የትህነግ አዲሱ ቀልድ – ወልቃይትና ራያ በጊዜያዊነት በፌደራል መንግስት እንዲተዳደሩ ሃሳብ አቀረበ

በጦርነቱ አውድ ድል እንዳገኘ በጌታቸው አረዳ አማካይነት የቲውተር መገለጫ እየሰጠ ያለው የትህነግ ሃይል የማንነትና የድንበውር ችግር ያለባቸው አካባቢዎች መፍትሄ እስኪገኝላቸው በፌድራሉ መንግስት ስር እንዲተዳደሩ ጥያቄቄ ማቅረቡ ተሰማ።

የኢትዮ 12 ታማኝ የመረጃ አካላት እንዳሉት መንግስት ” አሸባሪ” የሚለው ሃይል አወዛጋቢ በሚባሉት ስፋራዎች በሙሉ በፌደራል መንግስት እድንዲተዳደሩና ወደፊት ጉዳዩ በድርድር እንዲዳኝ መፍተሄ ሃሳብ አቅርቧል።

የመረጃ ምንጮቹ እንዳሉት አቶ ጌታቸው ከሚናገሩት ውጪ ድርድር ብቻ አዋጪ መፍትሄ እንደሆነ ዋናዎቹ አመራሮች ያምናሉ። ትግራይ ውስጥ ባለው ወቃታዊ ችግር፣ በመሃል አገር መንግስት ያለው የህዝብ ድጋፍ ከድርድር ውጭ የሚያስኬድ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሚያምኑት ወሳኝ አካላት ናቸው ይህን የመስማሚያ እቅድ ያቀረቡት።

በአሜሪካ አትላንቲክ ካውንስል የሚሰሩ አካላትን የሚያውቁና ለጉዳዩ ቅር የሆኑ እንዳሉት ትህነግ ያቀረበው ሃሳብ አሰቀድሞ በመንግስት የተነገረና በትህነግ “አይሆንም” የተባለ አማራጭ አሳብ ነው።

ጌታቸው ረዳ “የመንግስት ሃይል ተንዷል፣ ዋጋ የለውም፤ ደብረብረሃን እንገባለን” እያሉ በቲውተ ገጻቸው የአማራ ክልልንና የፌደራል መንግስት መካከል ልዩነት ለመፈጠር በሚያስፈራሩበት ወቅት የተሰማው ዜና አስገራሚ ሆኗል።

የትህነግ ሃይል ከትግራይ ነቅሎ እንዲወጣ ፋልጎት እንዳለ ከስልት አንጻር የሚናገሩ ሃይሎች፣ የትህነግ ሃይል ተበትኖ ከትግራይ ሲወጣ ለመመታት እንደሚጋለጥ፣ ይህም ስልት አሁን ላይ መንግስት እንደሚፈልገው የምናገሩ ወገኖች ትህነግ ከፕሮፓጋንዳ ውጪ ከትግራይ ውጭ በየትኛውም ስፍራ የህዝብ ድጋፍ አግኝቶ ሊኖር እንደማይችል ደጋፊዎች ሳይቀር ማመናቸውብ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባና በመላው አገሪቱ እንዲሁም የክልል መንግስታት የተያዘው አቋም ትህነግ በሰራው መረብ መጠመዱን እንደሚያመላክት፣ ከዚህም በላይ አሁን በያዘው የጦርነት መንገድ ለመቀጠል ስለሚችገር ሽግር ያለባቸው ስፋርዎች በሙሉ በፌደራል መንግስት ስር እዲሆኑ ሃሳብ ማቅረቡን የመረጃው ሰዎች አመልክተዋል። ከመንግስት ወገን የሰላም ፍላጎት ቢኖርም ክልሎች በጉዳይ ላይ በጋራ አቋም መያዝ ስላለባቸው እንደሚመኩበት መረጃውን ያመላከቱን ክፍሎች ገልሰዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያውያኑ በአላሙዲ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ

በሌላ ዜና በአፋር ግንባር በዛሬና በትላንትናው ዕለት ትህነግ ሰፊ ማጥቃት ያደረገ ቢሆንም ውጤቱ አሳዛኝ እንደሆነ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።

ኢትዮ 12 እንደዘገበው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share