የአገር ክህደት፣ አኩሪ ተጋድሎ፣ አንጸባራቂ ድል፣ ጠንካራ አገራዊ አንድነት

ከጥቅምት #24_24
253355492 431266415053421 8212548144488761030 n
የሰሜን ዕዝን ዋና አዛዥን በመርዝ ለመግደል በመሞከርና የሠራዊቱን እንቅስቃሴ እስከማደናቀፍ በተደረገ ሙከራ አሸባሪው ሕወሓት በሀገርና በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ክህደት የመፈጸም ተግባሩን በይፋ ጀመረ። ይህ የክህደቱ መነሻ እንጂ ፍፃሜ አልነበረምና “መብረቃዊ ምት” በሚል ስያሜና ሴራ ጀርባውን በወገን ተማምኖ ፊቱን ወደጠላት አዙሮ የትግራይን ክልልና ህዝብ በመጠበቅ ላይ በነበረውና ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እህሉ ሊበላሽ ሲል ደርሶ በሚታደገው፣ በአንበጣ ወረራ አርሶ አደሩ እንዳይጎዳ ከፍተኛ እገዛ ሲያደርግ በነበረውና ከጥቂት ደመወዙ ቀንሶ ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ሲገነባ በኖረው የሰሜ ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ከህደትና አረመኔያዊmድርጊት ፈጸመ።
እብደታቸው መጠን አልነበረውምና ያሰቡት ሰሜን ዕዝን አጥቅተው በአጭር ቀናት ወደ አዲስ አበባ በመትመም የዝርፊያና ኢፍትሐዊ ድርጊታቸው ዳግም ማስቀጠል ነው።ይሁንና ፍላጎትና አቅማቸው የተጣጣመ አልነበረምና እንኳን አራት ኪሎ ሊደርሱ በጀግናው የመከላከያ ኃይል፣ በአፋርና አማራ ልዩ ኃይሎች እንዲሁም በምልዓተ ህዝቡ አኩሪ ተጋድሎ መቀሌም እንኳ መሸሸግ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጠረ።
(ኤፍ ቢ ሲ)

አርማሽ ይውለብለብ !

 

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.