የማይካድራው ጨፍጫፊ ቡድን ሳምሪ በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ውስጥ እንዳለ አሸባሪው ሕወሃት አስታወ

አማራ ሚዲያ ማዕከል

ሰኔ 29/2013 ዓ.ም በሕግ ማስከበር እርምጃው ከሚጠብቀው በተቃራኒ ነገሮች በፍጥነት የተቀየሩበት አሸባሪው ሕወሃት ሽንፈቱን በአማራ ሕዝብ ላይ ባነጣጠረ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ደመደመ፡፡
በማይካድራ የሚገኙ ንጹሃንን ጨፍጭፈው ወደሱዳን የሸሹት ቡድኖች የራሱ ወታደሮች መሆናቸውን አሸባሪው ህወሓት ዘግይቶም ቢሆን አስታውቋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ያደራጃቸው እና በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ ያካሄዱት ሳምሪ የተባሉት ወጣቶችና ሚሊሻዎች በሱዳን በስደተኛነት ስም ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ጉዳዩ ቢዘገይም አሸባሪው ህወሃት እነዚያ ገዳይ ቡድኖች በሱዳን እንደሚገኙ ተናግሯል፡፡ አሸባሪው ቡድን ለፋይናንሻል ታይምስ እንደገለጸው እስከ 30 ሺህ የሚጠጋ ወታደር በሱዳን አለኝ ብሏል።
ፋይናንሻል ታይምስ የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ነገሩኝ እንዳለው ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ 30 ሺህ ወታደሮች በሱዳን ተጠልለው አሉ ብሏል፡፡
ሳምሪ በሚል መጠሪያ አሸባሪው ቡድን አደራጅቷቸው የነበሩት ገዳዮች በማይካድራ ቤት ለቤት በመዞር መታወቂያ እየተመለከቱ አማራዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋቸው ይታወሳል።
መንግሥት በተደጋጋሚ የሳምሪ አባላት በሱዳን የስደተኞች ካምፕ በስደተኛ ሥም እንደተጠለሉ ሲገልጽ ቢቆይም ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ሆነ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት ጉዳዩን መስማት የፈለጉ አይመስሉም ነበር፡፡
ዘግይቶም ቢሆን ግን አለማቀፉ ማኅበረሰብ መስማት ያልፈለገውን እውነት ህወሃት የመንግሥት ተደጋጋሚ ጩኽት ትክክል እንደነበር ይፋ አድርጓል፡፡
አሚኮ እንደዘገበው።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ለቸኮለ! ቅዳሜ ታኅሳስ 30/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share