“የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው..” ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ

242796110 2097044107113593 9066537167633155136 n
የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
  • አሸባሪዎቹ ህወሓቶች ከጦርነቱ በፊት ከጀርባ ይዘውት የነበረው ዓላማ የእነሱን ጥቅም በኢትዮጵያ ላይ መጫን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ካለ አብሮ ለመስራትና የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት በጉልበት ጠምዝዘው የራሳቸውን ፍላጎት ማሟላት የሚል ነው፤ ይሄ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነበር ዓላማቸው፤
  • ለዚህ ዓላማ መሳካት ደግሞ ወታደር ያስፈልገናል ብለው ልዩ ሀይልን እንደ ሽፋን ተጠቅመው ከ200 ሺህ በላይ ሰው ያለበት ሀይል አደራጅተው ነበር፤
  • የጀመረው ጦርነት ዓላማውም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው፤ እኛ ደግሞ የተከተልነው ስትራቴጂ ኢትዮጵያን ከብተና የማዳን ነው፤ የጦርነቱ ፍትሀዊነት የሚመነጨውም ከዚህ ነው፤
  • የጦርነቱን ዋነኛ ማዕከል መቀሌን አድርገን በፍጥነት በመሄድ ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ መቀሌን መቆጣጠር አለብን ካልሆነ አደጋ ነው ብለን አንድ ሰው እንደ አስር እየተዋጋ በፍጥነት ጨርሰናል፤
  • በሰው ሀይል ማደራጀት እነሱ ይበልጡን ነበር፤ ነገር ግን የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው፤
  • የኢትዮጵያዊነቱ መንፈስ እንደገና ደግሞ ዩኒፎርም ለብሰህ ዩኒፎርም የለበሰህ ጓደኛህ ከኋላህ ሲመታህ የሚፈጥረው መንፈስ አለ ያንን ጉልበት ይዘን ነው የተዋጋነው
  • ከሰራዊት አንጻር ያስቀመጥነውን ግብ አሳክተናል፤ የታገቱብንን አባሎቻችንን አስለቅቀናል፤ የተወሰዱብንን ብረትና ተተኳሽ አስመልሰናል፤ ኢትዮጵያን አድነናል፤
  • ህወሓትን እንደ ድርጅት በትነነዋል፤ የሚደመሰሰውን ደምስሰናል፤ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የነበረውን የድርጅቱን አስኳል በትነን ለሰባትና ስምንት ወራት ዋሻ ውስጥ ከተናል፤ የቀረውን ደምስሰናል፤
  • ኢትዮጵያን ሁሌም የሚወጋት የእኛ የራሳችን ሰው ከውጭ ሃይል ጋር በመሆን ነው፤
  • የውጭ ሃይል ቀጥታ አይመጣም፤ የውስጥ ሰውን እየያዘ ነው እየተዋጋን ያለው፤ ከውጭ የሚመጣው ጠላት በግልጽ ቢመጣማ ኖሮ ምንም ችግር አልነበረም፤
  • ኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ሰው የፈለገውን አስተሳሰብ፣ የትኛውንም እምነት ይከተል፤ የትኛውንም ፖለቲካ ይከተል እኛ አያገባንም፤
  • ኢትዮጵያን ከነኩ ግን ከውጩ ሰው ሳይሆን የምንጀምረው ከራሱ ነው፤ የራሳችንን ቤት ቆሻሻ ካላጸዳን ኢትዮጵያን ማቆም አንችልም፤
  • በአሁኑ ወቅት መከላከያ በስፋት ነው እየተጠናከረ ያለው በትጥቅ፣ በአየር ሃይላችን፣ በእግረኛ ሃይላችን፣ ሊገመት በማይችል አይነት መልኩ ነው እየተዘጋጀን ያለነው፤
  • መከላከያን ማጠናከር ለማንኛው ኢትዮጵያዊ በሩ ክፍትነው፤
  • ማንም ሰው መከላከያን መቀላቀል ይችላል፤ መደገፍ ይችላል፤ ማረም ይችላል ምክንያቱም የራሱ ሀብት ነው፤
  • የውስጥ እና የውጭ ስጋት አለብን፤ የውስጥ ስጋቱ ጊዜ የሚፈጅ አይደለም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚስተካከል ነው፤
  • ለውጩ ስጋት ጠንክረን መዘጋጀት አለብን፤ በዚህ ሁለት አመት መከላከያ ፍጹም ሙሉ ለሙሉ ይቀየራል፤
  • ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ይሄ ጊዜ መለማመጃችን ይሆናል፤
  • እኛ የሚያስፈልገን ዘር አይደለም፤ ሰውነታችን ነው፤ ሰውነታችን ካለ አገር አለ!
(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  "ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ፍኖተ ካርታ መውጣት አለበት" - ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ

1 Comment

  1. የመከላከያ ሰራዊታችን ፍፁም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ማየት እጅግ ደስ ይላል : አረመኔው ህውሀት የማያሸንፈውን ጦርነት ጀምሯል ኢትዮጵያ አሸናፊ ነች :: በርቱ የሀገር ጠባቂዎች

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share