ሀገራችንን በማስቀደም ምዕራባዊያነ እናሸንፍ (በጋዜጠኛ ቶማስ ሰብስቤ)

ልዮነታችን ሀገራችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ማድረግ የለበትም::በየትኛውም ሀገር ልዮንት አለ ፣ ያለመግባባት ፣ ከፍተኛ ተቃርኖ ያለም ፣ የሚኖርም ነው::ሀገር ይዞ የትኛውም የፖለቲካ ስጣ ገባ ና ማሀበራዊ ውጣ ውረድ  በጊዜና በብልሀት መወጣት ይቻላል::ያለብን ችግር ምን ያህል የከበደ ቢሆን ሰው ሀገሩን እያፈረስ ችግር አይፈታም::ከግለሰብ እስከ ማህብረሰብ ያሉ  እጅግ ውስብስብ ችግሮች ፣የመኖርና ያለመኖር ትንቅንቆች ፣ ፍታዊነት ማጣት ለመመለስ ሀገር ያስፈልጋል ሁሌም::ሊቢያኖች እንደዛ የፈለጉትን እና የተዋደቁለትን ዲሞክራሲ ሀገራችውን አፍርስው አላገኙትም::ሚሊየኖች የቀጠፈውና የገበሩት ሶሪያዊያን የት ናችው ……..ያሰቡት ሳይሆን ያላስቡት ሆነ ….…ሶሪያ ወደምች…..…ሚሊየን አለቁ…..…ለሺ ዘመን የገንቡት ሀገር ዛሬ የለም ፣ ዛሬ ሶሪያኖች በስድት ተበታትንዋል ::ከግለሰብ የዘለለ የሀገር ክብር የሚመኙት እንጂ ዛሬ በጃቸው የለም::ሁሉም ነገር አከተመማቸው ግን ዛሬም ችግራቸው አልተፈታም::ጦርነትና እርስ በእርስ መጋጨት ጥያቄያችንን ይመልሳል ብለው የገቡበት ውርደት ጥያቄያቸውንን አይደለም ሊመልሰላቸው ይቅርና ሀገራቸውን አሳጣቸው::እና የሀገሬ ስው ሀገርህን ጠብቅ::ሀገር አፍርሶ የሚመለሰ አንዳች ነገር የለም ፣ ኖሮም አያውቅም::

 

በብሄሬ ተበደልኩ ብለህ ልታምን ትችላለህ ፣ ጭቆና ለዘመናት አልፎብኛል ብለህ ልታምነ ትችላለህ ፣ ለብሄር እኩልነትና ፍትሀዊነት እየታገልክ ይሆናል ፣ ለዚህ ጥያቄ መልስ የምታገኝው ሀገር ከሚያፈርሰ ሃይልና ሀገራት ጋር በጋራ የራሰህ ሀገር ላይ ድንጋይ በመወርወር ሳይሆን ፣ ሀገርህን እያፈረሰክ ሳይሆን ብሄር የሚገኝበትን ሀገርህን አንድንት እየጥበክ መታገል የብልህ ጨወታ ነው::ሶሪያኖቸ ሶሪያን አፍርሰው ችግራችውነ እንዳልፈቱት ሁላ ማንም ስው ሆነ ቡድን ኢትዬጵያን እያፈረሰ ቸግሩን የሚፈታ መስሎተ ከተሰማው ፖለቲካ ሊገባው ይቅርና የቆመበትንና የሚታገልለትን ጉዳይ ጠንቅቆ መርዳቱ ያሳሰባል::ሰው እንዴት ቤቱን በሳት ሆን ብሎ እያቃጠል ከቤቱ ውሰጥ ንብረቱን ሊስበስብ ይሻል ፣ ሰው እንዴት ሀገሩን እያፈረስ ብሄሩን ከሀገሩ ውስጥ ሊያወጣ ይሻል…..ሀገር ይዞ ነው መልስ ያለው::

 

ኢትዬጵያን ለማፈራረስ ባለ ሩጫ ውሰጥ ምዕራባዊያን ከጀርባ ሆነው መሰለፋችው ሊያስገርመን አይገባም ፣ የሶሪያንና ሊቢያን ውጣት ከናተ ጋር እንቆማለን ብለው አሜሪካ ፣ፈረንሳይ፣እንግሊዝና አጋሮቻቸው ሀገር እንዳወደሙ በቅጡ ለገባው ሰው ምንም አይገርመውም፣የትኛውም የራሳቸውን ጥቅም የሚያሰጠቅሙበት ነገር ላይ ሀገር ለማፍረስ ወደሃላ የለም እነሱ ጋር፣ ለተቃዋሚውም ልግዥውም በቢሊየን ዶላር መሳሪያ ያሰታጥቁሃለ ::ሀገርህን ስታፈርስ አላማችው ተሳካ ከዛ ብሃላ ሊስሙሀም አይችሉም፣የነሱን ሎሌ መንግሰት በወደቀ ሀገር ላይ ይመሰርቱልሀል ::ከዚህ በሃላ የአንተ ጥያቄ ቅዥት ይሆንና የነሱ ትዛዝ ሲፈጰም ትመለከታልህ ወደድክም ጠላህም::የትኛውም ምዕራባዊ ሀገር ኢትዬጵያ ከፈረሰች በሃላ የእንትና ብሆር ጥያቄ አልተመለሰም ብለው አይታገሉልህም፣ እርስ በርስ ስትጫረስ መሳሪያና ቡጫቂ ምግብ ይስጡሃል አልቀ::

 

የትኛውም ምዕራባዊ ሀገር የተጋሩ መራብ ፣መሰቃየትና ሰቃይ ለራሱ ፖለቲካ ባይረዳው መስሚያ የለውም::ከተጋሩ ጋር መቆም የሁሉም የሀገራችን ህዝብ ግዴታም ነው ፣ መረዳዳትና ሀገራዊ አንድነታችንን ማሳየት አለብነ፣ ችግራቸው ችግራችን ነው ፣ ኢትዬጵያን እያፍረሱ ተጋሩን መውደድ የለም::ለትግራይ መቆም ለሀገር መቆም ነው ፣ ምዕራባዊያንን ማሽነፍም ነው::ትላንትም ዛሬም ለሀገር ቆሚለው የሚል ስው በትግራይም ሆን በየትኛውም የሀገራችን ቦታ ላለው ችግር የመፍትሄ እንጂ የሌላ ችግር መንሳኤ መሆን የለበትም::ምዕራባዊያን ሀገራችን ካፈረሱተ በሃላ ፣ሀገር አልባ ሆነን መከራችን ይበዛል እንጂ ረፍት የለንም ::

 

ከግብጰ ጋር ሆና የአባይ ግድብ ላይ ሴራ ምጠመጥም ሀገረ አሜሪካ በምን እሳቤ ነው ለትግሬ ፣ ኦሮሞ ፣አማራ ፣ኩናማ……የምታስብልህ ወገን ፣ ወደድንም ጠላንም ግድቡ የትኛውም ብሄር በፍትሀዊነት ሆን ኢ ፍትሃዊንት መጠቅሙ አይቀርም::የአሜሪካና የግብጰ ሴራ ተሳክቶ ቢፍርስ እኛው በጨለማ እንገፋዋልን እንጂ እነሱ ምንም አይሆኑም::የትኛውም የውጪ ወራሪ ሀገር ውስጥ ቢግባ ማንም ከሚመጣው ሰቃይና ምከራ ፣ሞትና እልቂት በዘሩ ሆነ በሰራው አያመልጥም::ሀገር ሲወድም ሰፈርህም ይወድማል ፣ ቤተስብህ ባያልቁ ውዳጅህን መቅብር አይቀርም::አንተ ትከሰራለህ ፣ታልቃለህ ፣ መሬትህን ጥለህ ትሰደዳልህ ፣ ሀብት ንብረት ይወድማል ፣ ክብር ቢስ ሆን ወድ ሃላ ታስባለ ፣ ጠላቶች ያተርፋሉ ::ያኔ ምዕራባዊያን አጠገብ የሉም::

 

ሀገር ማስቀደም ማለት ቤተስብህን ፣ አካባቢህን ፣ ማህብረስብህን ፣ ብሄህን ፣መሬትህን በጋራ ማስጠብቅ ማለት ነው::ይህ እያስጠበቅ የትኛውም ጥያቄ እሰኪፈታ ታገል፣ ላመንክበት ነገር ሁላ የትኛውንም መስዋትነት ክፈል::የሀገር ፍቅር ያለው ሰው ለሚሆንው ብቻ ሳይሆን ስለሆንም ነግሮች ብዙ ያስባል::

 

አልማዝ አሰፋ እዳለችው….የምንኖርበት አለም በድንበር የተከለሉ አገሮች የተደራጁባት ነች:: እያንዳንዱ አገር የእራሱ አስተዳደር ስላለው ከድንበር ውጭ ያለው ጎረቤት ወይም ከሩቅ አገር የመጣ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት መብት የለውም:: ከገባም የሚደርስበትን ጥቃት ሳንገነዘብ አልቀረንም:: ከአገሪቱ ተወላጆች መሃል የሚወጡት መሪዎች ለዚያች አገር የወደፊት እድገት : ልማት : ብልፅግና : ሰላም : አንድነትና ሉአላዊነት ኃላፊነት አለባቸው:: አገርን አገር የሚያሰኘው የሕዝብ መኖር ነው:: አገርን የሚያነሳውም የሚጥለውም የሕዝብ ተባብሮ በሰላምና በአንድነት መኖርና ተግቶ በጋራ መስራት ነው:: ሕዝብ በሰላም ሲኖርና እንድነቱን ሲያጠናክር : አገር ሰላምና አንድነት አላት ይባላል:: ሕዝብ በሰላምና በአንድነት ኑሮ አገር እንድትበለፅግ ከተፈለገ መልካም አመለካከትና ቅንነት ያላቸው ግለሰቦች አስተዳዳሪና መሪ መሆን ይገባቸዋል:: ጥሩ መሪ የመጀመሪያ ግንዛቤ ማድረግ ያለበት : የሕዝብ ተወካይና ጉዳይ አስፈፃሚ እንጂ አዛዥና ገዢ እንዳልሆነ ነው::

 

ሀገር ማስቀድም የህልውና ጉዳይ ነው:: ሀገራችንን ይዘንና አስቀድመን የትኛውም አሁን ላይ ያለ ትንሽም ሆን መጠነ ስፊ ችግር  በጋራ እንወጣዋለን፣የተሻለው ጊዜ ሀገር ይዘን መጠበቅ ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:   የሕብር ሬዲዮ ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሮግራም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share