“አረመኔውና ጨፍጫፊው ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ ከ100 በላይ ንፁሃንን ጨፍጭፏል” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት።
“የጀግኖቻችንን የተቀናጄ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና እናቶችን በያሉበት መንደርና ሰፈር በመግባት፣ ቀሳውስትን ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብቶ የፍጥኝ በማሰር ከ100 በላይ ንጹሃንን ጨፍጭፏል። የትግራይ ወራሪ ቡድን ቀደም ሲል በሰሜን ወሎ፣ በአፋር ክልል የፈፀመውን አይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በድጋሜ ፈፅሟል። ይህ ሰይጣናዊ ቡድን ከወረራቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ግብዓተ መሬቱ እስካልተፈፀመ ድረስ ሌሎች ጭፍጨፋዎችን እንደሚፈፅም ግልፅ ነው።

241388922 1627821567392831 4726832662839271828 n

በጥላቻ የናወዘውና ጭፈጨፋን የዕለት ተዕልት ተግባሩ ካደረገው የትግራይ ወራሪ አድማስ የነካ በደል፣ ሰቆቃና የግፍ ፅዋ ሕዝባችንን ለመታደገ ፍጥነታችንን ጨምረን ማርሻችንን ቀይረን ከያለበት ግብዓተ መሬረቱን በመፈፀም ሕዝባችን ልንታደግ ይገባል።

ሚዲያዎቻችንም ይሄንን እውነት ዓለም እንዲያውቀውና ከወራሪውና ጨፍጫፊው ጋር በምናደርገው ትግል አብረውን እንዲቆሙና ድርጊቱንም እንዲያወግዙት በፍጥነት መዘገብና ቦታው ድረስ በመሄድም ሁኔታውን ማስረዳት ይገባናል።
በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የትግራይን ወራሪ ቡድን ግብዓተ መሬቱን በማፋጠንና ለሕዝባችን ዳግም ስጋት እንዳይሆን በማድረግ ደማቸውን እንደምንመልስ ጥርጥር የለውም። የትግራይን ወራሪ ኃይል ከየገባበት እየመታን ባለንበት ወቅት የቤተሰብና የወገንን ሀዘን የምንጠግነው በትግራይ ወራሪ ኃይል መቃብር ላይ ይሆናል!!!!
አሚኮ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ማርቲን ሉተር ኪንግና የአሜሪካ የፍፁም ህብረት ራእይ - ገለታው ዘለቀ

1 Comment

  1. ወሬ ማናፈስና በሰው ላይ ሲቃ ማብዛት የዘመናችን የዜና አውታሮች የንዋይ ገቢ መፈለጊያ ብልሃት ሆኗል። በመሰረቱ የዛሬዎቹ የዜና አውታሮችና የድህረ ገጽ በሬ ወለደ የወሬ አዳማቂዎች ከሚሰጡት አርዕስት ጋር የማይገናኝ አይንን ማርኮ ፉርሽ የሆነ የወሬ ታቡር ደላቂዎች ናቸው። ይህም የሚሆነው ውደድኝ፤ ተጫኑኝ ለማባዛትና ፍርፋሪ ሳንቲም ለመልቀም ነው። ስለሆነም ወሬውን ሁሉ በተሰላና በሳለ ህሊና ካላየነው ተታሎ ያታልላል።
    የወያኔ ጭካኔ ገና ከጅምሩ የታወቀ ነው። ከሰው ዘር ያልወጡ የአራዊት ስብስቦች ናቸው። በዚህም የተነሳ የገደሉትን፤ ያፈረሱትን፤ የዘረፉትን ሁሉ በዝርዝር በስም ቀኑና ዓመተ ምህረቱ ተለይቶ እንዲሁም የአይን ምስክሮችን በማሰባሰብ ለታሪክ እንደማኖር በቅንጫቤ ወሬ ጆሯችን ደነቆረ። አንድ ትግራይ ውስጥ ተወልዶ ያደገና አማርኛና ትግርኛ አቀላጥፎ የሚናገር በወያኔ አጠራር የአማራ ክልል ነዋሪ በዳባት በኩል የገባው የወያኔ ጦር ያደረሰውን ቋንቁውን እንደማያውቅ ሆኖ ወራሪው ሃይል ሲነጋገር የሰማውን እንዲህ ይገልጣል። እድሜዬ የገፋ በመሆኑ ከቤት መዋል ከጀመርኩ ቆይቻለሁ። አንዲት ቤትም ታዛም የማትባል ፍርስራሽ ውስጥ ነው የምኖረው። ታዲያ ሳይታሰብ የወያኔ ተዋጊዎች መንደሯን ወረሯት። የሚበልጡት ገና ለጋና ሴቶችም የሚገኙበት ነው። አልፎ አልፎ የመገናኛ መሳሪያ የያዙ ይታያሉ። ምንም ነገር ሳይዙ የሚከተሉም አሉ። ይህ በዚህ እንዳለ ፈረስ፤ አህያ፤ በቅሎም ቢሆን ግደሉ ሲል ሰማሁት። ቀጥሎም ይህ ለእቃ ማጓጓዣና ለሌሎችም ነገር የሚጠቅማቸው ስለሆነ መገደል አለባቸው። ጥሩ ሰንጋ ካያችሁ ተሰባስበን ብለን አርደን እንበላለን አምጡት። በተረፈ ለሰው ምንም ምህረት አታድርጉ በማለት ሲናገር የምሰማውን ማመን አቃተኝ። ግን እንደተባለው ሆነ በማለት እሪታ በተሞላበት መንገድ ከአንድ ቤተሰብ ስለተገደሉትና የካህኑ ሞት አንገብግቦት እንደ ህጻን በማለቀስ ጫወታው ተዘጋ።
    ወያኔ ጥፍር ሲያወልቅ፤ ሲያፍን፤ ሶዶማዊ ተግባር በወንድና በሴት ላይ ሲፈጽም የነበረና ያለ ድርጅት ነው። በታሰሩ ወንዶች ላይ ሽንቷን ስትሸና የነበረችውን የወያኔ ሴት አረመኔ ያውቁ ኖሯል። በቆለጥ ላይ ውሃ የሞላ በማንጠልጠል ያኮላሿቸው፤ እንዳይወልድ ክትባት ተብሎ የማምከኛ መድሃኒት የተወጉ ስንቶች እንደሆኑ ያውቃሉ? ታዲያ ወደ 50 ዓመት የተጠጋው የወያኔ ገመናን የሚረዳ ዛሬ በአፋርና በአማራ እንዲሁም በትግራይ ህዝብ ላይ የሚፈጽመው በደል አዲስ ሊሆንበት አይገባም። ለእኔ የሚገርመኝ አሁንም የሰላም ጥሪ የሚያሰሙ የውጭና የውስጥ ሃይሎች ናቸው። የምን ሰላም? ከማን ጋር ነው ሰላም የሚደረገው? በመቀሌ የእናቶች እንባ፤ የሰላም ሚኒስትሯ እንባ መቼ የደ/ጽዪንና የመሰሎቹን ልብ ይህ ሁሉ ውድመት ከመሆኑ በፊት አራራ። ወያኔ ልቡ ከድንጋይ የተሰራ ለመሆኑ የራሱን ወገኖች ከብልጽግና ጋር አበራቹሃል በማለት ማረድ ብቻ በቂ ነው። ብልጽግና ምንድን ነው። ዛሬ ታይቶ የሚጠፋ ሃላፊ የፓለቲካ ንፋስ። እንዴት ነው ሰው እኔን ካልመሰልክ በማለት የምናርደው? ይህን ድርጅት ነው የትግራይ ልጆች ከሩቅም ከቅርብም ሆነው የሚደግፉት። የሚያሳዝን፤ የሚያስለቅስ፤ ለሰው ልጆች መብት ገና ከጥንስሱ ጀምሮ ያልቆመ በትግራይ ህዝብ የሚነግድ የእብዶች ስብስብ።
    በማይካድራና በሌሎች ቦታዎች ሰዎችን እየጎተቱ የጨፈጨፉት የሳምሪ የሱዳንና የተመድ ተጠዋሪ ስደተኛ መሆናቸው ቀርቶ ወያኔ አስቀድሞ በዘረጋው ወጥመድ አሁን ከሱዳንና ከግብጽ ጋር አብሮ በዚህም በዚያም ለውጊያ እያስገባ እያስጨረሳቸው እንደሆነ እንሰማለን። አዎን የሰው ደም በከንቱ ያፈሰሰ ደሙ ይፈሳል። ገና ብዙ መተላለቅ ይጠብቀናል። በአማራ ተወረርን፤ ሻቢያ መጣብህ እየተባለ ልጅንና ንብረቱን በሃሰት የሚገብረው የትግራይ ህዝብ መቼ ይሆን የወያኔን ደባ ለይቶ የዘርና የቋንቋ ፓለቲካውን አክ እንትፍ ብሎ ከቀሪው ወገኑ ጋር በመሆን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔ ከትግራይ ህዝብ ጀርባ ላይ የሚያወርደው? የተባበሩት መንግስታት በሱዳን ያለው የስደተኞች ቁጥር ቀንሷል ወዴት እንደ ሄድ ግን አላውቅም የሚለው ውስልትና ነው። አሁን ከሱዳን ጋር የሞቀ ፍቅር የጀመረው የአሜሪካ የስለላ መረብ በየስፍራው ተበትኖ ሁሉን ያያል። ተመድም የዚሁ የስለላ መረብ ተቀጥላ ነው። ግን ነጩ አለም ጥቁር ለጥቁር ቢላተም ችግር የለባቸውም። ለዚያ ነው ሁሌ በሸፍጥና በሴራ የሚያጋድሉን። እኛም አረብና ነጭ የሚለንን ሰምተን ሃገር ለማፍረስ ሃተፍ ተፍ የምንለው።
    ስለሆነም አረመኔውና ጨፍጫፊው ወያኔ ከማለት ወያኔ የሰራቸውን በፎቶ፤ በቪዲዪ፤ በሌሎችም መንገዶች ከላይ እንዳልኩት የስፍራውን ስም፤ ቀንኑ፤ የጠፋውን ንበረትና የሰው ስም በዝርዝር መያዝ አስፈላጊ ነው። አንድ ዘመዶቹ ተገድለው የተቀበሩበት ሰው ቦታው ደርሶ እዚህ ነው የቀበርናቸው ሲሉት ቆፍሬ ማየት አለብኝ ይላል። ተራፊው የመንደር ሰውም አብዷል ይታሰር ይሉታል። ይህ መሆን የለበትም። አፍንጫና አፍን ሸፍኖ የቆየ አስከሬንም ቢሆን ወጥቶ መታየቱ፤ ፎቶ መነሳቱ፤ ተገቢ እንጂ እብደት አይደለም። እኔ የሚገርመኝ የጋዜጠኞቹ ዘገባ ነው እልፍ ሰው ባለቀበር መንደር ቆመው (አንዳንድ እማ መቃብር ላይም ተቀምጦ) የሚያስተላልፉት ዜና ከፊታቸውና ከስብዕናቸው ጋር አብሮ አይሄድም። ሃዘን ጭራሽ አይታይባቸውም። ይልቁንም የኳሽ ጫወታ ወሬ የሚያስተላልፉ ነው የሚመስሉት። ሞትና መከራውን የተላመድት ይመስላሉ። ይህን ይሆን የስነ ልቦናና የአ ዕምሮ ጠበብቶች Desensitization አላውቅም። ግን ሰው ሰው መሆኑ የቀረ ይመስላል። የሚሰማ ካለ ክራራይሶ ያሰኛል። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.