የኢትዮጵያ መንግስት 7 የተመድ ሰራተኞች በ72 ሰአታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ ትእዛዝ አስተላለፈ

243506950 4849119065119931 604808744548481952 n
የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር በተለያዩ ኤጀንሲዎች ውስጥ የሚሰሩ 7 የውጭ አገር ዜጎች በ72 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፉን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የመንግሥታቱ ድርጅት ባልደረቦች በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ህገ ወጥ ሥራ ሲሠሩ የተገኙ መሆናቸውም ነው የተገለፀው።
የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት ሰባት የውጭ አገር ዜጎች
1- የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ UNICEF ሚስ አዴል ኮደር
2- የዩኤን የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ግራንት ሊያቲ
3- የዩኤን የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ተወካይ ሚስ ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ፣
4- የዩኤን የሰላምና ልማት አማካሪ ከውሲ ሳንቼሎቲ
5- የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ባልደረባ ሶኒ ኦኒግ ቡላ
6- የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ምክትል አስተባባሪ ሰኢድ መሀመድ ሀርሲ
7- የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ኃላፊ ሚስ ማርሲ ቪጎዳ ናቸው
EBC

1 Comment

  1. ተመድ የአሜሪካ የስለላ መረብ ተቀጥላ ድርጅት ነው። በእርዳታ ድርጅት ስም ሃገሮችን የሚያራኩቱ እነዚህ ሃይሎች ናቸው። ለምሳሌ የአሜሪካው ዪስ ኤድና የዓለም የምግብ እርዳታ አቅራቢው ድርጅት ሲ አይ ኤ ከሚጠቀምባቸው እልፍ መረቦች ቀዳሚዎቹ ናቸው። ለዜና ፍጆታ ቢሊዪን ዶላር የሚያወጣ እርዳታ አቀረብን ይሉንና የራሳቸው አቅራቢዎች፤ የራሳቸው ገዢዎች፤ የራሳቸው አከፋፋዪች ወዘተ በመዘርጋት ለሚዲያ ከተለፈፈው የእርዳታ አሃዝ 1% እንኳን በቀጥታ ለእርዳታ ፈላጊዎች አይደርስም። ለምሳሌ በሄቲ በደረሰው ያለፈ የመሬት መንቀጥቀጥ የዓለም መንግስታት እርዳታ እንሰጣለን ብለው ቃል ከገቡት 2% እንኳን ለህዝቡ አልደረሰም። ይህ ሴራ ለአፍሪቃዊያን ግልጽ ሊሆንላቸው ይገባል። የሚያስገርመው የዓለም ባንክ (World bank) የዓለም አበዳሪ ድርጅት (IMF) ቀድሞና አሁን ማን እየመሩት እንዳለ ለተገነዘበ የሴራውን ውጥንቅጥነት ይረዳል። ይህ ሁሉ ሴራ የአለምን ጥሬ ሃብት ለመቆጣጠርና ተላላኪ መንግስታትን በየሃገራቱ በስልጣን ለማስቀመጥ የሚደረግ ሩጫ ነው። አሁን ከሱዳን ጋር ፍቅር የጀመሩት አሜሪካኖች ዋናው አላማቸው ሱዳንን ለራሳቸውና ለግብጽ መንግስት ስራ አስፈጻሚ ማድረግ ነው። ግን አሜሪካ የገባችበት የፓለቲካ ሰልፍ ሁሉ ፈጥኖም ባይሆን ቆይቶ የሮም አወዳደቅ እንደሚሆን አይናችን እያየ ነው። ለዚህም ነው ጀሮ ያለው ይስማ የምንለው።
    እነዚህ አሁን ከሃገር እንዲወጡ ተነገራቸው የተባሉት የወያኔ ተላላኪዎች በጎን የክፍያ ክፍያ የሚቀበሉ በእኛው ሃገር ዘንጠው የሚኖሩ ገፋፊና እሳት ለኳሾች ናቸው። ለዚህ ነው የትግራይ ህዝብ ተራበ በማለት የሌላውን ወገን መራብና መራቆት ጭራሽ እንዳላዪ አይተው የሚያልፉት። አላማቸው ወገንን ከወገን ጋር ማላተም ነውና። ከስንዴ ጋር ልዪ ልዪ የራዲዪ መገናኛዎችን፤ መሳሪያ፤ መድሃኒት ሌላም ነገር ለወያኔ ሙታኖች እንደሚያቀርቡ ራሳቸው አምነው ይናገራሉ። ልክ እንደ አሜሪካው የፈጠራ ወሬ አናፋሽ CNN ኑሮአቸው የደራ ወሬአቸው የፈጠራ፤ ስራቸው የተንኮል ነው። የኤርትራውን መሪ እንደ አራዊት የሚስሉትም ለእነርሱ አላጎበድድ ስላለ ነው። ይህ ሴራቸው በዝምባብዌው ሮቨርት ሙጋቤ ላይ ካደረጉት ሴራ ጋር ይገናኛል። ለመሆኑ ሳሞራ ሚሸልን ማን ገደለው? ለምን አፍሪቃዊ እይታና አዲስ ጉልበት ይዘው የተነሱ የምድሪቱ መሪዎች ሳይታሰብ ይሞታሉ? ብዙ ማለት ይቻላል። ግን አሁን ስፍራውም ጊዜውም አይፈቅድም። ህዝባችን ሊነቃ ይገባል። የቆዳችው መፍካት ተንኮላቸውን አይደብቅም። ለእልፍ ዘመን ሲያጫርሱን የኖሩት እነርሱ ናቸው። እንንቃ። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.