የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዳግም እንዳይመረጡ ተጠየቀ

በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ እየጨመረ በመጣው የሥነ ምግባር ጉድለት፤ማጭበርበርና ጾታዊ ጥቃት የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዳግም እንዳይመረጡ ተጠይቋል።
አለም አቀፉ ኢንዲፔንደንት ፋይናንሽያል ኦዲት ባቀረበው የኦዲት ሪፖርት በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ማጭበርበር፣ ጾታዊ ጥቃትና የሙያ ደረጃዎችን ያልጠበቁ አሰራሮች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል።
የአለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ የ2020 አመታዊ አፈጻጸምን በተመለከተ የኦዲት ሪፖርት ቀርቧል።
በዚህም በተቋሙ እየጨመረ የመጣውን የሥነ ምግባር ጉድለት ማጭበርበርና ጾታዊ ጥቃት ተከትሎ የድርጅቱ ዳይሬክተር ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይመረጡ የአለም ኤች አይቪ ኤድስ ሄልዚኬር ፋውንዴሽን ጠይቋል።
ሪፖርቱ በ2020 የበጀት አመት የአለም ጤና ድርጅት ከ332 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአሰራር ውጪ ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ማድረጉን አመላክቷል።
በተጨማሪም 2.5 ሚሊዮን ደላር ደግሞ ከደረጃ በታች ለሆኑ ውሎችን በመዋዋል ገንዘቡ ኪሳራ ላይ መዋሉን ነው የተገለጸው።
ፋውንዴሽኑ በድርጅቱ ለታዩት ችግሮች ተጠያቂው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም መሆናቸውን አመልክቶ ለሁለተኛ ዙር የድርጅቱ አመራርነት እንዳይመረጡ በማሳሰብ ነው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥያቄውን ያቀረበው።
የኦዲት ግኝቶቹ በአለም የጤና ድርጅት ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና በስራዎቹ ላይ ግልፅነት የጎደለው አሰራር መኖሩን እንደሚያመለክቱም አስታውቋል።
“በዚህ ችግር ምክንያት ሰዎች የኮቪድ መከላከያ ክትባቶችን እንዳያገኙ፣ ሚሊዮኖች ለሞት እንዲዳረጉና ከግለሰቦች እጅ በልግስና የሚሰበሰበው ገንዘብ ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ሲሉ የኤች አይቪ ኤድስ ሄልዚኬር ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ማይክል ዌንስተን ተናግረዋል።
የአለም ጤና ድርጅትን አመኔታ ለመመለስና የታዩ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ችግሮች ለመቅረፍ ተመድ አዲስ ፕሬዚዳንት ሊሾም እንደሚገባም ፕሬዚዳንቱ ማስታወቃቸውን ቢዝነስ ዋየር አስነብቧል።
EBC
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መዋቅር እና አደረጃጀት መመሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share