የአማራ ሕዝብ ብቸኛ አማራጭ – መስፍን አረጋ

ጠላቶች በሁለት ዓይነት ይከፈላሉ፡፡  አንደኛው ሁኔታወችን መሠረት ያደረገ ጠላት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጠላት ነው፡፡

ሁኔታወችን መሠረት ያደረገ ጠላት፣ ሁኔታወቹ በቀሰቀሱት ጦርነት ድል አድርጎ ሁኔታወቹን ቢያስቀይር ጠላትነቱ ወዲያውኑ ያከትማል፡፡  በተጨማሪ ደግሞ ድል ቢያደርግም፣ የድል ተደራጊውን ስሜት ላለመጉዳት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡  ድል አደረኩ ብሎ በድል ተደራጊው ላይ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አያደርግም፡፡  ይልቁንም ደግሞ ከኔ ይቅር በማለት ለድል ተደራጊው ከሚገባው በላይ ይቸርለታል (ቸር ይሆንለታል)፡፡  ለተሸናፊው ቡድን ርህራሄንና ከበሬታን ስለሚያሳይ ጨዋ አሸናፊ (gracious winner) ይባላል፡፡

ለምሳሌ ያህል አጤ ምኒሊክ በጨዋ አሸናፊነታቸው ወደር ያልነበራቸው ታላቅ ንጉስ ነበሩ፡፡  አጤ ምኒሊክ ጨዋ አሸናፊ ባይሆኑ ኖሮ፣  ከኦሮሞ መስፋፋት በኋላ በጉዲፈቻና በሞጋሳ አማካኝነት ኦሮሞነትን እንዲላበስ የተደረገውን እልፍ አእላፍ ሕዝብ ወደ እውነተኛ ማንነቱ በግድም በውድም እንዲመለስ ከማድረግ የሚያግዳቸው ምንም ኃይል አልነበረም፡፡ ወሎን፣ ወለጋን፣ አሩሲን … በቀደምት ስማቸው ማስጠራት ይችሉ ነበር፡፡  በጥቅሉ ለመናገር አጤ ምኒሊክ ጨዋ አሸነፊ ባይሆኑ ኖሮ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሕዳጣኑ ከቦረኔ ውጭ ኦሮሞ ነኝ የሚል ማንም ስለማይኖር፣ የኦሮሞ ቁጥር ሚሊዮን እንኳን ባልሞላ ነበር፡፡  በኦሮምኛ የተሰየመ ቦታ ደግሞ የትም አይኖርም ነበር፡፡

በሌላ በኩል ግን ማንነትን መሠረት ያደረገ ጠላት፣ ጠላትነቱ ዘላለማዊ ነው፡፡  በለስ ቀንቶት የሚጠላውን ቡድን ድል ቢያደርግ፣ በጥላቻው ላይ ንቀት ስለሚጨምርበት ጥላቻው ይበልጥና ይበልጥ መሪር ይሆናል፡፡  የድል ተደራጊውን ቅስም ለመሰባበር የማይፈጽመው እኩይ ተግባር የለም፡፡  ከጥላቸው ምሬት የተነሳ ድል ተደራጊውን እያሰቃየና እያዋረደ ቀስ በቀስ ይገድለዋል እንጅ፣ ባንድ ጥይት አይገላግለውም፡፡  እርካታ የሚሰጠው የጠላቱ መከራ እንጅ የራሱ ተድላ አይደለም፡፡  ጠላቱን እስከጨፈጨፈ፣ እስካሰቃየ፣ እስካስራበ፣ እስካስጠማ፣ እስካሳረዘ ድረስ፣ የሱ መጨፍጨፍ፣ መሰቃየት፣ መራብ፣ መጠማት፣ መታረዝ ቅር አያሰኘውም፡፡  የጠላቱ አንድ ዓይን የሚጠፋ ከሆነ፣ የሱ ሁለት ዓይኖች ድርግም ቢሉ ዴንታ የለውም፡፡  

ተጨማሪ ያንብቡ:  ክፉን ሰውና ክፋተኝነትን እንዴት እናውቃለን? በይሄይስ አእምሮ

ወያኔ አማራን በማንነቱ የሚጠላ የአማራ መሠረታዊ ጠላት ነው፡፡  አማራ ገዝግዞ የጣለውን ደርግን በአማራ ድጋፍ አስወግዶ ስልጣን ሲይዝ፣ ከአማራ ጋር በመከባበር ከመተባበር ይልቅ፣ አማራን አሸነፍኩ እያለ በመታበይ ከኦነጋውያን ጋር የተሞሸረው፣ አማራን የሚጠላው በአቋሙ ሳይሆን በማንነቱ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡  አማራን አሸነፍኩ ካለ ደግሞ ጨዋ አሸናፊነትን ተላብሶ ለጊዜውም ቢሆን ተሸናፊ የሆነውን የአማራን ስሜት ላለመጉዳት ከመጣር ይልቅ፣ ባማራ ሕዝብ ላይ ለመናገር የሚቀፉ ብልግናወችን የፈጸመው ጥላቸው የማንነትና የማንነት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡

ባሁኑ ጦርነት ደግሞ በለስ ቀንቶት አማራን ቢያሸንፍ የአማራን ሕዘብ በሁሉም ረገዶች ቁም ስቅሉን እያሳየ ቀስ በቀስ እንደሚያጠፋው የሃያ ሰባት ዓመታት ታሪኩ በግልጽ ይመሰክርበታል፡፡   ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ እንዳይጠፋ ከፈለገ ያለው ብቸኛ አማራጭ ወያኔን ማጥፋት ነው፡፡

አቶ ዳንኤል ክብረት ወያኔን በሥጋ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም ማጥፋት አለብን ሲል ምንም አልተሳሳተም፡፡  ዳንኤል ክብረትን በጥላቻ ንግግር የሚኮንኑት አሜሪቃኖች፣ ‹‹አንድ ነፍሰጡር ያረገዘችው ልጅ የወደፊቱ ሂትለር መሆኑን ብታውቅ ታስጨንግፈው አታስጨንግፈው?››  (“Kill an unborn baby hitler?”) በሚል መላምታዊ ጥያቄ በትልቁ ጋዜጣቸው በኒዮርክ ታይምስ (New York Times) ላይ ላያሌ ቀናት የጦፈ ክርክር የተከራከሩ ተመጻዳቂወች ናቸው፡፡  አሜሪቃኖችን (በተለይም ደግሞ አንቶኒ ብሊንከንን  (Antony Blinken) የመሳሰሉ አይሁድ አሜሪቃኖችን) የሚያሳስባቸው ጀርመናዊት የፀነሰችው ልጅ ሂትለር ይሆን ወይ የሚለው የገና ለገና ስጋታቸው ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ እየተፋለመ ያለው ግን ሂትለርነታቸውን በግልጽ ካስመሰከሩ የወያኔና የኦነግ መሪወችና እነሱን በጭፍን ከሚከተሉ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ አውሬነትን ከተላበሱ መንጋወቻው ጋር ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በወያኔ እንዳይጠፋ ከፈለገ ወያኔን ማጥፋት አለበት፡፡  ወያኔን ለማጥፋት ደግሞ ቁልፉ እርምጃ ኦነጋዊውን ዐብይ አሕመድን ማስወገድ ነው፡፡  የራሱ የሆነውን ኦነግን በደንብ አድራጅቶ፣ እስካፍንጫው አስታጥቆ፣ በወሳኝ ቦታወች ላይ ያሰማራው ዐብይ አሕመድ፣ አማራን አትደራጅ፣ አትታጠቅ፣ አትዝመት የሚለው፣ የአማራን ሕዝብ ባንድ በኩል በወያኔ በሌላ በኩል በሸኔ እያንገረገበ ፍጻሜውን ለማፋጠን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራን መደራጀት የሚያማቸው የኢትዮጵያን ትንሣኤ የማይሹ ፀረ - ኢትዮጵያ ሃይሎች ናቸው! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

የአማራ ሕዝብ በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ድባቅ ተመትቶ የነበረውን ወያኔን ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያንሰራራ ያደረገውን፣ ቀጥሎ ደግሞ ያማራን ሕዝብ ፍዳ እያስበላ ባጭር ጊዜ ውስጥ ደሴ በር እንዲደርስ ያመቻቸለትን ኦነጋዊውን ዐብይ አህመድን የጦር ጠቅላይ አዛዥ አድርጎ ከወያኔ ጋር ጦርነት መግጠም፣ ውጤቱ የአማራን ሽንፈትና እንደ ሕዝብ መጥፋት ማፋጠን ብቻና ብቻ ነው፡፡

ዐብይ አህመድ የጭቆናን ምንነት በቅጡ ሊረዳ በማይችልበት ለጋ እድሜው “ያማራ ጨቋኞችን” ለመታገል ጫካ ገብቶ የወያኔን ጡት እየጠባ ባማራ ጥላቻ ተመርዞና ተሰቅዞ ያደገ፣ አማራን በማጥፋት አማራዊ ናት የሚላትን ጦቢያን አፈራርሶ በሷ መቃብር ላይ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo empire) ለመመሥረት ቆርጦ የተነሳ፣ በዚያ ላይ ደግሞ በማንነቱ ምክኒያት በሥርሰደድ (chronic) የስነልቦና በሽታ የሚሰቃይ ኦነጋዊ አውሬ ነው፡፡  የዚህ እኩይ ግለሰብ የአማራ ጥላቻ፣ ከወያኔ የአማራ ጥላቻ እጅግ ቢብስ እንጅ አያንስም፡፡  ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ ወይም ደግሞ ከለማበት የተጋባበት እንዲሉ፡፡

ዐብይ አሕመድ ማለት በአማራ ሕዝብ ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እስኪፈጸም ድረስ ሥራየ ብሎ እየጠበቀ፣ በነገታው አዳባባይ ወጥቶ አበባ በመትከል፣ ወይም ደግሞ በፌስቡክና በትዊተር ስለ አበባ ውበት በመደስኮር፣ ወይም ደግሞ ስለ ስንዴ ማሳ በመቀባጠር፣ የአማራን ሞት ከዝንብ ሞት እንደማይቆጥረው በግልጽ የሚያሳይ፣ የአማራን ሕዝብ ክፉኛ እያቆሰለ፣ ማቁሰሉ ብቻ ስለማያረካው በቁስሉ ላይ እንጨት የሚሰድ አረመኔ ነው፡፡  የዚህ አኩይ ግለሰብ የአማራ ጥላቻ እጅግ የመረረ ከመሆኑ የተነሳ፣ አማራ ወያኔን አሸንፎ እሱን ከሚያድነው ይልቅ፣ ወያኔ አማራን አሸንፎ እሱን ቢሰቅለው እንደሚመርጥ ሥራው ሁሉ በግልጽ ይመሰክርበታል፡፡

ስለዚህም የአማራ የህልውናው ጦርነት ዋና ትኩረት መሆን ያለበት የወያኔን ኅልውና ባረጋገጠው በዐብይ አሕመድ ላይ ነው፡፡  የህልውናው መፈክር መሆን ያለበት ደግሞ ሁሉም ነገር ወደ ወሎ ሳይሆን ወደ ሁሉም ነገር ወደ ዐራት ኪሎ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች እና የመንግሥት ሰዎች ራሳቸውን/አቋማቸውን በቅጡ ሊፈትሹ ይገባቸዋል?! (በዘርዓያዕቆብ)

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

7 Comments

  1. “ዲባቶ” ልባል ባዩ መስፍን አረጋ የጻፋቸውን 10 ጽሑፎች ወደ ኋላ ሄጄ አንብቤአለሁ። ርእሶቹ ተለዋወጡ እንጂ መልእክቱ አንድ ነው። ኢትዮጵያን መምራት ያለበት አማራ ብቻ ነው ነው! በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ከሳይንስ ምሑር፣ ከቀድሞ ኢሕአፓ እና ከወሎዬ ይህን መስማት ምን ያህል አስፈሪ ዘመን ላይ እንደ ደረስን ይገልጣል። የህወሓትን እኲይ ሥራ የሚሠሩለት ለኢትዮጵያ ያሰቡ መስለው ነው!

    “ዲባቶው” ለሚያፈልቃቸው አሳቦች መረጃ እንኳ ለማቅረብ አይቸገርም። ጥላቻው ሙያውን አስረስቶት ሰነፍ አድርጎታል።
    ምሳሌ 1/ “አማራ ገዝግዞ የጣለውን ደርግን” ይለናል፤ ይኸ ጨርሶ ተሰምቶ የማይታወቅ አዲስ ታሪክ ነው!
    ምሳሌ 2/ “አጤ ምኒሊክ በጨዋ አሸናፊነታቸው ወደር ያልነበራቸው ታላቅ ንጉስ ነበሩ። አጤ ምኒሊክ ጨዋ አሸናፊ ባይሆኑ ኖሮ፣ ከኦሮሞ መስፋፋት በኋላ በጉዲፈቻና በሞጋሳ አማካኝነት ኦሮሞነትን እንዲላበስ የተደረገውን እልፍ አእላፍ ሕዝብ ወደ እውነተኛ ማንነቱ በግድም በውድም እንዲመለስ ከማድረግ የሚያግዳቸው ምንም ኃይል አልነበረም። ወሎን፣ ወለጋን፣ አሩሲን … በቀደምት ስማቸው ማስጠራት ይችሉ ነበር። በጥቅሉ ለመናገር አጤ ምኒሊክ ጨዋ አሸነፊ ባይሆኑ ኖሮ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሕዳጣኑ ከቦረኔ ውጭ ኦሮሞ ነኝ የሚል ማንም ስለማይኖር፣ የኦሮሞ ቁጥር ሚሊዮን እንኳን ባልሞላ ነበር። በኦሮምኛ የተሰየመ ቦታ ደግሞ የትም አይኖርም ነበር።”

    “ዲባቶ” ይልቅ ሳያስብ አንድ እውነት ነግሮናል፦ “ጠላቶች በሁለት ዓይነት ይከፈላሉ። አንደኛው ሁኔታወችን መሠረት ያደረገ ጠላት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጠላት ነው።” ሁለተኛው ጠላት እርሱ ነው! የጥላቻ ማሲንቆ እንበለው?

  2. Dr. Abiy Ahemed is innocent , genius, who works
    16 hours a day to unite Ethiopia , defeat the Ethiopian
    internal & external enemies , build the economic
    infrastructure guided by God Almighty.

    More than 100 Million People support the
    Abiy Administration and those who oppose him
    are the TPLF bandas.

    Ethiopia will be free & flourish for ever.????????????????????????????????✝️✝️✝️✝️????????????

  3. Kkkk አለም ነኝ ማነኝ ያልከኝ ?መስፍን አረጋ ሀሳብ ሰጠ ሀሳብ የሚመነጨው ከሚይስብ አእምሮ ነው አንተ ግን ለዛ ባለመታደልህ የፊዚክሱን ሊቅ ልትግደራደር ያምርሀል። ክፍያህ በተሳደብከው ልክ በመሆኑና መተዳደሪያህ በመሆኑ ቀጥልበት እስክንድርም ላይ ሂደህ መስክርበት ላንተ ሞራል ቦታ የለውም። በሌላ ስድብ ተጠምደው ይህን ጽሁፍ አላዩትም እንጅ እነ እውነቱ፣አምባው በቀል ይቀላቀሉሀል ስድብን እንደ ስራ ቆጥረህ የምትበላው እንጀራ ምን ይሰራልሀል? ጠብቅልን ተብ
    ለህ ካልሆነ የእሱ ጽሁፍና ያንተ ስድብ አይገናኙም ።

    • ሳታነብ ነው እንዴ አስተያየት የም ት ሰጠው? መስፍን ለጻፈው የተሰጠውን መልስ አስተያይ እንጂ። ስምህ ቢረጋ ነው? ወይስ ባይረጋ?

      • መስፍን ብለህ መጣህ? ማንነትን ለመለወጥ ችግር።የለብህም ነገ ደግሞ ሀጎስ ነኝ ትለናለህ.

  4. ሲባል ሰማሁ። የሳይንሱ ምሁር ያውም የፊዚክስ ሊቅ እና የቀድሞው የኢሕአፓ አባል መስፍን አረጋ። መቸም ጉድህ ብዙ ነው የስይንስ ምሁር ከሆንክ ይህንን የመሰለ የጠባቦች ጥበባ አስተያየት ብልህ ባልጻፍከው ነበር።ሆኖም ግን አታውቀውም ብይ ሳይሆን ለማስታወስ ያህል ውሻ ባለቤቱ ምግብ ሲበላ እግሩን አጣምሮ ቁጢጥ ብሎ የባለቤቱን ወይም የጌታውን እጅ እጅ ይመለከታል ።ባላቤቱም በልቶ ሲጨርስ ፍርፋሪ ይወረውርለታል።ውሻውም ፍርፋሪ ስለአገኘ አላፊ አግዳሚን በጩኸት ከማወክ አልፎ ደጎስ ያለ ፍርፋሪ ካገኘም ልናከስ ይላል።በመሆኑም በTPLF ወንበዴውች የተዘረፈ የእርዳታ ነቀዝ የበላው የስንዴ ዱቄት ፍርፋሪ ስለተወረወረልህ ቅጣንባሩ የጠፈ መሰረተ ቢስ ቦተሊክ ለመጻፍ በመሞከርህ በጩኸት አደነቆርከን። በተጨማሪ በዚህ አስተያየት እንዳነበብኩት የቀድሞ የኢሕአፓ አባል እንደነበርክ ነው። እንደተባለው ከሆነ በኢሕአፓ የትግል ወቅት የተሳተፍክ አይመስልም ምክንያቱም ኢሕአፓ እንድ ወያኔ፤ኦነግ እና ሸኔ ጠባብ ብሄርተኛ አልነበረም።ከሆዳሞች እና ከህዲ ባንዳዎች በስተቀር።በመሆኑም በጽሁፍህ መሠረት በኢሕአፓ ታሪክ ውስጥ የለህበትምና በስሙ ለመንገድ አትሞክር።ያው ከጌታቸው ረዳ ጋር ጽና።እንዲሁም የአማራው ክፍል እየተዋጋ ያለው ከትግራይ ክልል አርሶ አደር ሽፍታ ጋር እንጂ ከፌደራል መንግሥት ጋር አይደለም ታዲያ በዶ/ር አቢይ ላይ ይህ ሁሉ ጥላሸት የሚነፋበት ምኑ ላይ ነው? ወይንስ እንደ መስፍን አርጋ እንድ kkkk ቢረጋ (Birega) እንዲሁም ሌሎች ለወያኔ አጎብዳጆ የቁጭ በሉ ፕሮፓጋንዳ ዲዲት ነፊዎች አማካይነት በወሬ የወሎም ሆነ የጎንደር ነውሪዎች እንደ ድርጪት ወፍ በመበርገግ ቀያቸውን በመልቀቃቸው የዶ/ር አቢይ አስተዳደር የወያኒ ወንበዶዎችን በመውጋቱ ነውን? ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ የሰራቸው እና የሚሰራቸው ታላላቅ ስራዎች ተረስተው ስለ ስንዴ ማሳ፤ አባባ በመትከል ስለ አበባ ውበት አወራ በዚህም ወቀስከው እኒህንም በመሥራቱ ተወቀሰ ።ለመሆኑ አንተ እንደተባለው በሳይንስ ምሁርነትህ እና በፊዚክስ ሊቅነትህ ምን ሰራሁ ብለህ ራስህን ጠይቀሃልን?
    እንዲሁም ለቢረጋ (kkkk Birega) የወፍ ምስክራ ድንቢጥ እንዲሉ መስፍን አረጋን የፊዚክስ ሊቅ ብለህ ነገርከን ይህ ሹመት ነው ወይንስ ሙገሳ? ወይንስ በሊቅነቱ ባበረከተው የምርምር ውጤት? ወይንስ ከእሪ በከንቱ በታተም የወረቀት መረጃ በመመርኮዝ? ወይንስ እንዳንተው በወያኔ ቅጥረኝነት አጋርነቱ? ያው ቢጽ ለቢጽ ስለሆናችሁ ተሞጋገሱ እንጂ በአንድ ብትጨመቁ አንድ ዶ/ር አቢይን አትሆኑም ያ እንደ ቡች ቁጭ ብሎ መጮህ።በነገራችን ላይ ቢረጋ አንተ የማትደርስበት ጎጀብ ከሚባል የስድብ ኮሌጅ በከፍተኛ ማዕረግ ነው የተመረቅሁ ስለሆነም ስራየ ስለሆነ ከእኔ ጋር ብዙም ሰፋጣ አታብዛ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share