ዝም በል ! ንገሩኝ ባይ በዓለም ፪ ዕዉነት የለም !! – ማላጅ

ለህዝብ እና አገር በሚጠቅሙም ሆነ ጥያቄ በሚያስነሱ ጉዳዮች ላይ ዞትር እገሌ አለ ፣ መግለጫ ሰጠ ፣ ትዕዛዝ ሰጠ ….እንጅ ህዝብ ፣ አገር እና መንግስት በግንባር ተነጋገሩ ሲባል ለመስማት አላደለንም ፡፡
ጥዋት የተነገረ በረፋድ ሲሻር ፣ ሲተገሙ ዓሜን ፣ ሲሰደቡ ዓሜን ፣ መሸ አሜን ፤ነገ ዓሜን አስከ መቸ ይሆን የሞት ቀንበር ተሸክመን በሰመመን የምንኖረዉ ለማት እንዴት ተሳን ፡፡
እኮ እንዴት ነዉ ኢትዮጵያ ላይ ሁለት ዕዉነት የሚኖረዉ ፡፡

ኢትዮጵያ የአንድ ነገድ ወይም የቀደሙ በደም እና በአጥንት የሰሯት አገር እና ለተዉልድ ህይዋታቸዉን ቤዛ ያደረጉትን ዉሾን ያነሳ ዉሾ..እያለ ከጥፋት እና ክህደት ኃይሎች ጋር ሲከድም የነበር የደንቆሮ አጨብጫቢ ለአገር እና ወገን ደህንነት እና ነፃነት አሳቢ አድርጎ ሲያመልክ የነበረን ይዞ ዕዉነተኛ እናተጨባጭ ሁነኛ ለዉጥ ለጠበቅን እና ለምንጠብቅ አሁንም ከተጫነን አዚም አለመላቀቃችን ምልክት ነዉ ፡፡
ለዚህ ነዉ ትናንት ደጋግመዉ ለዘመናት ህዘብን እና አገርን ደጋግመዉ ለካዱት እና ለጎዱት መጠሪያ እና ማስመሰያ በለዋወጡ ቁጥር ዕዉነት እያልን አሜን ማለት በዕዉነት ላይ ያለን ግንዛቤ መንታ መሆን ነዉ ፡፡

መንታ ሀሰት እንጅ መንታ ዕዉነት ኖሮ አያዉቅም ነገርግን ሁሉም በብርሀን ስለጀግንነት ፣ስለፅድቅ የሚያወራ ሲጨልም እና በመከራ ጊዜ ዓይኔን ግንባር ያድርገዉ ለሚሉት ዕዉነት ማለት ከንቱ እና ዕርባነ ቢስ ሀሰት ወይም የመንታ ዕዉነት ሰለባ ከመሆን ቆፈን ለመላቀቅ ራሳችንን ማዘጋጀት ስሜታዊ እና ሰሞነኛ ከመሆን ወጥተን ዘላለማዊ ዓላማ ይዘን በህብረት እና አንድነት ራሳችንን እና አገራችንን መታደግ ይኖርበናል ፡፡
ለዚህ ሀተታየ የጥቅምት 24፣2013 ዓ.ም. የተከሰተዉ እና የተወለደዉ የዘመናት ኢትዮጵያን የማጥፋት ሴራ ሂደት ዉጤት እንደነበር መረዳት ያለብን ዛሬ ሳይሆን ከኋላ የታሪካችን መማር እና መኖር መቻል ነበር ፡፡

ዛሬ ከስምንት ወር በፊት የተጀመረዉ ብሄራዊ ስጋት እና ዕዉነት የተበተነ እና የበነነ ነበር ሲባል ዕዉነት ፤ዛሬ ከስምንት ወር በኋላ ሰኔ 23፣2013 ዓ.ም. የበነነ፤የተነነ ዳነ ሲባል ዕዉነት ለምንል ምን ያህል ስለዕዉነት እና ስለራሳችን ያለን ግምት ከጊዜ ወደ ጊዜ የማይሻሻል መሆኑን ነዉ ፡፡
በወቅቱ ህግ ማስከበር ከማለት የአገር እና የህዝብ ደህንነት ለማለት አለመቻል፣ድል በድል ከማለት ጊዜያዊ አድናቆት እና መንጫጫት መዉጣት እንደሚገባ፣ ራስን እና አገርን ለመከላከል የምንዘናጋበት እና የምንኩራራበት ፣ የምናቀላፋበት( ኢትዮጵያን የሚል አይተኛም ፤አያነቀላፋም )፣ ሰሚ ስጠን …. በሚል በተለያዩ ፅሁፎች ለመግለፅ ጸሞክሯል ዳሩ ሰሞንኝነት እና መንታ ዕዉነት አባዜ አፍዝ አደንግዝ አስኪመስል ይኸዉ ዛሬ ላይ አደረሰን/ ጣለን ፡፡
አንድ ዕዉነት መኖሩን ክደን የራሳችንን ዕዉነት መሰል ሀሰት እየተጋትን እንደአገር እና ህዝብ የዘመኑን ከፍተኛ ሁሉን አቀፍ ዋጋ በጥቂቶች ጥፋት እና ዕብሪት ዳፋ የግፋ ፤ግፍ እያስተናገድን ነዉ ፡፡
ይህ የሚሆነዉ ከራሳችን እና ከምንኖረዉ ዉጭ ሌሎች የሚነግሩን አሜን ባይ አድር ባይነት ጠባይ ስለተጣባን ነዉ ፡፡
የሚገርመዉ ሞተ ሲሉን ሞቷል ፣ ተነስቷል ሲሉን ተነሳ ለማለት የተጋን ትዉልዶች መቸ ዓምላክን እና ራሳችንን የምንመለከት እና የምንሆን እንደሆነ እንደ ሠዉ እና ኢትዮጵያዊ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

አሁንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ራሱን ከራሱ ፣ከታሪኩ እና ከመሰል የዓለም ህዝብ እና አገራት መማር እና ለምንጊዜም መዘጋጀት አለብን ፡፡
ለዚህ ከአስራኤል፣ ከራሽያ፣ ከቀደሙት የእኛዉ ዋኖች ለመማር መስነፍ የለብንም ፡፡

በታሪክ መንደርደር እንጅ መኖር አይቻልም ፡፡ ሞኝ የጌታ ልጅ ነበርኩ ይላል በተራ እና በሰሞነኛ ዕንቆቅልሽ መዘናጋት የለብንም ፡፡
ኢትዮጵያዊነት በተግባር እና በመኖር እንጅ በአስመሳዮች ተኩላወች ወርቅ አስጨብጥ መደናገር እና መወናከር ነዉ ፡፡
“የጨዉ ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ፤ ብልህ ያለቅሳል ” እንዲሉ ለዓመታት የነበረዉን ኢትዮጵያን ለማሽመድመድ ኢትዮጵያዉያንን በተለይም ዓማራ ተሳደደ፣ ተወገደ ፣ ነደደ….ለሚሉት ሁሉ ኢሰባዊ እና ፀረ ኢትዮጵያ ጠላቶች አሁንም እንደትላንት ልማድ ሱዳን ፣ ግብፅ፣ ከሀዲዎች….ምዕራባዉያን……..መቱለት ለሚሉት ኢትዮ ጠሎች ወዮላቸዉ ፤እንዘንላቸዉ !!!
ግን እንደ ዕባብ ልባም ፤ እንደ ዕርግብ የዋህ መሆን እንጅ …….መዘንጋት ፤መዘናጋት የለብንም፡፡ ጠላትን ይቅር ማለት ዕንጅ ጥቃቱን እና ጥፋቱን መርሳት አይቻልም ፡፡
ጠላት በተለይም መረዕራባዉያን ዓማራ ለሚሉት መቀጠል አለመቀጠል የኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ጉዳይ ነዉ ፡፡
ዓማራነት ኢትዮጵያዊነትና እና ማንነት ላይ አስከሆነ መደራጀት ችሮታ ሳይሆን ግዴታ ነዉ ፡፡
“ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ህልዉና ለመታደግ እና ለማስቀጠል የማከለስ ፣የማይገሰስ ከሰማይ በታች ያለ ማደናቆሪያ ልማድ እና ገደብ መገርሰስ እና መናድ ይኖርበታል፡፡”
ንገሩን ባዮችም ዝም ብትሉ ይበጃል ሁለት ዕዉነት የለም እና ያዞ ዕንባ …….መቆም አለበት ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ” !!

ማላጅ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.