አንጋፋው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

alemayehu eshete

አዲስ አበባ ቤቴ
አለማየሁ እሸቴ ጎዳና የት ነው?

የድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ ነፍስ ይማር። ከተማር ልጄ እስከ አዲስ አበባ ቤቴ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ራሱ ደፍሮ በሐ7ደበት ጎዳና አሸናፊ ሆኖ የዘለቀ ታላቅ የጥበብ ሰው ነው። በተለይ አዲስ አበባ ቤቴ ደግሞ በዚህ ዘመን ፈተና ለበዛባት አዲስ አበባ የመጨረሻው ማስተዛዘኛ ማንቂያም ጭምር ናት። አለማየሁ እሸቴን ጨምሮ ታላላቅ ሥራ ለአገራቸው የሰሩትን በቅጡ በሕይወት እያሉ መዘከርም ማክበርም ዛሬም ድረስ አለመቻሉ ያስቆጫል። የአዲስ አበባው. ልጅ ተወለወዶ ባደገባት ከተማ የታዋቂነቱን ያህል በከተማው አንድ ስያሜ በስሙ አለው? አዲስ አበባ ሰፊ ናት።በሺህ የሚቆጠሩ ማቁዋረጫ ጭምር አለ። እነዚህን ጎዳናዎች እንደ አለማየሁ ያሉ ስም ሊሰየሙ ይገባል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በአርከበ ጊዜ በአዲስ አበባ ጎዳና የተለያዩ አፍሪካ አገሮችን ስያሜ ጭምር አካተው አይተናል።ጥሩ ጅምር ነበር።

በአሜሪካ ግዛቶች በአንዱ ግዛት ያሉ ከተሞችና የተለያዩ ግዛቶች ስያሜ በሌላኛው አለ። አዲስ አበባ ላይ ጋምቤላ፣አሳይታ፣ጅጅጋ፣ጎንደር፣ወለጋ፣ሀዋሳ ፣ባህር ዳርና የመሳሰሉት ስያሜን የያዙ ቢኖር መልካም ነው። እዚህ ታዋቂ ሰዎቻቸው ትልቅ ቦታ አላቸው።በየቦታው ያሉ የመንገድ ስያሜዎች አሉ። አለማየሁ እሸቴን ለማሰብ አዲስ አበባ ቤቴ አለማየሁ እሸቴ ጎዳና ወይም አለማየሁ እሸቴ ጎዳና ቢያንስ ወደ ሰፈሩ ጉርድ ሾላ የሚወስደውን ዋና መንገድ ከመገናኛ መገንጠያ ጀምሮ አለማየሁ እሸቴ ጉርድ ሾላ ማለትስ ይከብዳል? በሕይወት ያሉ በሌላውም ዘርፍ ያገለገሉ ቢታወሱ መልካም ነው።ስያሜው ካለፉም በሁዋላ ቢያንስ ከመቅረት ይሻላል።

ጣይቱን በቆረቆረቻት ከተማ ሐውልቱዋ እንዳይቆም የነበረው ጥላቻ በምርጫው ዋዜማ ተቀይሮ ቢያንስ ማዕከሉ ሊገነባ ነው። የቀድሞ አራዳ ፍርድ ቤት የራሱ ታሪክ ቢኖረውም የጣይቱ ማዕከል መሆኑ ብዙዎች ይሁን ልቦና ይስጣችሁ ማለታቸው አይዘነጋም። የሆነው ሆኖ የአለማየሁ እሸቴ ጎዳና ጉዳይ ይታሰብበት።

በድጋሚ የአለማየሁ እሸቴን ነፍስ ይማር።

ሀብታሙ አሰፋ

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.