ጦርነቱ ባስቸኳይ ይቁም! –  ከ”ሰላም አሁኑኑ ማህበር”

መስከረም 15, 2014   (25th September 2021)

ባአገራችን ኢትዮጲያ በተለይም በሰሜን እንዲሁም በምእራብ፣ በደቡብ ያለው ጦርነት በቶሎ ባስቸኳይ መቆም አለበት። ባልፉት አስር ወራት የኢትዮጲያ ልጆች ደም በከንቱ እየፈሰሰ፣ የወጣቶች እምቡጥ ህይወት እየተቀጠፈ፣ የእናቶች እንባ እየረገፈ ነው። እንኳን በአገራችን ቀርቶ በሌሎች አገራት ይፈፀማል ያላልነውን እጅግ አስከፊ፣ አስነዋሪ፣ አሳፋሪ፣ አሳዛኝ ግፍና ጥፋቶች በእርስ በርስ ጦርነታችን ደርሷል። ከጠፋው ህይወት  የአካል ጉዳት በተጨማሪ በዜጎቻችን ስነ ልቦናን ለረዥም ግዜ የሚሰብር፣ ህይውታቸውን የሚረብሽ ሽብር እየተፈፀመ ነው።

በወንድማማቾች መካከል የሚፈሰው ደም፣ኢ-ሰበአዊ ጥፋት፣ ነውር፣ የንብርት ውድመትና ፣ የፕሮፕጋንዳ ጦርነት ወደ አስፈሪው ጨለማ እየወሰደን የአገራችንን ምሰሶና ማገር እየናደብን ነው። ይህ የእርስ በርስ መጠፋፋት ለማናችንም ሳይጠቅም የደሃውን ፣የምስኪኑን፣ ከፖለቲካውም ከስልጣን ፍትጊያው የሌለበትን ዜጎችን ህይወት እይቀጠፈ፣ እያፈናቀለ፣ ለርሃብ፣ እርዛትና  ሰቀቀን እየጣለ ነው።

በፖለቲከኞቻችን አለመግባባት የተፈጠርው ቀውስ፤ የህዝብ ፀብ እንድሆነ እይተነገርን የሚጠፋው ጥፋት ባስቸኳይ መቆም አለበት። ከዚህ የሚጠቀሙት መሳርያ የሚሸጡልን፣ የጦርነት የእልቂት ዜና እያስራጩ የሚቸረችሩትና ገንዘብ የሚለቅሙት፣ በንፁሃን ሞት የሚነግዱት  የስልጣን ነጋዴዎችን፤እንዲሁም የኛነታችን ሰላም፣ እድገት፣ ጥንካሬን የማይፈልጉ የውጭ ሓይሎችን ነው።

በአሁኑ ግዚያት ጦርነትን ስለማስቆም የሚሰማበት ግዜ ሳይሆን፤ በተፋላሚዎቹ ደጋፊዎች   የሚቀነቀነው ግፋ በለው፣ ቁረጠው፣ ግደለው፣ ማርከው፣ ደምስሰው አጥፋው የሚል የጥፋት ሽለላና መፍክር ነው። ለሞትና  ለጥፋት ገንዝብ የሚዋጣበት፣ ወጣቶች፣ ታዳጊ ልጆች ለሞት የሚሰለጥኑበት፣ ወደ ጦር ሜዳ የሚሄዱበት  ወቅት ነው። የሚፈሰው የራሳችን ወንድም እህቶቻችን ደም ነው። የምትደፈረው  የኛው እህታችን እናታችን ናቸው፤ የሚሞቱት ለጦረነት የሚማገዱት የኛው ልጆች ወንድም እህቶቻችን ናቸው።

የነበረንን ሁሉ አጥፍተን ምን ልንገንባ ነው? አገር ያለሰው እኮ አገር አይደለም::  አገር ማለት ሰው ሲኖርበት ነው። አገርን መውደድ ማለት የአገሩን ሰውን መውደድ ማለት ነው። ጦርነቱ በገፋ ቁጥር ወጣት ሴቶቻችን ባል አልባ፤ ህፃናት ወላጅ አልባ የሚያድርግ ፤ሲያድጉም ከፍተኛ የስነ-ልቦና  ጠባሳና ጉዳት የሚያደርስ ነው።

ይህ ጦርነት አሸናፊ የለውም። በጦርነቱ ተሸናፊዎች ሁላችንም ነን። ሟቾቹ ወንድሞቻችን እህቶቻችን፤የጠፋው የራሳችን ንብርት፣ ትምህርት ቤት፣ የጤና ተቋማት፣ የእምነት ቦታዎች እንዲሁም የኢኮኖሚ መሰርተ-ልማቶቻችን ናቸው።

ከሰማይ እንደ እሳት የወረደው ክፉ መንፍስ በወንድሞቻችን ፖለቲክኞቻችን፣ መሪዎቻችን ልብ ገብቶ ለጦርነት፣ ለጭካኔ፣ ለሞት ፣ለጥፋት ሁላችንንም እየዳረገን ነው። የእምንት አባቶቻችን፣ ያገር ሽማግሌዎቻችን የተማሩ ቀና ሊቃውንቶቻችን ይህን ክፉ መንፍስ አገር ሲያፍርስ፣ ህዝብ ሲያጠፋ፣ አስንዋሪ ድርጊት ሲፈፀም ሊያውግዙ፣ ሊያስቆሙ ሊይስተምሩን  ይገባል።

ጀግንነት ወንድም እህትን የቤት እንሰሳን  መግደል፣ መድፈር ማጥፋት ሳይሆን ጀግንነት ወንድም እህትን ከጥፋት ማዳን፤ ከጦረንት ማውጣት፣ አገርን ባህልን እምነትን ማዳን ነው። ለአገራችንና ለህዝባችን መኖር እንጂ መሞት የለብንም።  ”ላገራችን እንሞታለን” ሳይሆን ”ሰለ አገራችን  ስለ ህዝባችን ስንል እንኖራልን”  ነው ማለት ያለብን። ከሞትነውማ አገር ያለ ሰው ግኡዝ ባዶ መሬት ነው።

በተቃራኒ ጎራ ቆማችሁ የምትገዳደሉ  ወንድም እህቶቻችን እባካችሁ ስለምትወዱት፣ ስለ ቆማችሁልት አላማ፣ ልጅ፣ ሰፈር፣ እምነት፣ ስትሉ ይሄንን ጦርነት አቁመን ችግራችንን ፣ ሃሳባችንን ያለጦርነት በሰላም በጠረጴዛ ዙሪያ እንወያይ። ዛሬ ጊዚያዊ ድል ብናግኝ ነገ ደግሞ ተሸናፊ ነንና ይህን የክፋት ድርጊት አቁመን በሰላም ጉዳዮቻችንን እንወያይ። ጦርነቱ ቢቀጥል ይብልጥ ሞት፣ ጥፋት ርሃብ፣ እርዛት፣ ለቅሶ ዋይታ ለመጪው ትውልድ ቂም በቀል  ማውርስ  ነው።

በየትኛውም ወገን አመራር ላይ ያላችሁ የፖለቲካ ሹሞች፣ የጦር አበጋዞች፣የእምነት መሪዎች፣ ያገር ሽምግሌዎች፣ የሚዲያ ባለሞያዎች፣ ሙሁራኖች ሆይ፤ ይህ ጦርንት ሙሉ ለሙሉ ሳያጠፋን አገራችንን ሳያፈርስ  አሁኑኑ በቶሎ መቆም አለበት። የተዘጋው መንግድ ፣ የመብራት፣ የውሃ፣ ስልክ አገለግሎት መክፍት አለብት። ሰላማዊ የንግድ እንቅስቃሴ በቶሎ መጀመር አለበት። ባንኮች መክፈት አለባቸው።  ይህ የህዝብ አግልግሎት እንጂ የፖለቲክኞች ወይም ጦርኞች አግልግሎት አይደለም። በርሃብ፣ በምግብ እጦት እይተስቃዩ  ያሉ ወገኖቻችንን በቶሎ የምግብ መድሃኒት እርዳት  መድርስ አለበት።

ማእክላዊ መንግስትና ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ሆደ ሰፊ ሆኖ ስለ አገርና ህዝብ ህልውና ሲባል ጦርነቱን ለማቆም ታላቁን ድርሻ መወጣት አለበት። በፖለቲካ አምለካከታቸውም ወይም ተያያዥ ድርጊታቸው የታሰሩ ወገኖችን መልቀቅና  ለውይይት ማብቃት ይጠብቅበታል። ሌሎችም ባላንጣ ጦረኞች ለሰላም  ዝግጁ መሆን አለባችሁ። ሁሉንም ወገን ያሳተፈ ሰላማዊ ውይይት፣መግባባት መድርግ አለበት። አገራችሁን ህዝባችሁን የምትወዱ ወገኖች ሁሉ፤  አገርና ህዝብ ከስልጣናችህ ይበልጣሉና ስልጣናችሁን አጋሩ፤  አካፍሉ፤ ሁሉንም ለሚያስማማ ውሳኔ ተገዢ ሁኑ።

ተፋላሚ ወገኖች ለሰላም ጥሪ እምቢ ካሉ የኢትዮጲያ ህዝብ ጦርነት በቃኝ ማለት አለበት። ለርስ በርስ ጦርነት ለየትኛውም ወገን ወታደር ላለመሆን፣ ገንዝብ፣ስንቅ ላለመስጠት መቁርጥ አለበት። ጦርነቱ ይቁም ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ፣ ፀሎት፣ ፆም ማድርግ ያስፍልጋል።

በመደብኛው መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በማህብራዊ ሚዲያ  የምትሰሩ እንዲሁም ብዙ ተከታይ ያላችሁ ወገኖች፣ ተፅኖ ፈጣሪዎች ስለ አገራችሁና ስለ ህዝቡ ስትሉ የጦርነት ቅስቀሳና አፈቀላጤ ከመሆን ታቀቡ፤ ስለ ስላም አስፍላጊነት ና ጦርነቱ በቶሎ የሚቆምበትን ስራ እንድትሰሩ በእግዚአብሔርና በምትወዱት እንማፀናችኋልን። ስራችሁ የሚምዝግብና ሪክርድ የሚሆን ስልሚሆን ከወደፊት ተጠያቂነት ራሳችሁንም አድኑ። ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይብልጣልና።

የራሳችንን ግጭት ራሳችን እናቁመው። የውጭ ሃይላት ሁሌም የራሳቸው ድብቅ ፍልጎት አለና፤ እኛ ከሰላም ውጪ የተደበቀ ፍላጎት የሌለን ኢትዮጲያንና ወዳጆች ጦርነትን በቃ እንበል። ከእንግዲህ  ልጆቻችን ወደ ት/ቤት፣ ዪንቨርስቲ እንጂ ወደ ጦር ካንፕ  ወይም ጦር ሜዳ መሄድ ያቁሙ።

በመካከልችን ያልውን ልዩነት፣ ያልጦርነት በሰላም ተነጋግርን እንፍታ። አንት ትብስ አንቺ ትብስ ተባብለን፣ ግምሽ መንግድ እየትጓዝን ፣ ሰጥቶ በመቀበል ዳር እንዳርሰው። በዚህ ሃሳብ የምንስማማ ወገኖች ሁሉ እንዲሁም  ትውልደ ኢትዮጲያን ፤ ሙሁራን፣ ዜጎች፣ በሚቅጥሉት ሶስት  ወራት  ከሁሉ  አስቀድመን ጦርነቱን እንዲቆም የምንችለውን ሁሉ እናድርግ። የጦርንቱ አጋፋሪዎቹ ላይ ጫና በማድርግ  ይህን የጥፋት ጦርነት እናስቁም። የእምነት አባቶች፣ያገር ሽማግሌዎች፣ ሙሁራኖች  የሚዲያ ሰዎች ስለ ሰላም፣ስለ መግባባት ስንል እጅ ለእጅ ተያይዘን ወድጥፋት እየሄደች ያለችውን አገራችንን ህዝባችንን  እናድን።

በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ የሆኑ  ብልፅግና ፓርቲ/ ማእክላዊ መንግስት፣ ሕወሃት/የትግራይ ክልል መንግስት፣ የኦርሞ ነፃንት ግንባር/ሰራዊት/ ”ሸኔ” ተብሎ የሚጠራውን ጨምሮ፣ የአማራ ና የአፋር ክልል መንግስታት፣ ሊሎች ጦርኞችን ሁሉ ጨምሮ እንዲሁም የኤርትራ መንግስት ላይ ወንድማዊ ጫና በማድርግ ይህን  እልቂት ቶሎ እናስቁም። ራሳችን ለራሳችን በምናድርገው ይህ መልካም ድርጊት አጋር የውጭ አገር መንግስታት ወይም ድርጅቶች  እርዳት ቢታከልበት መልካም ቢሆንም እነዚህ አገራት ወይም ድርጅቶች  ግን ምን አቅጣጫ መሆን እንዳለበት የምንወስነው ግን ራስችን ብቻ መሆን አለብን።

ይህን ታላቅ ጉዳይ ከዳር ለማድርስ በዚህ ሃሳብ የምንስማማ ወገኖች  ወግንተኝነት ሳይድርብን፣ አላማችን ጦርንቱን ባስቸኳይ ማስቆምና ወንድሞቻችንን በሰላምዊ መንግድ ችግራቸውን እንዲፍቱ ማመቻችት ስለሆነ በዚህ  አላማ የምታምኑና በሙሉ ፍላጎትና  ያልክፍያ፣ በችሎታችሁ በግዜችሁ፣ በገንዝባችሁ አስተዋፆ ለማድርግ የህሊናና የአገር እዳ ያለብን ወግኖች   እየተርዳዳን   “ጦርንቱ ይቁም፤  ሰላም አሁኑኑ” በሚል መሪ ቃል በቅርቡ በሚደርግ የማህበራዊ መድርክ ጥሪ ተስባስብን ይህን ጦርነት የምናስቆምበትን መከርን ወደ ወንድሞቻችን፣ ወደ ጦርንቱ አጋፋሪዎች ቀርበን ለመማፀን ብሎም  ህዝባችን  ጋ ለመድርስ እንችል ዘንድ ጥሪ እናድርጋለንና  በቅርቡ ለሚደርግ ጥሪ ነቅተው ይጠብቁ።

ለዚህ መልካም ተግባር ለመሳተፍ የምትፈልጉ ወገኖች በምን መልክ ልትደግፉ እንድምትችሉ በመግልጽ በዚህ e-mail ይላኩልን።  [email protected]

እግዚአብሔር ይርዳን።

8 Comments

 1. ሽህ ታርዶ ሽህ ተሰዶ አማራን እና ኢትዮጵያን እንዲሁም ኦርቶዶክስን ለማጥፋት 40 ዓመት ሙሉ የሰራን ጭራቅ ከምድረ ገፅ አጥፍተን ጦርነቱን እናቆማለን። በጣም የሚያሳዝነው ግን በሰላም ስም መቀለዱ ነው። ወታደሩ የታረደው በዘር እየተመረጠ መሆኑ ን፡ ልብ ይሏል!!! በማር የተለወሰ መርዝ።

  • በውነቱ መፍትሄ ያልሆነ መፍትሄ ጽፎ አንባቢ ጽሁፍ አንብቦ ስለ ሀገሩ እንዳያውቅ የሚደረግ ደባ ይመስለኛል። ጦርነቱን ለማቆም ፍላጎት ያለው ለሀገር የሚያስብ አመራርና ሹመኛ ያስፈልጋል። በቂ ምክንያት ሳይሰጥበት መከላከያ ሀይሉ መለስ የትግሬ መሬት ይሁን ብሎ ባካለለው ድምበር ድረስ እንዲወጣ ተደርጓል ትግሬም በመንግስት እገዛ የአማራ ፋኖ ያስመለሰውን ጠቅላላ መሬት ይዟል በዚህ ሳያበቃ አገኘሁ ተሻገር ከትግሬ ይልቅ ዋና ጠላቶቹ የአማራ መበደል ያንገበገባቸው አማሮችና እውነተኛው የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው ሰውዬው በስልጣን ለመቆየት ድፍን አማራን ቢያሳርድ ግድ የሚሰጠው አይሆንም።
   ይህንን ካልን ዘንዳ ጦርነቱ ፋይናንስ የሚደረገው በአብይ መንግስት በመሆኑ ትግሬዎች የስንቅና ትጥቅ ችግር የለባቸውም። የተደፈረው የሞተው ንብረቱ የወደመው እንኳን ለቁጥር ለግምትም ይከብዳል።
   እንግዲህ ጦርነቱ ባስቸኳይ ይቁም ማለት ትርጉም አልባ ጽሁፍ ከመሆኑም በላይ ጥቅም ያለው አልመሰለኝም ከዚህ ተያይዞ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጦርነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ አይመስላቸውም ያላቸውን ድልብ ጦር ወደቦታው የስራ ልምድ እንዲያገኝ እንኳን አልላኩትም። ነገሩ ውስብስብ ከመሆኑም በላይ ውስጥ ለውስጥም የሚሰሩ ብዙ ስራዎች አሉ።

 2. ‘ሰላም አሁኑኑ’ አላችሁት ማህበራችሁን?????? እውነት ማህበር ነውን??? ግማሽ የወሎ ገበሬ የተውሰነው ተረሽኖና የተረፈው ተሰዶ- በማን በወያኔ፣ ግማሽ ትግራይ ተበጥብጦና ተፈናቅሎ(የወያኔ አባላት አላልኩም) – በማን በውያኔ ,ሩቡ ጎንደር ታምሶ – በማን በወያኔ ፣ አንድ ስድስተኛው አፋር ተፈናቅሎ በማን በወያኔ- ወዘተረፈ ይህ እንዳለ ሆኖ ነው ሰላም እንዲሆን ሁሉም ባለበት ይቁም የምትሉት ባለጊዜወች???እዚህ ላይ የተረሸኑ ፣የተደፈሩ ፣አስክሬናቸው እንዳይቀበር ተከልክሎ ሆን ተብሎ በጅብ እንዲበላ የተደረጉ ወዘተ የእንሰሳዊና አረመኔያዊ ውሸታም ቀዳዳ ወያኔ ዘግናኝ ስራወች አልተገለጹም፡፡
  ለማንም ግልጽ እንዲሆን ሰላም ይሆን ዘንድ የሚፈለጉ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች አሉ፡፡ ለወዳጅም ለጠላትም ለውጭውም ለውስጡም ለሁሉም በያሉበት፦
  1ኛ)) ወያኔ ከአማራ መሬት ወልቃይትንና ራያን ጨምሮ አንዲት ኢንች ሳይቀር ከአማራ መሬት በሙሉ ወይ ተገርፎ ወይ በቃኝ ብሎ መውጣቱ መረጋገጥ ያለበት የማይሻር የአማራ ህዝብ (የቁማርተኛው ብልጽግና አላልኩም) የሞት ወይንም የሽረት ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡
  2ኛ) በየደረጃው በህይወት ያሉ የወያኔ ከፍተኛ አመራርና በየደረጃው ያሉ አባላቱ የሰሜኑን ጦር በማታ፣ ባልተዘጋጀበትና፣ በዘር ለይቶ ማረድን ጨምሮ በጦርነቱ ውስጥ እንደጥፋት ድርሻቸው እንደዚሁም የ27 አመታት በሰሩት የሌብነት ስራቸው( ባዶ እጃቸውን አዲስ አበባ መጥተው የህዝብ ሀብትንና ገንዘብን ዘርፈው ትልልቅቤት፣ ፋብሪካ፣ ፎቅ፣ ንግድ ወዘተ ይዘዋልና)የዘረፉት ከነወለዱ ተቆጥሮ እንዲመለስ/እንዲወረስ ተደርጎ ጥፋቶቻቸው በፍርድ ታይቶ ውሳኔ ከተሰጠ በኋል ብቻ ነው ሰላም ይሁን የሚለው ሊታሰብ የሚችለው፡፡ ሌላው ጄሌው የወያኔ መንጋ በምህረትም ይሁን በፍርድ ነገሩ ተቋጭቶ ሊያልቅውሳኔ ያገናል፡፡ ስለዚህ ይህንን ሀሳብ የጻፋችሁ ህልመኞች ራሳችሁ ወያኔውች ናችሁ አለበለዚያም የወያኔ ስውር ደጋፊወች ናችሁ፡፡ ለማንኛውም ህልማችሁ ቅዠት ስለሆነ ወያኔ በጦርነቱ ተንበርክኮ ከላይ የተገለጹት ሁለት ጥያቄወች እስካልተመልሱ ድረ ሰላም ይሁን ማለት እናሙኛችሁ ነው ትርጉሙ፡፡

 3. አልገባኝም። ትዕዛዝ ነው ልመና? ልመና ከሆነ ወያኔም ሆነ ሌሎች አጥፊ ሃይሎች ተለምነው እምቢኝ በማለት ነው ዛሬ ላለንበት እብደት የደረስነው። ትዕዛዝ ከሆነ እንደ ልመናው ሰሚ የለም። ባጭሩ የእብዶች ጥርቅም አንድ ለሌላው ድንጋይ በሚያቀብልበት ምድር ላይ “ጦርነቱ ይቁም፤ ሰላም አሁኑኑ” ማለቱ የራሳቸውን የቀን ተቀን ባህሪ ሳይቆጣጠሩ ተፈጥሮን እንቆጣጠራለን በማለት እንዳፋከሩን የቀድሞ የፓለቲካ ሙታኖች ባዶ ልፍለፋ ነው። ከእውነት ጋር የተቀራረበ አማራጭ በማቅረብ ቢሆን ኑሮ ነገሩን ፈትሾ ለማየት ይቀል ነበር። በሜዳ ላይ ጦርነቱ ይቁም ማለት ተስፈኛነት ከመሆኑ የተሻገረ ጠቃሚነት የለውም።
  መስሎን እንጂ ካበድን ቆይተናል። እንደ ነጯ ደ/አፍሪቃ የአፓርታይድ አሰራር በወያኔና በሌሎች ሃይሎች ክልልን ተገን አርጎ በምድሪቱ የከፋፍለህ ግዛው ስርዓት ከተዘረጋ ወዲህ የሰዎች ሰቆቃ ሰማይ እንደደረሰ በእነዚህ አጥፊ ሃይሎች የፈረሱ ቤቶችና የተገደሉ የሰዎች ቁጥር የፈጣሪ ያለህ ያሰኛል። ግን ሰውም ፈጣሪም የጭንቅ ጭኾቶቻችን መስማት አቁመው አሁን ላለንበት የላቀ መገዳደልና እብደት ደርሰናል። እንግዲህ እንስሳት፤ ሰብልና ሰውን ከሚያወድም የወያኔ የተምች ክምችት ጋር ነው ስላም እንፍጠር የምትሉት። ሰላሙን ተቀብሎ እንደገና ሮኬትና ሌላም ነገር ታጥቆ፤ ሱዳንና ግብጽን አሰልፎ ዳግም ውጊያ ቢከፍት የእናንተ የሰላም ጥሪ አቋም ያኔም ጦርነቱ ይቁም ይሆን? ይህ መላቢስነት ነው። በልመና የቆመ ጦርነት የለም። ቢቆምም ተመልሶ ያገረሻል። በዓለም ታሪክ ያየነው እንደዛ ነው።
  ሃይለስላሴ ደስታ የሚባል ሰው “ኦ ሰላም በስምሽ ስንት ግፍ ተሰራ” የሚል መጽሃፍ ጽፎ ድሮ ድንጋይ ዳቦ እያለ ማንበቤ ትዝ ይለኛል። ያኔ ሰው እንደ አሁኑ እንደ እንስሳ በመሰሉ ሳይሰለፍ። ሰው ወንጀለኛን ወድቃ በተነሳቸው ባንዲራ በህግ አምላክ በማለት በሚያስቆምበት ጊዜ። በሰላም ስም እልፍ በደል እንደተሰራ ክምር የታሪክ መጽሃፍት ይናገራሉ። አልፎ ተርፎም አንድ ጋ ስለ ሰላም እየተናገሩ ሌላው ጋ የጦር መሳሪያና አማካሪ እያቀረቡ ብዙዎቹን እንዳጨራረሱ ይታወቃል። ሰላምን ማንም አይጠላም። ግን ሰላምን ለማያውቅ ልቡ ሁልጊዜ ተጠራጣሪና በዘሩና በቋንቋው ተሰላፊ ለሆነ ሃበሻ እንኳን በሃገር ጉዳይ ቀርቶ በቤተሰቡም ሰላም ማስፈን ተስኖታል። ስለ ሰላም መናገርና በሰላም ውስጥ መኖር ይለያያሉ። ግን በሰላም ስም የስንት ሃገሮች ሰላም ደፍርሷል? መርምሮ ማየት ነው።
  አንባቢ እና አንተ የምትለው ሁሌ ስንገዳደል እንኑር ነው እንዴ ይል ይሆናል። አይ እኔ ባልልም የምናረገው ይህኑ ነው። በመሰረቱ ሰላምን የሚጠላ ፍጡር የታመመ ብቻ ነው። በሃገራችን ያለው ሽኩቻና የሰላም ማጣትም ከውጭና ከውስጥ በሚመነጭ የታመመ አስተሳሰብ ነው። ሌላው ሁሉ ለሽፋን የሚሰጥ ሃሳብ ነው።
  ስለሆነም የውጭ ሃይሎች አስታራቂ ሆነው ቀረቡ ወይም እኛው በእኛው እንታረቅ ሰላም በሃበሻው ምድር “እንቁልልሽ” እያለች እያለፈችን ነው። ለዚህ ዋናው ማስረጃ የዘር ፓለቲካው አቀንቃኞች የራሳቸው ዘርና የቋንቋ ተናጋሪዎች መከራ እንጂ የሌላው ሞትና መፈናቀል እንደማይታያቸው በግልጽ እያሳዪን ነው። ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንድትፈርስ እንፈልጋለን ብሎ ለዘመናት በሰነድ የተዘጋጀን አጥፊ ሃይል እንዴት ባለ ሂሳብ ወደ ሰላም ይመጣል ብለን እናስባለን? የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር ነው። የሚሻለው እንደ ናፈቁት ተገንጥለው ከሱዳንና ከግብጽ ጋር ቢኖሩ ነው። ይመቻቸው። በቃኝ!

 4. I read this call for PEACE and call for CESSATION OF THE WAR with great interest.

  The war so far didn’t benefit anyone but caused great misery, death, displacement, man made hunger and inhuman atrocities.

  The politicians and war mongers from both side tried war for 10 months and so far no winner. They didn’t become a flour on air as we were told and they didn’t control Addis in few days as we’re told.

  I see the comments in this page for the above article which dismiss it entirely, they call for further war as solution. These people are not the one suffering or affected by the war as they are in safe place.
  The solution is to stop the war and deal their issue peacefully otherwise the country will perish.

  All parties need to sit around the table and negotiate and form a general consensus to resolve their issue.

 5. ሰላም አሁኑኑ ከማለት ውጭ ምንም የረባ መፍትሔ ማቅረብ አልቻላችሁም። ሰላም የማይፈልግ ህወሓት ብቻ ነው፤ እራሳቸው ደጋግመው በአደባባይ የሚናገሩትን የሰማችሁ አትመስሉም። ከ45 ዓመት ጀምሮ ኢትዮጵያን ማፍረስን ዓላማ አድርጎ የተነሳ ህወሓት ዛሬም እየዛተ ነው። በተጨማሪ ግለሰብ ራሱን ሠውሮ እንደ ድርጅት “ሰላም አሁኑኑ” ማለቱ ሌላ ጥያቄ ያስነሳል። ይኸውም ህወሓት ከገባበት ማጥ ለመውጣት የቀየሠው እቅዱ በካድሬዎቹ አፍ “ሰላም! ሰላም!” ነው፤ ጠብ ጫሪም ሰላም ፈጣሪም እራሱ ነው! ዛሬ ግ ን ስልቱ ተነቅቶበት ሕዝብ አምርሯል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.