ለዉጥ ሂደት እንጅ ዉጤት አይሆንም – ማላጂ

ethiopia’s prosperity party
ethiopia’s prosperity party

በአገራችን በተለያዩ ጊዜያት ለዚያዉም የሰነበተዉን ትተን የዘንድሮዉን ብንጠቅስ ጥቅምት ፳፬ ቀን ፪ ሽ ፲፫ ዓ.ም. የኢትዮጵያን የአንድነት ካብ ለማፍረስ እና የታላቋን ትግራይ ግዛት ለመቀለስ  ከፍተኛ ዝግጂት በማድረግ አጎራባች የኢትዮጵያ ግዛት ክፍሎችን ( ጎንደር እና ወሎ ) ብትግራይ ተስፋፊ ፣  ወራሪ እና ዕብሪተኛ ስብስብ በኃይል ወረራ መፈፀሙን የምናስታዉሰዉ ነዉ ፡፡

ሆኖም በከፍተኛ የህይወት እና የሀብት ዋጋ በጊዜዉ የታሰበዉን እና የተቃጣዉን አገር የማጥፋት ክህደት ለዓመታት ከነበረ ሴራ አኳያ በተግባር ሊደርስ ከሚችለዉ አኳያ ለመግታት ተችሏል፡፡

ያም በቁርጥ ቀን ልጆች በተደረገ ከፍተኛ መስዋዕትነት የተገኘ ድል ነዉ፤ ነበር   ፡፡ ምስጋና እና ዘላለማዊ ክብር ለዕዉነተኛ የቁርጥ ቀን የህዝብ ልጆች፡፡

ሆኖም በዚያ በመጨረሻዉ መጀመሪያ ዙር ዓማራን መሳነስ፤ ኢትዮጵያን ማፍረስ የአጥፊ እና ተስፋፊ ጊዜያዊ የድል ጊዜ ጀምሮ የነበረዉ ጮቤ መርገጥ የጦርነቱን መጀመሪያ እንዲሁም  የማሳረጊያ እርምጃ መነሻ እንጂ ምንም እንዳልነበር በታህሳስ ወር በተረዳሁት ልክ በጊዘያዊ ድል መዘናጋት እንደማይገባ ለማስገንዘብ ሞክሬአለሁ ይህም በጊዜዉ በመፅሄት ወጥቷል፡፡

ሁላችንም መረዳት ያለብን እኛ አገር የሚባለዉ እና የሆነዉ ነገር አራባ እና ቆቦ የመሆኑን ጉዳይ ከተለያዩ የአገራችን ሁነቶች ተሞክሮ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በተለያ መንገድ በተለያዩ ሠወች ያልተጨበጠ መረጃ መደናገር ለዳግም መከራ እና በደል መከሰት መንስዔ መሆኑን አሁን ላይ ከምንገኝበት ፪ኛ  የት.ህ.ነ.ግ. የዕብሪት፣ ጥፋት እና መስፋፋት እያጨድን ያለንዉ መከራ ነዉ ፡፡

ለአሁን መነሻየ በሰሞኑ  በተለያዩ የሰሜን ምዕራብ አገራችን ከጥፋት የእሳት ዕራት  መልዕክተኞች አጥፍቶ ጠፊዎች የተላቀቁ ቦታዎች ላይ የደስታ መግለጫ የመሳሪያ ድምፅ/ተኩስ ይሰማል የሚል መረጃ መስማታችን ነዉ ፡፡

ርግጥ ነዉ ባህል ከተባለ በሰርግ፣ በሞት፣ በክርስትና……..ባጭሩ በደስታ እና ሀዘን ምልክት/ መግለጫ  መሳሪያ እንደሚተኮስ እናዉቃለን …..በየቤታችን አድገንበታል፡፡ ቁም ነገሩ ባህል ማለት  ለበጎ  ዕድገት ወይስ ለጥፋት ነዉ ከሚለዉ መነሳት አለብን ፡፡

የሠዉ ልጅ የሚሸነፈዉ እና የሚንኮታኮተዉ በጦር ሜዳ ጦርነት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የድህነት፣ የስነ ልቦና እና የማህበራዊ ቀዉስ ሴራ ዉስጥ በማጥመድ እና በማዉደም ነዉ ፡፡

ለዚህም በቤት እንስሳት እና በተዘራ ቡቃያ ሳይቀር እንደ ዶሮዋ ላልበላ ዕሬ ላጥፈዉ  በደሙ የጥፋት እና ምቀኝነት አባዜ ት.ህ.ነ.ግ. ትናንት በመላዉ አገሪቷ ዛሬ በዓማራ ህዝብ ላይ ሠዉን ብቻ ሳይሆን ከቤት  እንስሳት ፣ ከአዝርዕት…..አልፎ ዓባይን ፣ጣናን፣ተከዜን……ለማድረቅ  በርትቶ እየሰራ ነዉ…..እናም ጦርነት ማለት ሁለንተናዊ የተቃራኒ ኃይል ህልዉና ማዛባት እና ማጥፋት ነዉ ፡፡

እናም እንዲህ ከሆነ እኛ ሳር ቅጠሉ እየተቃጠለ ፣ ሠዉ ከቤት ፣ንብሩ  እየተሰደደ  መጠለያ ዛፍ እስኪያጣ  ከሞት የተረፈዉ ሚላስ ሚቀመስ እያጣ፤ ወጣቱ  እራሱን እና አካባቢዉን ብሎም አገሩን ከጥፋት ለመታደግ  ባዶ እጁን በጨበጣ  ታንክ እና ከባድ የነፍስ ወከፍ እና የወል የጦር መሳሪያ አስካፍንጫ ከታጠቀዉ ቡድን ጋር ጎረሮ ለጉረሮ እየተናነቀ መሆኑን ከሁላችን በላይ  የዓማራ ህዝብ እና እየደረሰበት ያለዉ የሚመስክረዉ ነዉ ፡፡

እናም ሁላችንም ለዘላቂ እና አስተማማኝ ድል መድረስ የምንፈል አስከሆን አንድ ጫማ / ስንዝር መሬት ከጠላት ይዞታ በተለቀቀ ቁጥር የጥይት ድምፅ ማሰማት ጠላትን ከመደገፍ እና የድል ጉዞዉን ከማናቀፍ  ማይለይ በመሆኑ ሁሉም የዓማራ ክልል ህዝብ ፣ የነጻነት ታጋዮች፣ ልዩ ልዩ የመንግስት የፀጥታ እና የህዝብ ዘቦች/ አለኝታዎች የመሳሪያ ተኩስ / ድምፅ ለደስታ መግለጫ መጠቀም አስቀድሞ መዉደቅ እንደሆነ ለሚመለከተዉ ሁሉ ሊያስተምሩ  ይገባል፡፡

የመሳሪያ ብክነት የድህነት ማፋጣኛ መሳሪያ ስለሚሆን እና ይህም ቀጥተኛ ጠላትን ዕድል እና ጉልበት ከመስጠት ስለማይለይ መሳሪያ ማባከን አርቆ ያለማሰብ ስሜታዊ ፀረ ኅዝብ እና ዕድገት አፍራሽ ባኅል መኆኑን ልንረዳ ይገባል፡፡

የጀግኖች ተጋድሎ እና የዕለት ተዕለት ዉሎ ሂደት የሚገኝን ለዉጥ ለዉጤት እና ዕድገት ለማብቃት ራሳን ማዘናጋት እና በጊዚያዊ ሽግሽግ ማተኮር ሁለንተናዊ ትኩረት እና ጉልበት ( አቅም) ማጣት ስለሚያስከትል እና እያንዳንዱ በአሁኑ ጊዜ በጠላት ላይ በሚመዘገብ የበላይነት ለዉጥ በሂደትነቱ እንጅ በዉጤት መርካት እንዳይሆን በሁሉም ይመለከታኛል ባይ  ዘንድ ሊታሰብበት ይገባል ፡፡

ቀደምት አባቶች ተኩሶ መሳት እና አግኝቶ ማጣት  አንድ ናቸዉ ፤ ፪ቱም እንደ ዕግር ዕሳት ያንገበግባሉ የሚሉንን ይዘን  እና ይህም “ጥይት በማይገባ ሁኔታ ማጮህ  ” ያልተገባ ብክነትየሚያስከትለዉን ድህነት ፣ ጥፋት  እና ሞት የኢትዮጵያዊነት እና የጀግንነት መገላጫ አለመሆኑን ሊወገዝ ይገባል ፡፡

ለዉጥ / እንቅስቃሴ ሂደት እንጂ ዉጤት አለመሆኑን ብዙወቻችን የምንረዳዉ ቢሆንም ትናንት ያቃጠለን በዓመድ የተዳፈነ ዕሳት ዛሬ እንዲያተፍን ዕድል ፋንታ ከመስጠት የማዘናጊያ እና መዳከሚያ መንገድ መማር እና መዉጣት አለብን  ፡፡

እያንዳንዳችን እንማራለን ፤

እየተማርን እንሰራለን ፤

እየሰራን ለነጻነት እና ክብር እንታገላለን ፡፡

ለራሳችን እና አገራችን በአንድነት እና ህብረት በፅናት ዘብ ዕንቆማለን ፡፡

ከዚህ ዉጭ ማንኛዉም ድል እና ዉጤት የሚለካዉ በእኛ አስተሳሰብ እና ማገናዘብ ደረጃ ልክ ነዉ ፡፡

“ ከድል በፊት አታብስር ፡፡ ”,

“ድር ቢያብር፤ አንበሳ ያስር፡፡”

“  ከ ጦር ግንባር ሠልፍ  በፊት ታሪክን ማወቅ  ” ለዘላቂ እና አስተማማኝ  ድል እንደ መረማመጃ ድንጊያ ናቸዉ ፡፡

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

“Unity is strength”

1 Comment

  1. Wrong theory ! Change is the the very interdependent and intrinsic nature and character of both results and process . It is very simplistic to say that change is just a process , not result or outcome !

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.