በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለአዲስ ግጭት ዝግጅት መኖሩን ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች አመለከተ

ድርጅቱ ዛሬ በማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴ ገጾቹ በአጭሩ ይፋ ያደረገው መረጃ ትግራይ ውስጥ ያሉ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥት ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ወደ ጎን ብለው ለአዲስ ግጭት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ይገልጻል።
–በሌላ በኩል የትግራይ አማፅያን ኃይል ዋና አዛዥ የተባሉት ጻድቃን ገብረስላሴ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ እና ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲገኝ ጥሪ ማቅረባቸዉን ሮይተርስ ዘግቦአል። ፃድቃን በድርድር ላይ የተመረኮዘ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ነን ማለታቸዉን ሮይተርስ ዘግቦአል።
–ኢትዮጵያ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት መጀመርዋ ተገለፀ። በሌላ በኩል የአረብ ሊግ የኢትዮጵያን የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ የሚያደርገውን ያልተፈለገ ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያ እንደማትቀበልም አስታዉቃለች።
–እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። ተከሳሾቹ ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤት አንቀርብም ክርክሩ የፖለቲካ ክርክር ነው። የሚፈታውም በአስፈፃሚው አካል እንጂ በፍርድ ቤቱ አይደለም’’ ሲሉ በድጋሚ አስታውቀዋል።
–የአፍሪካዋ “ማዘር ትሬዛ” ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ከ41 ዓመታት በላይ አሳዳጊ ላጡ ህፃናት እናት በመሆን አሳድገው ለቁም ነገር በማብቃት የአገር ባለውለታነታቸውን ያሳዩ እናት ነበሩ።በጉጉት እየተጠበቀ ነዉ።
የአዉሮጳ እግር ኳስ ሻንፒዮና እንደቀጠለ ነዉ። ዛሬ በብሪታንያ ለንደን ላይ በኢጣልያ እና ስፔን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚካሄደዉ የግማሽ ፍጻሜ ግጥምያ በጉጉት እየተጠበቀ ነዉ።
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  14 ዓመታት ተፈርዶበት እስር ቤት የሚገኘው ውብሸት ታዬ የሲኤንኤንን ሽልማት አሸነፈ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share