“ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ”  ማደናገሪያ እንጅ ህዝባዊነት አይደለም !!! – ማላጂ

በኢትዮጵያ የቡድን ስልጣን እና ጥቅም ከማስከበር እና ትዕዛዝ ጠባቂ ከመሆን ባለፈ ህዝባዊነት እና ወገናዊነት ያለዉ እና በተግባር ያስመሰከረ አገራዊ አደረጃጀት ከጠፋበት ግማሽ ምዕተ ዓመት ማስቆጠሩን አንርሳ የተረሳም ፤የሚረሳም ካለ እናዉሳ ፡፡

ካለፈ የማይማር ወደፊትም እንዴት እንደሚኖር ሀሳብ(ዕቅድ) እና ግብ ሊኖረዉ እንደማይችል መገመት ይቻላል ፡፡

ለዓመታት ብሄራዊ አንድነት እና ህዝባዊ ትስስርን ለማናጋት በአንድ የህብረተሰብ ክፍል ላይ በሚደረግ ልዩ ልዩ ኢሰባዊ ድርጊት ( ሞት ፣ ማሳደድ፣ ማፈናቀል….ዝርፊያ….) ግጭት እያሉ ማደናገር ከድርጊቱ በፊት  ሀሳቡ  የአገር ሉዓላዊነትን የማዳከም የኢትዮጵያ እና ህዝቦች ባላንጣ የዘመናት ዱለታ መሆኑን እየታወቀ  የማይገባ ስያሜ ግጭት ማለት ችግሩን የመዳፈን እና መፍትሄ አለመሻት  ፍላጎት ነበር ፤ ነዉ ፡፡

ከጥንት አስካሁን ዐማራን ለማጥፋት በጠላትነት የሚፈርጅ እና የፈረጀ ሁሉ የዓማራ ጠላት በማለት ብቻ ለመቀንበብ ለሚሞክሩ ኢትዮጵያን ለማክሰም የተደረገ እና እየተደረገ ያለ ተልዕኮ መሆኑን  ኢትዮጵያዊ እና ሠባዊ ፍጡር የሆነ ሁሉ ስለማያዉቅ ነዉ ብሎ ማለፍ የቁም ሞት እንደሆነ መረዳት የሚያቅተዉ ወይም የማይፈልግ ቢኖር እርሱ አገር ለማጥፋት ከሚሰሩት እንደማይለይ መገመት ለቀባሪ ማርዳት ነዉ ፡፡

እና ለምን ይሆን የዓማራ (ኢትዮጵያዊ) ለዘመናት የተሸረባ የጥፋት ሴራ በዓለማችን በየትኛዉም ዘመን እና ታሪክ በራሱ ህዝብ እና መንግስት የደረሰበትን ዕልቂት ፣ ሞት ፣ስደት ፣ድህነት …..የመሳሰሉት ወደር አልባ አሳሮች ግጭት እያሉ  ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ የሚሆነዉ ፡፡

ግጭት ዕኮ በተመሳሳይ የማህበራዊ እና ሉዓላዊ ደረጃ ወይም ዕርከን ለሚገኝ ግለሰብ ፣ ጎረቤት፣ቡድን ፣ ማህበረሰብ ፣ ህዝብ ፣ መንግስታት…. ወዘተ ለሚከሰት የጥቅም ወይም ይገባኛል ጥያቄ አስነሽ በመካከል ሲኖር ነዉ ፡፡

ለዓብነት በ1960 ዎች  በመቃዶሶሾ እና አዲስ አበባ፣ በካርቱም እና አዲስ አበባ፣ በኢራን እና አሜሪካ፣ በቻይና እና አሜሪካ….. ሆኖ ዝቅ ሲል በአርሶ አደር ዉሃ ፣ግጦሽ/መኖ…. ሊባል  ይችላል ፡፡

እና አስከ መቸ ነዉ በአንድ ህዝብ ላይ ለዘመናት  በሰዉ ልጅ ታሪክ ባልነበር ዘግናኝ ኢሰባዊ ጥፋት በተደራጀ እና በታቀደ  ኃይል እና አካል ክቡር የሆነዉን የሰዉ ልጅ ለዚያዉም በደም እና አጥንት በመሰረታት እናት አገር ምድር  እንደ ሶስተኛ ዜጋ እየታየ እና እየተሳደደ ላለ ህዝብ የዘመናቱን መከራ ግጭት  ብሎ ሞትን/ፍጅትን ዕኩል የመሰየም አባዜ የሚቀጥለዉ ፡፡

የየትኛዉም ብሄራዊ አደረጃጀት የህዝብ ዉግንና አስካለዉ ድረስ ህዝብ በራሱ አፈር ምድር ባይታዋር ሆኖ የግፍ ግፍ እያስተናገደ ከሞት እና ስደት በኋላ አለን ማለት እና አገር እየፈረሰ እና ህዝብ የደም ዕንባ እያለቀሰ ትዕዛዝ ጠባቂነት አስከመቸ እንደሚሆን  ባይታወቅም ህዝባዊነት ከአድር ባይነት እና ከግለሰባዊ አድርባይነት ስሜት እና አመለካከት አስካለወጣ የዜጎች ሞት እና ስደት የአገር ሞት መበቻ መሆኑን ሁላችን መርሳት  የለብንም ፡፡

በአጭሩ በዘመናችን ከማለባበስ እና ከማድበስበስ ለአገር እና ለህዝብ መከራ እና ስቃይ ከማራዘም ዉጭ የሚኖር ፋይዳ ስለማይኖር  ህመሙን የደበቀ መዳኛ የለዉም እንዲሉ  በአገራችን እና ዜጎች ላይ የሚደርሱትን እና የደረሱትን የዓለማችንን የዜጎች የስቃይ ክብረወሰን የሚከነዱ መከራወችን የዳቦ ስም መስጠት መቆም አለበት ፡፡

“ትልቅ አስኪዳር ትንሽ ቆሞ ይቅር ” ቆሞ ቀር አስተሳሰብ መቁረጥ የዕኛ  ኢትዮጵያዉያን እንጅ ጠላቶቻችን (የዉስጥ እና የዉጭ) ለክተዉ እና ቆርጠዉ በሚሰጡን የሽንገላ ጋጋታ አንጠበቅ፡፡  ነጻነት እና ክብር በራስ ከራስ የሚገኝ  እንጅ ሌላዉ የሚቸረን ገፀ በረከት አለመሆኑን እንወቅ ፡፡

ዕድሜ ልካችንን አለን እያሉ ለሚክዱ እና ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ  ንግግር አይሉት ማደናገር ገለል ብለን በህብረት እና በፅናት በመቆም ከመርህ ይልቅ  ለተግባር ከተፈጠሩት  በቁጥር ጥቂት በዓለማ ብዝኃነት ካላቸዉ ጋር ሁላችን ለአንዳችን ፤አንዳችን ለሁላችን  እና ለአገራችን ዘብ እንቁም ፡፡

የጋራ አገር እንጅ የጋራ የአስተሳሰብ ነጻነት የለም እያንዳንዳችን ስለራሳችን ሌሎች  ነጻነት እንዲሰጡን ወይም ታምር እንዲፈጠር በከንቱ ምንም ከማንም ሳንጠብቅ የተፈጥሮ እና ሠባዊ ክብር እና ነጻነታችንን እንጠብቅ ፤እንወቅ ፡፡

ወንዙም ፣ ሸንተረሩም…….ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ሲኖሩ እና ሲኖሩ ብቻ ነዉ ፡፡

አገር እየናዱ ፤ አገር አገር ሲሉ ፤

ስራቸዉ  ነዉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚግተለረሉ ፣

አደራ ብያለሁ ያለፈዉ ይበቃል እንዳትዘናጉ ፤ እንዳትታለሉ ፡፡

“በጀግኖች የቁርጥ ቀን ልጆች ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ ታፍራ እና ተከብራ  ለዘላለም ትኑር !!!”

 

ማላጂ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.