ዜጎችን ከጥቃት ችና ፍጅት መከላከል ብሄራዊ አንድነት እና ደህንነትን መታደግ ነዉ!!

በዘመናት ፀረ ብሄራዊ አንድነት እና ህዝባዊ ወገንተኝነትን ወደ ጎን ገፍቶ ለሶስት ዘመናት ድር እና ማግ ሆኖ የኖረን በሀሰት እና ጥላቻ ትርክት ጨቋኝ እና ተጨቐኝ በሚል የነጻ አዉጭነት የኃይል ትግል ለግማሽ ምዕተ ዓመት የዜጎችን ደም ከማፍሰስ፣ ድሆችን ከማስለቀስ ፣ህይዎት ከመንጠቅ እና ከማስነጠቅ አልፎ የአገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ከዉጭ ጠላት ጋር ለሚያሴሩ ቁርጠኛ እና ወሳኝ እርምጃ አለመወሰድ ህዝቧን እና የአገሪቷን ችግር እና መከራ እንዲወሳሰብ  እና እንዲራዘም አድርጎታል፡፡

አሁንም በድጋሚ የምንለዉ ዓለም በሚመሰክረዉ የዘመናት የነጻነት አገር ለግል እና ለቡድን ስልጣን ብለዉ የኢትዮጵያን ሠርቶ አደር ህዝብ ልጆች ለሞት እየጋበዙ  በሚጠሏት አገር እና በሚገድሉት ህዝብ ላይ የስልጣን መንበር ምኞት ለሚያቀበዘብዛቸዉ አሁን አስካሉበት ደረጃ አስኪደርሱ ኮትኩቶ እና አርሞ ያበቃቸዉ አካል የማይታወቅበትና እና የማይጠየቅበት ምክነያት በራሱ በህዘብ እና መንግስት መካከል የሚገኝ ፈች ያጣ ዕንቆቅልሽ ሆኗል፡፡

ዕዉነት የቀደሙት በተለይም የኮ/ መንግስቱ ኃይለማርያም አስተዳደር ቢሆን እንዲህ ዓይነት የዜጎች ህይወት እና የአገር ደህንነት፣ሉዓላዊነት ላይ ……. እንዲህ የመሰለ የዓማታት ግፍ እና በደል ይቀጥል ነበር ወይ ብለንም ስንጠይቅ ጉዳዩየገደለዉ ባልሽ የሞተዉ ዉሽማሽ ሀዘንሽ ቅጥ ዐጣ ከቤትም አልወጣየሚለዉን የቀደመዉን የአገራችን ብሂል እንድናመጣዉ ተገደናል፡፡

ብናስብ ….ብናወጣ ብናወርድ ….የማይገባን ዚህች አገር ነገር  ኢትዮጵያዉያን  ከሞቱ  እና አገሪቷ ምድረ በዳ ከሆነች በኋላ በስማቸዉ የአገሪቷን ስም ለዉጠዉ ነጻ ለማዉጣት ብለዉ በስሙ ለሚነግዱበት ህዘብ ከማን የጭቆና ቀንበር እናዳላቀቁት ለመናገር እንኳን ከወዴት ሊያገኙት በማሰብ እንደሆነ ለሚያጤን ግራ አጋቢ ነዉ ፡፡

በጥላቻ እና በክፉ ምኞት ልክፍት ህዝባዊነትም ሆነ አገር ምስረታ የማይታሰብ ነዉ ፡፡ አገር እና ህዝብን የሚጠላ መሬት እና ሌላዉን ለባርነት  ሲመኝ ባለአገር እና ነጻ ኅዝብ አገሩንም ሆነ ነጻነቱን አሳልፎ በመስጠት ለባርነት እና ጭሰኝነት አሜን ብሎ አንገቱን እንዲደፋ የሚደረግ ትንቅንቅ ከሩቅ የቅኝ ግዛት ምኞት ደዌ ከተጣባቸዉ ታሪካዊ የኢትዮጵያ እና ህዝቦች ባላንጣ የሚለይ አይሆንም ፡፡

ሁላችንም ያላወቅነዉ ሠዉ በአገሩ ባርነትን እና ሞትን አሜን ብሎ የሚቀበልበት ዘመን ላይ አለመሆኑን መረሳት ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያዉያን ቀደምት ጀግኖች በሰሜን በደቡብ፣ በመስራቅ እና በምዕራብ የአግረቷ ዋልታወች የህይወት እና ደም ዋጋ ሲከፍሉ አገር ብለዉ እንጅ ክልል ብለዉ እንዳልነበር የቅርብ ዘመናት ትዉስታ ነዉ ፡፡

ይህን ቅዱስ እና ዕልፍ አዕላፍ በጎ ብሄራዊ ኩራት የሆነዉን የህዝቦችን አብሪ ገድል ለማዛባት ለዓመታት የነበረዉ ታሪክን የማወናከር እና የማሳካር ድርጊት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተደረገ ዘመቻ ዛሬም ለማስቀጠል መመኘት ለየትኛዉም ወገን የማይበጅ በመሀኑ በግልፅ እና በሀቅ  ሊወገዝ፣ ሊነነገር እና በገቢር ሊገለፅ ይገባል፡፡

ዞትር የነገሮችን ስረ መሰረት ማቃለል፣ ማለባበስም ሆነ ማድበስበስ አገር እና ህዝብን ከጥፋት እና ዉድቀት ከመከላከል ይልቅ በክህደት እና በዕብሪት ተኖልተዉ በጥላቻ ፈረስ ለሚጋልቡት ሜዳዉን ማመቻቸት ይሆናል፡፡

ለረጅም ሁለት አስርተ ዓመታት የሆነዉን እና እየሆነ ያለዉን በማንነት እና በአገር ደህንነት ላይ የደረሰዉን ጥቃት፣ በደል፣ ሞት ፣ስደት እና ሁለንተናዊ መጎሳቆል በቁርጠኝነት እና በግልፀኝነት ከመንስዔ አስከ መፍትሄ አደባባይ አለማዉጣት ጥፋት እንዲቀጥል በደል እንዲደላደል ሞት እና ስደት(መፈናቀል) እንዲለመድ ሆኖ አግባብ እና ህጋዊ አስከመምሰል ተደርሷል፡፡

አገር እንደ አገር ለመቀጠል የህዝቦች በአገራቸዉ የመኖር የመንቀሳቀስ እና ሀብት ንብረት ሰርቶ ፤አፍርቶ በማንነታቸዉ ኮርቶ የመኖር መብታቸዉ አስካልተረጋገጠ ድረስ የመንግስት ስርዓት በተቀያየረ ቁጥር  ስም በመቀያር እና ህዝብ እና መንግስት በማደናገር የሚደረግ ክፉ ምኞት የሚቻል አይሆንም ፡፡

የገጠር እና የከተማ ትግል ብሎ ተቀፅላ ስያሜ በማዉጣት በመንታ አቋም ሆኖ የቡድን ፍላጎት ለማሳካት በአገር እና ህዝብ ኪሳራ መኖር ስራየ ላሉት ዋጋ እንዲጤቁበት ከማድረግ በተጨማሪ ፀረ ህዝብ እና ፀረ አንድነት መሆናቸዉን በግልፅ እና ቀጥታ ለህዝብ እና ለዓለም አለማሳወቅ በተለይ በአሁኑ ጊዜ  ለዘመናት የነበረዉ መከራ እና ፍዳ ተባብሶ እያለ አለባብሶ እና አደባብሶ ማለፍ ልማድ መሆኑ መቆም አለበት ፡፡

ዕዉነተኛ ህዝባዊ ወገንተኝነት ያለዉ የትኛዉም አካል ህዝብን ሰርቶ አደርን በተለይም በግል እና በማህበረሰብ ማንነት እና መገለጫ ላይ  ተመስርቶ ጥቃት ፣ግዳይ/ሞት እና ዘረፋ….. አያካሂድም ይህንም የሚያደርግ  ቢኖር ባለበት ማስቆም ወይም ማክሰም በተቻለ ነበር ፡፡

ህዝብን እና አገርን አምርሮ ለሚጠላ የትግል አስተሳሰቡን፣ መነሻዉን ሆነ ግቡን እና ድርጊቱን ማለትም የጥፋት የሞት እና ግብ አልባነትየመሳሰሉትን ለህዝብ እና ለዓለም በመሳወቅ በአስተሳሰብ ማለፍ እንዲሁም በድብልቅልቅ አቋም ገጠር እና ከተማ ሆኖ በህዝብ እና በአገር ላይ የክህደት እና የጥፋት ኃይል …..በሽሙንሙን ሳይሆን ….መንግስት እና ህዝብ እኛም እሳት አለ ሊል ይገባል፡፡

ተደጋጋሚ ወቀሳ፣ከሰሳ፣ ልቅሶ እና ብሶት ለጥፋት ተጓዦች ወደ ብሄራዊ ቀዉስ ለሚያደርጉት ጉዞ  መንገድ መቀየስ፣ መምራት ጊዜ መስጠት እንዲሁም ስንቅ እና ትጥቅ ከማቀበል አይተናነስም ፡፡

ህዝብ መሪ አስተባባሪ ካገኘ ፤ህዝብ እና መንግስት አንድ ከሆነ የማይቻል የለም ፡፡  አገር ሠላም  ዉሎ የሚያድረዉ  ሁሉም ዜጋ ራሱን አካባቢዉን እና የአገሩን ዳር ድንበር ለከላከል እና ለመጠበቅ መነጋገር፣ መደማመጥ፣ መንቃት፣ መታጠቅ ፣መረዳዳት፣ መተሳሰብ መቀናጀት፣ መደራጀት  እና በአንድነት ዘብ መቆም አለበት ፡፡

 በነጻ አገር ምድር የዜጎች የግለሰብ ፣የቡድን እና የማህበረሰብ ነጻነት በማያሻማ ሁኔታ ሲጠበቅ እና ይህም ከአገር  ሉዓላዊነት ፣ የዜጎች ክብር ፣ ትስስር እና ማንነት ተቃርኖ አስከሌለበት ጊዜ ድረስ በዚህ አግባብ ብቻ  አገርን ከብሄራዊ ደህንት ስጋት፤ ህዝቧን ከጥቃት እና ፍጅት መታደግ ይቻላል ፡፡

                                        “ አንድነት ኃይላችን መነጣጠል አጥፊያችን   ነዉ ” !!!

                                                          ማላጂ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.