September 7, 2021
1 min read

ኢትዮጵያ ዚምባብዌን ባለቀ ሰአት በተገኘ ፍጹም ቅጣት ምት1 ለ0 አሸነፈች

241451573 4777211605645231 2994308689886421217 n

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ከዚምባብዌ ቡድን ጋር ባሕርዳር ስታዲየም ውስጥ ባደረገው ግጥሚያ 1 ለ0 አሸነፈ። ጨዋታው ያለምንም ግብ ሊጠናቀቅ በተቃረበበት 90ኛ ደቂቃ ላይ የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት አስቻለው ታመነ በግሩም ኹኔታ ከመረብ አሳርፏል።
በዚህም ኢትዮጵያ ከጋና እኩል 3 ነጥብ እና የግብ ክፍያ በመስተካከል ደቡብ አፍሪቃን ትከተላለች። ጋና በሜዳው ባደረገው ግጥሚያ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን 1 ለ0 ያሸነፈ ሲሆን፤ ትናንት በደቡብ አፍሪቃ በተራው 1 ለ0 ተሸንፏል። በመጀመሪያው ጨዋታ ዚምባብዌ ከደቡብ አፍሪቃ ጋር ተጋጥማ ያለምንም ግብ ነበር የተለያየችው። በዚህም ደቡብ አፍሪቃ ምድቡን በ4 ነጥብ እና በ1 የግብ ክፍያ ትመራለች።
ኢትዮጵያና ጋና ይከተላሉ፤ ዚምባብዌ የምድቡ የመጨረሻን ደረጃ ይዛለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ መመራት ከጀመረ ወዲህ ከጠንካራ የአፍሪቃ ቡድኖች ጋር ተጋጥሞ ውጤት በማስጠበቅ እና በማጥበብ መሻሻል ዐሳይቷል።
(ፎቶ፦ ከማኅደራችን)
DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop