‹‹የማይካድራው ጭፍጨፋ በሕወሓት መዋቅር ተፈፅሟል›› ሪፖርት

በማይካድራ አማራዎች ላይ ብሔርን መሰረት አድርጎ የተፈፀመው ጭፍጨፋ ሳምሪ በተሰኘው የሕወሓት ገዳይ የወጣት ቡድን እና በሕወሓት አመራርና ታጣቂዎች መፈፀሙን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥምር የምርመራ ሪፖርት አረጋገጠ፡፡
ጥቅምት 24 ሌሊት በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመክፈት ጦርነት የከፈተው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ከጥቅምት 27 እስከ 30/2013 በማይካድራ የሚኖሩ አማራዎችን በመለየት የዘር ጭፍጨፋ መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጽሕፈት ቤት በጋራ ያደረጉት ምርመራ ሪፖርት አረጋግጧል፡፡
makydraዛሬ ይፋ የሆነው ሪፖርቱ ዘርን መሰረት አድርጎ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ሳምሪ ከተሰኘው ቡድን በተጨማሪ አካባቢውን ያስተዳድር የነበረው የሕወሓት መዋቅር ውስጥ ያሉ የቀበሌ አመራሮችና ታጣቂዎች በቀጥታ ተሳታፊ እንደሆኑ ይፋ አድርጓል፡፡
የሽብር ቡድኑ በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋው ከ1 ሺሕ በላይ ንፁሃንን በግፍ ገድሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን እውነቱ በተደጋጋሚ ሲያሳውቅና ገዳይ ቡድኑም ጭፍጨፋውን ከፈፀመ በኋላ ወደ ሱዳን በመሸሽ በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ መግባቱ ሲገለፅ የነበረ ቢሆንም ለሽብር ቡድኑ ያደሩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ይህን እውነት ደፍረው የዘገቡበት ወቅት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ከዚህ ወንጀል ራሱን ለማንፃትና መንግሥትን ሲኮንን የነበረውን ሕወሓት ሲደግፉና የወንጀሉን ፈፃሚ ሲያድበሰብሱ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
251493073 1669935389848115 503176142948569509 n

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.