July 19, 2021
37 mins read

 ከመሠረታዊው የሥርዓት ለውጥ ጥያቄ የመንሸራተት አዙሪትና ውጤቱ – ጠገናው ጎሹ

July 19, 2021
ጠገናው ጎሹ

እንኳን ዘመናትን ያስቆጠረ የጎሳና የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች ሥርዓትን አስወግዶ ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር የሚደረግ ትግል ማነኛውም ሌላ አይነት የለውጥ እንቅስቃሴ ምን መደረግ አለበት (what is to be done?) የሚለውን ቁልፍ ጥያቄ በእራስ መርህና የመዳረሻ ግብ ላይ ፀንቶ በሚቆም የፖለቲካና የሞራል ልእልና ፣ ወደ ተጨባጭ የተግባር ውሎ ሊያሸጋግር በሚችል አኳኋን ፣ እና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ለመመለስ  እስካልተቻለ ድረስ ትርጉም ያለው የለውጥ ውጤት የሚታሰብ አይሆንም።

ከሦስት ዓመታት በፊት በግዙፍና መሪር ዋጋ የተገኘውን ወርቃማ የሥርዓት ለውጥ እድል ተጠቅመን ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር ምን መደረግ አለበት ወይም ምን ማድረግ አለብን? የሚለውን ቁልፍ የዘላቂ መፍትሄ ፍለጋ ጥያቄ በአግባብና በወቅቱ ከመመለስ ይልቅ በፖለቲካ ወለድ ወንጀል በእጅጉ በተጨማለቀ እና ጨርሶ ሊታደስ በማይችል   ኢህአዴጋዊ ሥርዓት ውስጥ ጥርሳቸውን ነቅለው ባደጉ ሸፍጠኛና ሴረኛ ካድሬዎች የማዘናጊያ ቃላት (አንደበት) ተሽመድምደን በመውደቃችን ይኸውና ጨርሶ ማቆሚያ ባልተገኘለት እጅግ አስከፊ የመከራና የውርደት አዙሪት ውስጥ እንገኛለን።

ነፃነት ፣ ፍትህ ፣ የሰብአዊና የዜግነት መብት የሚሰፍንባት ኢትዮጵያ እውን ትሆን ዘንድ ግዙፍና መሪር ዋጋ የከፈሉ የብዙ አገር ወዳዶች (የዴሞክራሲ አርበኞች) ራዕይና ተጋድሎ  በሸፍጠኛ፣ ሴረኛ፣ ፈሪና ጨካኝ ኢህአዴጋዊያን ካድሬዎች  ተጠልፎ ለጊዜውም ቢሆን እንዲኮላሽ በመፍቀዳችን ዛሬም እራሳችንን ይበልጥ አስከፊ በሆነ የፖለቲካና የሞራል ቀውስ አዙሪት ውስጥ አግኝተነዋል።

አዎ! ዛሬም ከምር ከየእራሳችን ህሊና ጋር ታርቀን ፣ ተቀራርበን፣ ተነጋግረን ፣ተወቃቅሰን፣ ይቅር ተባብለን፣ ለህዝብ ትችት ወይም ወቀሳ ዝግጁዎች ሆነን ፣ አስፈላጊ ከሆነም በፍትህ ፊት ቆመን ለመዳኘት ሙሉ ፈቃደኞች በመሆን ከትውልድ ትውልድ እያስተላለፍነው ያለውን በንፁሃን ደም የመነገድ የፖለቲካ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዘግተን ከዘመን ጋር የሚራመድ ሥርዓተ ፖለቲካ እውን  ለማድረግ ባለመቻላችን ምክንያት የሰላምና የእድገት ጉዳይ ቅንጦት እንደሆነብን ቀጥሏል ።  ለዚህ ነው ዛሬም  መከረኛው ህዝብ ሁለቱ  የኢህአዴግ አንጃዎችና ጁንታዎች (የአራት ኪሎውና የመቀሌው) በቀሰቀሱት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ  ሳይወድ በግድ ተጎትቶ በመግባት አሳደው ፣ያዘው፣  እሰረው፣ ደብድበው፣ ሰይፈው ፣ቁረጠው/ፍለጠው፣ ስቀለው፣ ድራሹን አጥፋው ፣ ወዘተ ከሚል እጅግ  አስከፊ  የፖለቲካና የሞራል  ፈተና ውስጥ የሚገኘው።

የዚህ ዋነኛ ምክንያቶች ደግሞ ሀ) የህዝባዊ እምቢተኝነት ቁልፍ ጥያቄ መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ የሥርዓት ለውጥ እውን ማድረግ ሆኖ ሳለ የዚህ አይነት ለውጥ እውን መሆን የእኩይ ፖለቲካ ቁማራቸው ፍፃሜ እንደሆነ የተረዱ ተረኛ የጎሳ ማንነት ፖለቲካ ገዥ ቡድኖች ባዘጋጁልን “የተሃድሶ” ፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ የመዘፈቃችን ለ) ከዚህ እጅግ አሳፋሪ ስህተት ተምረን በወቅቱ ወደ ትክክለኛው የትግል መስመር ከመመለስ ይልቅ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የመከራና የውርደት መጠንና አይነት እየቆጠርን ከሦስት ዓመታት በላይ የመዝለቃችን ክፉ አባዜ መሆኑን ለማስተባበል የሚያስችል አንዳችም ምክንያት የለም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥርሱን ነቅሎ ካደገበት እጅግ አደገኛ የጎሳና የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት በተካነበት ርካሽ ስልት ማለትም ሥሥ የሆውን የህዝብ ሥነ ልቦና (ስሜት) ተጠቅሞ ለዚሁ ባሰለጠነው አንደበቱ በመስበክ (በማታለል) በተጀመረው የለውጥ እንቅስቁሴ ላይ የበረዶ ውሃ ሲቸልስበት እያየንና እየሰማን “ከሰማያዊው ዓለም ቁልቁል ወደ ምድራችን የተላከ ቅዱስ የኢህአዴግ ፖለቲከኛ” እንደሆነ   ሲነገረንና ሲተረክልን  ለምንና እንዴት? ብለን ሳንጠይቅ አሜን ብለን የተቀበልንበት እጅግ የወረደ አስተሳሰብ የማይፀፅተን ከሆነ እንኳን ዴሞክራሲን የትኛውንም አወንታዊ ለውጥ መመኘታችን ቅዠት እንጅ ከቶ የእውን አይደለም። ሊሆንም አይችልም።

እናም መከረኛውን ህዝብ ጨምረን የዚህ እጅግ የወረደና ሃፍረተ ቢስ የሆነ አስተሳሰብ ሰለባ እንዲሆን ያደረግን እለት ነበር ከመሠረታዊው የምን መደረግ አለበት ወይም ታዊው የምን ማድረግ አለብን?  ጥያቄ ተንሸራተን አሁን ወደ የምንገኝበት የቁልቁለት አባዜ መውረድ የጀመርነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ከሰማየ ሰማያት የወረደ የአገር ትንሳኤ መልእክተኛ” በሚል እንድንቀበል አደረገን የምንለው የመልካም ቃላት ዲስኩር የተፃፈበት ቀለም ሳይደርቅ እና ያዳመጥነው የድምፅ ቃና ወይም ቅላፄ ከጆሯዎቻችን ታምቡሮች (እርግብግቢቶች) ሳይጠፋ በላያችን ላይ መውረድ የጀመረውና አሁንም እየወረደ ያለው የመከራና የውርደት ዶፍ የዚህ አይነት እጅግ ደካማ የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የሞራል ድህነት እንጅ ያለመታደል ወይም የፈጣሪ ቁጣ ውጤት ፈፅሞ አይደለም። ለዚህ ነው ከሦስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረውንና  አሁንም ይበልጥ እየከፋ የቀጠለውን የሸፍጠኛና ሴረኛ ኢህአዴጋዊያን የመከራና ውርደት ሥርዓተ ፖለቲካ  ቆም በማለትና በስሜት የሚጋልበውን እኛነታችንን አደብ በማስገዛት በአሳዛኝ ሁኔታ የሳትነውን የምን መደረግ አለበት ጥያቄ በትክክል መመለስ የሚኖርብን ።

በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተረኛ ኢህአዴጎች የጎሳ/የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማር ጨዋታ አድማቂዎች በመሆን የትምህርትን (የመማርን) ትርጉምና እሴት እስከመቸና ምን ያህል ነው ማጎሳቆል ያለብንበዚህስ ምክንያት መከረኛው ህዝብ በመከራና በውርደት አገዛዝ ሥር መኖር ያለበት ለስንት ዘመን ነውማቆሚያ ባልተበጀለትና እጅግ መግለፅ በሚያስቸግር የቀውስ ማእበል ውስጥ የሚጓጉጠውን (ነፍሱን ግቢና ውጭ የሚለውን) መከረኛ ህዝብ “በለውጥ ጊዜ የሚያጋጥምን ነው ነውና አይዞን”  በሚል እጅግ ጨካኝ የፖለቲካ ስላቅ እስከ መቼና እስከ የት ድረስ ነው መቀጠል ያለበት ከሸፍጠኛ፣ ሴረኛ፣ ባለጌና ጨካኝ የጎሳ ማንነት ፖለቲካ ቁማርተኞች ጋር እየተሻሹ (እየተላላሱ) ስለ ምሁርነትና ስለ ሊቀ ሊቃውንትነት የሚተርኩልንን ደካማ (ወራዳ) ማወገኖችን በግልፅና በቀጥታ በቃችሁ ለማለት ምን ያህል ጊዜና ትእግሥት ነው የሚያስፈልገን?

 ደንቆሮና ጨካኝ የጎሳና የቋንቋ አጥንት ፖለቲካ ስሌት ቁማርተኞች የብልግና ሥልጣናቸውንና  የዚሁ ሥልጣናቸው መሠረትና ዋስትና  እንደሆነ የሚነግሩንን ህገ መንግሥታቸውን መንካት ማለት የአገር ልኡላዊነትን ማስደፈር ብቻ ሳይሆን አገርን ጨርሶ ማፍረስ እንደሆነ  ሲያላዝኑብን “ልአኡላዊነትን የምታስደፍሩትና አገርን የምታፈርሱት እናንተና የእኩይ ፖለቲካ ማስፈፀሚያ ያደረጋችሁት ሰነዳችሁ  (ህገ መንግሥታችሁ) እንጅ እኛ አይደለንምና ይልቁን  በቃችሁ” ለማለት ለምን እና እንዴት ተሳነን?

አዎ! ከዘመን ጠገቡ ደጋግሞ የመውደቅ አስከፊ አባዜ ለመውጣት አለመቻል ብቻ ሳይሆን ይበልጥ አስከፊ ወደ ሆነ የቁልቁለት አዙሪት በመንሸራተት ላይ የምንገኘው ፖለቲካዊ ተግዳሮቶቻችንን እና ከእርሱ  ጋር ተያይዘው የሚመጡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ሞራላዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶችን በተመለከተ የምናነሳቸው ጥያቄዎቻችንና የምንተነትናቸው ትንታኔዎቻችን ምን መደረግ አለበት ወይም ምን ማድረግ አለብን (what is to be done or what should we do? )  የሚለውን መሠረታዊ የመፍትሄ ፍለጋ ጥያቄ ለመመለስ በሚያስችል አኳኋን ለማስኬድ ባለመቻላችን የመሆኑን መሪር እውነት ለማስተባበል የሚያስችል አሳማኝ ምክንያት ጨርሶ የለንም።

ለዘመናት ስለ ዘለቀውና ግልፅና ግልፅ ስለሆነው የፖለቲካ ሥርዓት ብልሹነት በአገኘነው አጋጣሚ ሁሉ አብዝተንና ደጋግመን የመደስኮራችንና የመፃፋችን አስፈላጊነት እንዳለ ሆኖ  ይህን  ሁሉ የመከራና የውርደት ትርክትና ትንታኔ ወደ ተጨባጭ  ተግባር እንዴት እንተርጉመው ? የሚለውን አይነተኛ ጥያቄ እየሸሸን ጥርሳቸውን ነቅሎ ያሳደጋቸውን ህወሃት ከቤተ መንግሥት ፖለቲካ አስወግደው ሥርዓቱን ግን በእነርሱ የበላይ ገዥነት ተክተው “እያሸጋገርናችሁ ነውና በአጃቢነት ተከተሉን” ሲሉን አሜን ብለን የተቀበልን እለት ነበር ከመሠረታዊው የምን መደረግ አለበት ጥያቄ ተንሸራተን ዛሬ የምንገኝበትን አስከፊ የፖለቲካና የሞራል ውድቀት መንገድ የተቀላቀልነው ።

አዎ! ይህን እጅግ አስቀያሚና አሳሳቢ እንቆቅልሽ ቆም ብለን በማጤን በአግባቡና በወቅቱ ለመፍታት እስካልቻልን ድረስ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊነትን መናፈቃችን ቅዥት እንጅ ፈፅሞ እውን ሊሆን አይችልም።ይህ እውነት ስለ መሆኑ ደግሞ ከእኛው ከእራሳችን አስከፊና ተደጋጋሚ ሁለንተናዊ ውድቀት በላይ ሊነግረን የሚችል ማስረጃ ፍለጋ መውጣትና መውረድ ፈፅሞ አያስፈልገንም።

የጎሳና የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች ሥርዓት ከሩብ ምእተ ዓመት በኋላም ፍፃሜ ይገኝለት ዘንድ ተገቢውን የጋራ ሥራ ለመሥራት ያለመቻላችን ውጤት ከሁለት የተከፈሉ የኢህአዴግ አጃንጃዎች (ጁንታዎች)  አንደኛው (በተረኛው የኦህዴድ/ኦሮሙማ የበላይነት የሚመራው)  የአራት ኪሎ ቤተ መንግሥትን እና ሁለተኛው (የቀድሞው የበላይ አለቃ -ህወሃት) ደግሞ የመቀሌ ቤተ መንግሥትን በመቆጣጠር  እያስከተሉ ካሉት ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት  ጋር የመለማመዳችን እጅግ አደገኛ ልክፍት በእጅጉ ሊያሳስበን ካልቻለ ለአገር  ብለን የምንከፍለው ዋጋ ርካሽ እንዳይሆንብን ያሰጋል ። በሌላ አገላለፅ መስዋእትነት የምንከፍልለት መሠረታዊ ምክንያት ባለ ሁለት ፈርጅ መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅን ግድ ይላል። በአንድ በኩል  እብሪተኛ የህወሃት ቡድንን አደብ የማስገዛት ጉዳይ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ይኸው እብሪተኛ ቡድን ሩብ ምእተ ዓመት ሙሉ ሲጠቀምበት የኖረውን በፖለቲካ ወለድ ወንጀል የበሰበሰውንና  የከረፋውን ሥርዓት ያለምንም ትርጉም ያለው የለውጥ እርምጃ በተረኝነት ያስቀጠሉትን ሸፍጠኛ፣ ሴረኛና ጨካኝ የኢህአዴግ ውላጆች በፅእኑ መርህና  ዓላማ ላይ ቆሞ መታገልና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን የማድረግ ትግል ው።

እናት ምድር በጥቂት እኩያን ገዥ ልጆቿ ምክንያት ለብዙሃን ንፁሃን ልጆቿ  ምድረ ሲኦል በሆነችበት መሪር እውነት ውስጥ እንዲካሄድ የተደረገው እና እራሳቸውን ብልፅግና በሚል የማታለያ ስያሜ በሰየሙና የአራት ኪሎ  ቤተ መንግሥትን በተረኝነት በተቆጣጠረው የኢህአዴግ አንጃ  መሪዎች አዝማችነት እና የጎሳና የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርን የኑሮ ዋስትናው ባደረገ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የካድሬ ሠራዊት ዘማችነት ተፈፃሚ እንዲሆን የተደረገው ልክ ከሌለው ድህነትና ድንቁር አዙሪት ለመውጣት ያልተሳካለትን መከረኛ ህዝብ እጅግ ጨካኝ የፖለቲካ ድራማ ሰለባና አጃቢ በሚያደርግ የሸፍጥና የሴራ አውድ ውስጥ እንዲካሄድ የተደረገው  ንፁሃንን  ማጎሪያ ቤት አጉሮ በቀጠሮ በማመላለስ ግፍ የሚሠራው የእነ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ  ፍርድ ቤት “እነ እስክንድር ነጋ ለመወዳደር ይችላሉ የሚል ፍትሃዊ ብይን በየነ” በሚል ርካሽ የፖለቲካ ጨዋታ ታጅቦ እንዲከናወን የተደረገው በሚያሳዝን አኳኋን የህሊናን ሚዛናዊነት የሚያሳጣው የአድርባይነት ልክፍተኛነት እራሷን አሳልፋ በሰጠችው  የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሜዴቅሳ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ታሪካዊ  ስለ መሆኑ  ቡራኬ የተሰጠው   የሚመራው ተቋም በወረቀት ላይ የሰፈረለት የዓላማና የግብ ተልእኮ እና በመሬት ላይ ያለው የማያወላዳ ግዙፍና መሪር እውነታ ጨርሶ እንደማይገናኙ አሳምሮ እያወቀ የሰብአዊ መብትን ያህል ክቡር ጉዳይ የርካሽ ፖለቲካ ቁማር ሽፋን ሰጭ መሆንን መፀየፍ ባቃተው በሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተብየው በኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ያለምንም የጎላ እንከን የተጠናቀቀ ስለመሆኑ የተመሰከረለት  ሸፍጠኛና ሴረኛ ገዥ ቡድኖች በመንበረ ሥልጣን ላይ በተራፈረቁ ቁጥር በታዛቢነት ስም ከርካሽ ፖለቲካ ጨዋታ አጃቢነት (አድማቂነት) በማያልፉ የሲቪክ ማህበራት ተብየዎች ነፃና ትክክለኛነቱ የተነገረለት  ሥልጣነ መንበር ላይ ከወጣው ገዥ ሃይል ጋር የመገለባበጥ የአድርባይነት  ልክፍተኛ ከሆኑት ወገኖች አንዷ በሆኑት የአሁኗ ፕረዝደንት የክብር እንግድነት በአስረሽ ምችው ዝግጅት የምሥራችነቱ የተበሰረለት  እና ኪነ ጥበብን ያህል እጅግ ክቡር ሙያ በሥልጣን መንበር ላይ ለሚፈራረቁ ሸፍጠኛና ሴረኛ ገዥ ቡድኖች እኩይ የፖለቲካ ቁማር ማድመቂያነት አሳልፈው በሚሰጡ ደካማ (ወራዳ)  የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተብየዎች  የታጀበው  የገዥ ቡድኖች የምርጫ “ድል” ውጤት በዋናነት  የገንዛ እራችን ተደጋጋሚና አሳፋሪ የፖለቲካና የሞራል ውድቀት ውጤት ነው።  እናም በእውን ነፃነትና ፍትህ ፈላጊዎች ከሆን አሁንም ተጨማሪ ጊዜ ሳንገድል በሸፍጠኛና ሴረኛ የኢህአዴግ (የብልፅግና) ገዥ ቡድኖች  የማታለያ ሃይለ ቃላት (ለማታለያነት የሰላ አንደበት) ተሸንፈን ከመሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለውጥ መሠረታዊ  ምክንያት ( fundamental cause) እና እርሱኑ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ ከሆነው የተግባር ውሎ  በሚገርም አኳኋን  መንሸራተታችን ከምር ተቀብለን የሚበጀውን ማድረግ ይኖርብናል።

የገንዛ እራሳችን ልክ የሌለው ውድቀት ላስከተለውና እያስከተለ ላለው ተደጋጋሚና አስከፊ ውጤት ሰንካላ ሰበብ እየደረደርን (እየደረትን)  እና የሁለት ሸፍጠኛ ፣ሴረኛ፣ ፈሪ፣ ባለጌና ጨካኝ የኢህአዴግ አንጃዎች (ጁንታዎች) እጅግ አስከፊ ፖለቲካ ወለድ መከራንና ውርደትን እየተለማመድን ስለ ዴሞክራሲና ስለ ብሔራዊ (ኢትዮጵያዊ) ክብርና ኩራት መተረክ ወይም መደስኮር ወይም መስበክ እራስን ማታለል ነውና የሚሻለን መሪሩን ሃቅ መጋፈጥና ከዚህ አደገኛ  አባዜ ወይም አዙሪት ሰብሮ ለመውጣት የጋራ ጥረት ማድረግ ብቻ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ተጨማሪ የብዙ አሥርተ ዓመታት መከራና ውርደት ማሳለፍ አይኖርብንም።

ያለመታደል ጉዳይ ወይም የአምላክ ፈቃድ ያለመሆን ጉዳይ ሆኖብን ሳይሆን ግልፅና ግልፅ በሆነውና ዘመናትን ባስቆጠረው በእኛው በእራሳችን ልክ የሌለውና ተደጋጋሚ ፖለቲካዊና ሞራላዊ ውድቀት ምክንያት  ዛሬም የምንገኘው እጅግ አሳዛኝ በሆነ የውድቀትና የውርደት አዙሪት አባዜ ውስጥ ነው። አሁንም የተጠመድነው እኩይ ገዥ ቡድኖች እያመቻቹ በሚወረውሩልን አጀንዳ እንጅ ማቆሚያ ካልተገኘለት የፖለቲካ አስተሳሰብ ድህነትና የሞራል ጉስቁልና  ሰብረን ለመውጣት ምን እናድርግ ወይም ምን መደረግ አለበት? ለሚለው ቁልፍ ጥያቄ ተገቢውን መልስ በሚያስገኝ ሥራ ላይ አይደለም። ሸፍጠኛና ሴረኛ ገዥ ቡድኖች የሚያዘጋጁልንን አጀንዳዎች እየተቀበልን ወይ  እንደ በቀቀን በማስተጋባት ወይንም ደግሞ ለዘመናት  የኖርንበትንና  የእያንዳንዱን ቤት ምስቅልቅሉን እያወጣ የቀጠለውን መሪር ሃቅ በማንሳትና በመጣል ሥራ ላይ  ነው የተጠመድነው።

ሸፍጠኛና ሴረኛ የጎሳና የቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኛ ገዥ ቡድኖችና ግብረበላዎቻቸው ደግሞ ይህን አይነቱን እጅግ አስቀያሚ የፖለቲካ ድህነት አጥብቀው ይፈልጉታልና ከእርሱው እንዳንወጣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የማያደርጉት ጥረት ከቶ የለም። ወደፊትም በዚህ በዚሁ እንድንቀጥልላቸው የማያደርጉት ጥረት ከቶ አይኖርም።

አዎ! የነፃነትና የፍትህ ሥርዓትን እውን መሆን ከምር የምንሻ ከሆነ  ሸፍጠኞች ፣ ሴረኞች ፣ፈሪዎች ፣ ጨካኞችና እጆቻቸው በንፁሃን ደምና የቁም ሰቆቃ የተነከሩ የኢህአዴግ ውላጆች የሚሰጡንን አጀንዳ ያለመጠን ከማመንዠክ አባዜ ወጥተን  ዘመን ጠገቡን የጎሳና የቋንቋ ማንነት የፖለቲካ ቁማር ለማስወገድና ወደ ትክክለኛው የነፃነት፣የፍትህ፣ የአብሮነት፣የሰላምና የጋራ እድገት (ልማት) ሥርዓት ለመሸጋገር ምን ማድረግ አለብን? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ አጥጋቢና ዘላቂ መልስ መስጠት ይኖርብናል።

ከስህተት ለመማር ጨርሶ የማይችሉ ገዥ ቡድኖችንና ሸሪኮቻቸውን የመማፀንን፣ በክስተቶች ላይ ብቻ የመረባረብን ፣ በግልብ ስሜት የመክነፍን ፣ በእኩይ ገዥ ቡድኖች አጀንዳዎች ተጠልፎ የመውደቅን፣ ቆሞ እያስገደሉ  የአስከሬን  ቁጥር የመደመርና የመቀነስ እጅግ ክፉ አባዜን፣ የቁርጥ ቀን ወገኖችን ለግፈኛ ገዥ ቡድኖች ሰለባነት አሳልፎ እየሰጡ  ፈጣሪን ጀግና  ፍጠር እያሉ የመማፀን እጅግ አሳፋሪ ማንነትን  ወደ ትክክለኛው መስመር ለመመለስ  የነገና የተነገ ወዲያ ሳይሆን የዛሬ ሥራችን መሆን አለበት ።

ይህ እውን  ሊሆን የሚችለው ገዥ ቡድኖች ለእኩይ ዓላማቸው ማስፈፀሚያነት ለዘመናት የተጠቀሙበትንና አሁንም “በመቃብራችን ላይ ካልሆነ ጨርሶ አይሞከርም” የሚሉትን ህገ መንግሥት ተብየ እምቢ እስከ ማለት የሚደርስ ሰላማዊ ግን ጨርሶ የማይበገር ትግል መቀጠል ሲቻል ብቻ ነው። ይህን የጎሳና የቋንቋ ማንነት ፖለቲካ ቁማርተኞች ሰነድ ከበላይነት የጉልቻ ለውጥ በስተቀር ምንም አይነት ትርጉም ያለው የለውጥ እርምጃ ሳይደረግበት በቀጠለው ሥርዓተ ኢህአዴግ (ብልፅግና) ሥርዓት ውስጥ ሆኖ ለማስለወጥ ወይም ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማሻሻል ፈፅሞ የሚሞከር አይሆንም። በዚህ ሆን ተብሎ በተቆለፈ የፈሪዎችና የጨካኞች ሰነድ ላይ ተገቢው መሠረታዊ ለውጥ ወይም መሻሻል እስካልተደረገበት ድረስ  እንኳን ስለ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ህልውናዋ ስለሚቀጥል ኢትዮጵያም በእርግጠኝነት መናገር ፈፅሞ የሚቻል አይሆንም ።

ስለሆነም በዚህ ዙሪያና በአጠቃላይ የፖለቲካ ባህላችን ኋላ ቀርነትና ጋግርታምነት ላይ መክሮ ሥር ነቀል አገራዊ መፍትሄ አምጦ የሚወልድ ጉባኤ ማካሄድን  የግድ ይላል። ይህ ደግሞ ይህንኑ የእኩይ ፖለቲካ ማስፈፀሚያ ሰነድ በአዋጅ አግዶ የመዘጋጃና የመሸጋገሪያ  መንግሥት እስከ መመሥረት ሊሄድ የሚችል እልህ አስጨራሽ ትግል እንደሚጠይቅ መታወቅ ይኖርበታል ። ይህ ደግሞ አሳማኝና አስገዳጅ ምክንያት አለው። እጅግ ሸፍጠኛ ፣ሴረኛ ፣ ፈሪና ጨካኝ በሆኑ የኢህአዴግ (የብልፅግና) መሪዎች እና በሚሊዮን በሚቆጠርና የየጎሳውን ማንነት ሽፉን አድርጎ  የህዝብን ደምና የአገርን አንጡራ ሃብት  እየመጠጠ መኖር የለመደ ካድሬ የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን መሆንን ወዶና አምኖ ይቀበላል ማለት  ፈፅሞ የሚሆነ ነገር አይደለምና።

የሚያሳዝነው አሁንም ከዘመን ጠገቡ አጠቃላይ ማለትም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ፣ ሞራላዊ፣ ሥነ ልቦናዊና መንፈሳዊ ቀውስ (ውድቀት) ሰብሮ ለመውጣትና ወደ የምንመኘው ሥርዓተ ፖለቲካ ለመሸጋገር ከተግባራዊ ወይም ተጨባጭ መፍትሄ ፍለጋ አንፃር ምን ማድረግ አለብን?  የሚለውን ፈታኝ ጥያቄ ከምር ከመጋፈጥና ከመመለስ ይልቅ ዙሪያውን እየዞርን የትም በማያደርስ የትርክትና የትንታኔ ዲስኩር መጠመዳችን ነው።

በህወሃት መሪዎች የበላይነት ለሩብ ምዕተ ዓመት የዘለቀው እና ከሦስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በኦህዴድ (ኦሮሙማ) የበላይነት እና ሲጠሯቸው አቤትና ሲልኳቸው ወዴት በሚል የተሰጣቸውን እኩይ ተልእኮ ለማስፈፀም ጨርሶ በማይከብዳቸው የብአዴን ደናቁርትና ወራዳ ተባባሪነት የሆነውና እየሆነ የቀጠለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በማያወላዳ አኳኋን የሚነግረን ይህንኑ ግዙፍና መሪር እውነታ ነው።

የሰሞኑን የሸፍጠኞች፣ የሴረኞች ፣ የፈሪዎችና የጨካኞች እጅግ ርካሽ ግን አደገኛ የምርጫ ሂደት ድራማ እና ውጤቱን አስመልክቶ በምርጫ ቦርድ ተብየው፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተቀዋሚ ቡድኖች እና ቁጥራቸው ቀላል ባልሆነ ግለሰቦች ብዙ ሲባል ታዝበናል።

ይህንን የለየለት ርካሽና አደገኛ የምርጫ ድራማ አግባብነት ባለው የፖለቲካና የሞራል መርህና ተግባር መጋፈጥ ተስኖን የተለመደና ፋይዳ ቢስ የትርክትና የትንታኔ ድሪቶ ስንደርት ከወደ ሰሜን ሌላ እጅግ አሳፋሪና አደገኛ መርዶ አረዱን። ዳግም እንዳይነሳ ወይም ፖለቲካዊ  እስትንፋስ እንዳይኖረው አደረግነው ያሉት የህወሃት ሃይል ርዕሰ ከተማ መቀሌን ከመቅፅበት ተቆጣጥሮ የድል ነጋሪት ድለቃ ላይ መሆኑን  “በማብሰር” በህዝብ መሠረታዊ የማገናዘብ ችሎታ ላይ ተሳለቁ።አሁን ያለው ሁኔታ ግልፅና ግልፅ ነውና ብዙ ማለት አያስፈልገኝም።

ይህን እጅግ ተደጋጋሚና አስከፊ የፖለቲካ ውድቀት አዙሪት ሰብሮ ለመውጣት የሚያስችል የአስተሳሰብና የአደረጃጀት ልእልና መፍጠር እስካልቻልን ድረስ ህሊናቸውን (የፖለቲካና የሞራል ሰብእናቸውን) እየተፈራረቁ በሥልጣነ መንበር ላይ ለሚወጡ ሸፍጠኛና ሴረኛ ገዥ ቡድኖች (ፖለቲከኞች) አሳልፈው የሚሸጡ ወገኖች እጥረት ፈፅሞ ስለማይኖር ከአዙሪቱ መውጣት ባዶ ምኞትና ተስፋ ሆኖ ይቀጥላል። ከምር በቃ ለማለት እና እውነተኛ የሥርዓት ለውጥ እውን ለማድረግ የሚያስችል ሥራ ለመሥራት እስካልቻልን ድረስ ይህንኑ የትም የማያደርስ የትዝብት ድሪቶ እየደረትንና የምሬት ትርክት እየተረክን እንቀጥላለን።

እነርሱም (ገዥዎችም) አገር እንደ አገር ከቀጠለች ምርጫና ጡጫን እያቀላቀሉ የሸፍጥ ፣የሴራና የጭካኔ አገዛዛቸውን ያስቀጥላሉ ። ይህ ካልሆነላቸው ደግሞ የየራሳቸውን የጎሳ ወይም የመንደር መንግሥታት  መሥርተው መከረኛውን ህዝብ ወደ ባሰና  ጨርሶ ማቆሚያ ወደ እማይኖረው የቀውስ አዙሪት ውስጥ ይከቱታል ።ለዚህ ነው በገዥ ቡድኖች አጀንዳ እየተጠለፍን ደጋግመን እየወደቅን ያለንበትን አስከፊ የፖለቲካ አዙሪት ሰብሮ ለመውጣት ለምንና እንዴት እንደተሳነን ከምር መርምረን ትክክለኛውን የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ያለብን ነገና ከነገ ወዲያ ሳይሆን ዛሬውኑ መሆን ያለበት።

የአገር አፍራሾችን ህገ መንግሥትና የፖለቲካ መዋቅር እሹሩሩ እያሉ አገር ፈረሰ ወይም ሊፈርስ እያሉ እግዚኦ ማለት ጨርሶ ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop