የአሜሪካው ሲቢኤሲ ጋዜጠኛዋ ሄርሜላ አረጋዊ አሜሪካንን ትጠይቃለች
ከ400 በላይ የተባባሩት መንግስታት ድርጅት መኪናዎች ለጦርነት ሲውሉ የት ነበራችሁ?
የትግራይ ታጣቂዎች ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በመግባት ሺዎችን ሲገድሉ ምን አላችሁ?
*******************************
መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉደይ ላይ ገብተዋል፤ ከተፈቀደላቸው ዓላማና ተግባር ውጭ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል ያላቸውን 7 በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ግለሰቦችን በ72 ሰአታት ውስጥ የኢትዮጵያን ግዛት ለቀው እንዲወጡ ሲል ትናንት አዟል።
ይህንን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ውሳኔውን ተቃውመው ጽፈዋል። ውሳኔውንም መንግስት እንዲቀለብስ ጠይቀዋል።
መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ፤ ወደ ትግራይ የእርዳታ ምግብ ይዘው ከሄዱ 466 መኪናዎች ውስጥ የተመለሱት 38ቱ ብቻ ናቸው፤ ርዳታ ለማድረስ መኪና ያስፈልገናል ሲል አስታውቆ ነበር። በዚህ ወቅት ግን ዋና ጸሀፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሆኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያሉት ነገር አልነበረም።
በአንጻሩ አሸባሪው ህወሓት ረሀብን እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመበት እንደሆነ፤ መኪናዎችን ያስቀረው ለጦርነቱ ሲል እንደሆነና በፌዴራል መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር አስቦ መሆኑን ለእውነት የቆሙ ሁሉ ተረድተውታል።
ክእነዚህም መካከል የአሜሪካው ሲ ቢ ኤስ ጋዜጠኛ የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሄርሜላ አረጋዊ አንዷ ናት።
ሄርሜላ በወቅቱ አሸባሪው ቡድን ይህንን እየፈጸመ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስትን በትግራይ ህዝብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ለማሳጣት ሆን ብሎ የሚያደርገው መሆኑን አስታውቃ ነበር።
ዛሬም ሄርሜላ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን የትዊተር መልዕክት ተቃውማ መልስ ሰጥታለች።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የመንግስትን ውሳኔ በመቃወም፤ ኢትዮጵያ ውሳኔዋን ትቀይር የሚለውን መልዕክታቸውን የተመለከተችው ሄርሜላ፤ “ሰብአዊነት?” ስትል አጣጥላዋለች።
ከ400 በላይ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ተጉዘው የነበሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መኪኖች ትግራይ ቀርተው ጦርነቱን ይበልጥ ለማቀጣጠል ጥቅም ላይ ሲውሉ ለሁለት ወራት ዝም አላችሁ፤ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በመግባት ሺዎችን ሲገድሉስ ምን አላችሁ ስትል ተችታለች።
ሄርሜላ አያይዛም፤ ይህ አካሄዳቸውም በአፍሪካዊያን ሕይወት ላይ መጫወት ነው ስትል የአንቶኒ ብሊንከንን ሀሳብ ነቅፋለች።\
(ኢ ፕ ድ)