉን መስካሪ ፊት ለፊት መሪ እና መካሪ የምንጊዜም የትዉልድ አለኝታ እና መከታ የሚሆን ሠዉ በፅኑ የሚያስፈልጋት እና የምትሻበት ወሳኝ የጊዜ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ፡፡ ለዚህም ሁላችንም በፈፁም ወንድማማችነት እና ህብረት በአንድነት እና በጽናት ተግተን እንቃትታለን ፡፡