የጠ/ሚ አብይ ሚስቶች – አስቻለው ከበደ አበበ

ፀሐይ የሞቀውና አለም ያወቀው ነገር ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤትና የጠ/ሚ አብይ ህጋዊ ባለቤት መሆናቸውን ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት በማህበራዊ ሚዲያ ብቅ እያሉ ስለ ጠ/ሚ አብይ የትየለሌ ሚስቶች የሚነግሩን አንድ አባ የሚል መአረግ የተሸከሙ ሰው ከወደ ሰሜን ብቅ ብለዋል፡፡

እኚህ ሰው አባ ሠረቀብርሃን ወልደሳሙኤል በመባል ይታወቃሉ፡፡የዘር ፖለቲካን ከሐይማኖት ጋር እያቀላቀሉ የሚየወሩት እኚህ ሰው፣ ጠ/ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ሲወጡ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የትምርትና ስልጠና መምሪያ ክፍል ሀላፊ ነበሩ፡፡

ታጋይ-ቀሺ አባ እንደው ዝም ተብለው እንዳይታለፉ ደረጃቸውና ተጽእኖቸው ከፍ ያለ ነውና ባሉበት፣ አውስትራሊያ ይመስለኛል፣ እንሆ ተጠየቅ ብያቸዋለሁ፡፡ ግለሰቡ በብሉይ ኪዳን ታሪክ የሚታወቁትን ሟርተኛዋን ንግስትና ንጉስ፣ ኤልዛቤልና አክዓብ፣ እንደ ቅርጫ በሬ ለኤርትራና ኢትዮጵያ በየቲዩብ መልእከታቸው  ለሚሰማቸው ሁሉ ሲያካፍሉ ሰንብተዋል፡፡

በመጀመርያ ደሃን የምትጋፋና የምትናጠቀውን ሟርተኛዋ ኤሊዛቤልን ፕ/ት ኢሳያስን ነው አሉን፡፡ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ፕ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴን ከዚያም ኢትዮጵያ እራሷን ኤልዛቤል ነች ብለው አረፉት፡፡ ድፍን ኢትዮጵያ ኤልዛቤል የሆነችበት ምክንያት ደግሞ አካዓብ የሆነውን አብይን በማግባቷ ነው፡፡ይህ እንግዲህ የእሳቸው ትርጉም ነው፡፡

ተጋሩ፣ ትግራውያን ከዚህ በኋላ የአብይ ሚስት የሆነችው ኢትዮጵያን ነን እንዳይሉ መከሩ፣ ዘከሩ፡፡ ቃላቸውን የሚተላለፉትን ደግሞ ረገሙ፣ አወገዙ፡፡ እኚህ ሰው ከፍተኛ የአማራ ጥላቻ ያለቸውና እብሪታቸው   የትግራይ ተወላጆች ከሆኑት ዶ/ር ሐብተማርያም አሰፋ፣ ብስራት አማረ…የሚመደብ ነው፡፡ አባው በመንግስትና ህዝብ መካከል ያለው ግንኙነትን በባልና ሚስት መካከል እንዳለ ግንኙነት ተርከው ይበይናሉ፡፡

እኚህ ሰው የአብይ ደጋፊዎች ናቸው ብለው ያመኑባቸውን ሰዎች ሁሉ ለጠቅላዩ ድረው ሚስት ያደርጓቸዋል፡፡ ቱልቱላ ስብከቶቻቸውን ካዳመጥኩ በኋላ ይህን እንግዳ ትምህርት ከየት አመጡት ስል እራሴን ጠየቅሁ፡፡ ትንሽ የታሪክ መጽሐፍትንም ለማገላበጥ ሞከርኩ፡፡

ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ለመውረር ሦስት ግዜ የኢትዮጵያን ምድር ረግጠዋል፡፡ በአፄ ዮሐንስ 4ኛው፣ በአጼ ምኒልክ 2ኛውና በአጼ ኃይለ ስላሴ ቀዳማዊ ዘመነ መንግስት ለወረራ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡ አጼ ዮሐንስ ጣሊያንን ለመግጠም ዛሬ ጎረቤትና መንትያ እህት ሀገር ወደሆነችው ኤርትራ፣ ዶጋሊና ሰሃጢ ሲዘምቱ እንዲ ያለ ነጋሪት አስጎሽመው ነበር፤

“የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ፣ ኢትዮጵያ 1ኛ እናትህ ነች፡፡ 2ኛ ዘውድህ ነች፡፡ 3ኛ ሚስትህ ነች፡፡ 4ኛ ልጅህ ነች፡፡ 5ኛ መቀበሪያህ ነች፡፡ ሀገርህን ከጠላት ለመከላከልና ለመጠበቅ ስትነሳ የእናትን ፍቅር፣ የሚስትን ደግነት፣የልጅን ደስታ…እያሰብክ ተከተለኝ፡፡”

ዳግማዊ አጼ ምኒልክም እንደ ወንደማቸው ሁሉ የጣልያን ወረራን ለመከላከል ወደ አድዋ ለመዝመት ነጋሪት ሲያስጎስሙ አዋጁ ይህ ነበር፤

“…ለልጅህ፣ ለሚስትህና ለሐይማኖትህ ስትል ተከተለኝ፡፡…”

ከታሪክ ለመረዳት እንደምንችለው፣ ነገስታቱ እራሳቸውን የኢትዮጵያ ባል አድርገው አይመለከቱም ነበር፡፡ ምንአልባት ታጋዩ-ቀሺ አባ የማይወድቱን የአጼ ቴውድሮስ 2ኛን አባባል ይዞው ተናግረዋል እንዳይባል፣ ተምሳሌቱ አልገባቸውም ማለት ነው፡፡

እርግጥ ነው ቴውድሮስ ሲፎክር(ሲናገር አላልኩም) እንዲህ ይል ነበር፡፡

“የኢትዮጵያ ባል የእየሩሳሌም እጮኛ!” ይህም ኢትዮጵያንና እየሩሳሌምን ከኦቶማን ቱርክ ነፃ አወጣለሁ ከሚል ኢትበሃለዊ ትንቢት ተነስቶ ነው፡፡  አጼ ቴውድሮስ እኮ እተጌ ተዋበች ስትሞትም፤

እስቲ ጠይቁልኝ ርቃ ሳትሄድ

እተጌ ተዋበች ሚስት ናት ገረድ

ብሎ ሀዘኑን የገለጸ ንጉስ ነው፡፡

ታጋይ-ቀሺ አባ ሆይ ትርክተዎን ከየት አገኙት? ምን ነው ከመቶ አመታት በፊት ከነበሩትና በዘመናችን መስፈርት በፍጹም ሊለኩ ከማይገባቸው፣ እርስዎ እንዴት አንሰው ተገኙ?መቼም እንደሸብራሮቹ የወያኔ ታሪክ ተንታኞች፣ የኢትዮጵያ ነገስታተ እራሳቸውን ስዩመ እግዚአብሔር ብለው ይጠሩ ነበር እንዳይሉን፣ የመካከለኛ ዘመን የአውሮፓ ነገስታተት እራሳቸውን፣ እግዚአብሔር የመረጠው(Elect of God) ብለው ይጠሩ እንደነበር ታሪከ አንብበው ይረዱ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጥያቄ ለዶር እሌኒ ገ/መድህን - ሰለሞን ስዩም

መንግስትና ሐይማኖት ከልተለያየ መሪው ወይ ስዩመ እግዚአብሔር ነው የሚሆነው አልያም ካሊፋ ነው፡፡ ከዚያ ሲያልፍ ደግሞ እንደ ሞንጎሎ ንጉስ ጄንጂስ ካህን፤ በሰማይ ረቂቅ አምላክ አለ በምድር ደግሞ እኔ ነኝ ነው የሚሆነው፡፡ ታጋይ-ቀሺ አባ ፕ/ት ሣህልወርቅን ከኤልዛቤል ጋር ሲያመሳስሉ የነገሩን ነገር፣ ከመለስ ጋር የበላችውን ክዳ ከአካዓብ ጋር ሆናለች ይሉናል፡፡

ስውዮው እንግዲህ የኢትዮጵያ ባል መሆን ያለበት መለስ ብቻ ነው የሚሉን፡፡ እሱ ከሞተ በኋላስ? ሌጋሲ ከሚባለው ሙት መንፈሱ ጋር ኢትዮጵያን እናጋባ ወይስ ዋርሳዎቹን እነ ጌታቸው አሰፋን አቦይ፣ አቦይ እንበላቸው?

እዚህ ላይ አንድ እውነት አልዎት፡፡ ጌታቸው አሰፋ ባል ነኝ ብሎ ቢያስብ አይደል ኢትዮጵያውያኑን (አማራ፣ኦሮሞ፣ጉራጌ፣ጋሞ፣ሱማሌ…) ሲያኮላሽ የከረመው፡፡ ዛሬ ታጋይ-ቀሺ አባ በሃዘን የሚቆረቆሩላቸው ሰለነዚህ ወነጀለኞች ምንም አይሉንም፡፡ አባው በእጃቸው የያዙትን  መስቀል ትተን በልባቸው ያለውን ብንመለከት፣ የማሌሊት አርማ፤ የማጭድና መዶሻው ምስቃይ አይነት እንደሆን አያጠራጥርም፡፡

ታጋይ-ቀሺ አባ ጎነደርን፣ እኛ ጦርነት ላይ ሳለን ለምን የጥምቀትን ባዐል አከበራችሁ ሲሉ ይከሳሉ፡፡ ነገር ግን ሕዳር ጽዮንም በስፍርዋ በአማኞቿ እንደተከበረች ይታወቃል፡፡ ጌታስ ቢሆን ያለው እኮ “የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር” ነው፡፡

እንደሚመስለኝ ጠሊቁ የሳቸውን ስነ ልቦና በሳይኮ አናሊስስ ሲተነተን፣ የጠ/ሚ አብይ ሚስት ለምን የጎንደር ተወላጅ ሆነች የሚል ነው፡፡ የትግራይ ተወላጅ ብተትሆንስ ኖሮ ታጋይ- ቀሺ አባ ዝም ይሉ ነበር?

በእሳቸው እሳቤ አማራው በፖለቲካ ጋብቻ ለሚሰትነት መፈለግ ያለበት ብሔር ብቻ ነው፡፡ከዚያም በፈላጭ ቆራጭ አባዊነት፣ ማታ ማታ እግር እያጠበ፣ እግር ስሞ “ጎይታና ደቅስ”  ጌታዬ ተኛ የምትል ባርያ ሚስት መድረግ ነው፡፡ ፍርዱ ከላይ መጣ፣ እና ምን ይደረግ? በገዛ ወንድሞቻችሁ ላይ ጦርነት ከፍታችሁ፣ ወንድም የሆነውን የትግራይ ህዝብ ለመከራ ዳረጋችሁ፡፡

ጠ/ሚ አብይ እንደ ሌሎቹ ቀደምት  ኢትዮጵያውያን ነገስታት(መሪዎች) ሁሉ በእናታቸው በኩል የደረሳቸውን መገለጥ ተቀብለው፣ እራሳቸውን ብቁ ለማድረግ ለአመታት ተዘጋጅተዋል፡፡ ይህ መረጃ ከእራሳቸው አንደበት የተገኘ ነው፡፡ የጻፏቸው መጽሐፍ “ርካብና መንበር” ይህን ይመሰክራል፡፡

በመጽሐፋቸው እንደሚነበበው፣ መቼም እስራኤላዊውን ሙሴን ለአመራር ምሳሌ ያደረጉ መሪ፣  ፍፃሜያቸውን ሳምሶናዊ ያደርጋሉ ብሎ ማሰብ አላዋቂነት ነው፡፡ ስለዚህም ይመስላል ጠ/ሚ አብይ ርዋንዳ በነበሩ ግዜ ፈረንሳዊቷ ላቀረበላቸው አብረን እንሂድ ጥያቄ መልሳቸው አይሆንም የሆነው፡፡ መጨረሻቸውን የሚውቁ እንደነበር ዝግታቸውና ንግግራቸው ያረጋግጥልናል፡፡

እሳቸው ስልጣን እንደተቀበሉ ስራቸውን የጀመሩት ለእናትና ባለቤታቸው ክብር በመስጠት ነበር፡፡ ጠ/ሚሩ የሚወቀሱበት ነገሮች ቢኖሩም፣ በመድረክ ላይ እጃቸውን በካራቴ እያወናጨፉ ሲናገሩ  አላየናቸውም፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብንም እንደሚሰታቸው የሚያዩ አይመስለኝም፡፡

ታጋዩ-ቀሺ አባ የመንግስትና ህዝብ ግንኙነትን የሚያሰቡበት ርዕዮት፣ በህወሓት ዘመን ሁን ተብሎ በህዝብ ውስጥ እንዲሰርጽ የተደረገውን ነው፡፡ ይኸውም መለስ ዜናዊን እንደነ ኪምል ሱንግ ዘላለማዊ ኮሚኒስት መሪ ማድረግ ነበር፡፡ ከሞተ በኋላ እንኳን ሌጋሲ ምናምን እያሉ ሲያደናቁሩን ነበር የከረሙት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታሪክ ሲደገም! - ከኢየሩሳሌም አረአያ

የአባ ሠረቀብርሃን ኤልዛቤላዊ ትርክት፣ በተለይ አማራውን የሚመለከተው፣ የጀርመን ናዚ ትርክት ቅጂ ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ በግዜው የነበሩ የፕሮትሰታንት ስነ-መለኮት ሊቆች፣ አይሁዶችን ለማጥፋት የናዚዝም ተባባሪ ለመሆን መጽሓፍ ቀዱስን  እንደሚመቻቸው አድርገው ለመፃፍ ሞክረው ነበር፡፡

እየሱስ የአርያን ዘር ነው ከማለት አልፈው፣ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ዮሐ 8፡44 ያለውን“…እናነት ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ…” የሚለውን ጥቅስ ከአውድ ውጭ በመጥቀስ፣ አይሁዶችን አለማጥፋት የእግዘብሔር ትእዛዝን አለመቀበል ነው አስከ ማለት ደረሱ፡፡በግዜው የአይሁዶችን ተጽኖ ከጀርመን መጥፋት የሚል ተቋም እስከ ማቋቋም ደርሰው ነበር፡፡

ፋሺስት ሞሶሎኒ፣አይሁዶች በሊግ ኦፍ ኔሽን የተላለፈውን በጣሊያን ላይ የመሳሪያ ማእቀብ ውሳኔ በመደገፋቸው፣ እነደ ሲለልቪያ ፓንክረስት ያሉ አፍቅሮ ኢትዮጵያውያን የሚጽፉትን ነፃነት ለኢትዮጵያ መጣጥፍ በአይሁድ ጆረናሎች ላይ በመነፀባረቃቸውና ጃንሆይንም ሃጋና የሚባል የአይሁዶች ቡድን በስደታቸው ግዜ በመርዳቱ፣ ፀረ አይሁድነትን ከናዚዝም ቀጥሎ በማስተጋባት ሃገራችንን ማመስ ጀመረ፡፡

የአይሁድ መንግስት በፓልስታይን ዳግም ከመመስረቱ በፊት፣ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት በሚል መጠሪያ ንግስት ሳባን መረጃ አድርገው መንግስታቸውን የመሰረቱትን ኢትዮጵያውያን ለማጥፋት ፋሽስት ጣልያን አማራው ላይ ዘመተ፡፡

በጣሊያን ወረራ ወቅት፣እንደ አባ ዶዮ ያሉ ኦሮሞዎችና የሊቢያው ቡቸር ፋሺስት ጣሊያን እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣሁት ሞስሊሞችን ነፃ ለወጣ ነው ብሎ ሲነግራቸው ጉዳዩን የተገነዘቡ ሞሰሊሞች ባይኖሩ ኖሮ የአማራው መከራ የከፋ ይሆን ነበር፡፡

በአይሁዶች ላይ 1938 እ.ኤ.አ ጀርመን ውስጥ የደረሰውን የዘር ጥላቻ ጥቃት፣ ክርሰታል ናቨት፣ በሻሸመኔ ከደረሰው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ከፕሮፓጋንዳው መመሳሰል ጀምሮ፣እስከነ ፖሊስና ወጣቶቹ በመዋቅር ተጣምረው ሓይማኖትና ብሔር ላይ የተኮረ ጥቃት መፈጸማቸው  ናዚዝምን መመሪያው ያደረገ እንቅስቃሴ ኢተዮጵያ ውስጥ መኖሩን አመላክቶ አልፏል፡፡

የጠ/ሚ አብይ ደጋፊዎች ከሚናገሩት፣ በሳቸውም ዋነኛ ሚዲያ እንደሚስተጋባው. ከጀበሀ- ሻቢያ የወረሱት ይምስለኛል “ውሾቹም ይጮሃሉ፣ ግመሎቹም ይሄዳሉ” አባባል በዝብርቅርቅ ኢትዮጵያዊነት መሰረት ላይ መስርቶ በሸክላና ብረት እግሮቹ ለሚጓዝ ፖለቲካ ይቅናህ እንዳንለው ምን ያህል ኢትዮጵያን ይዞ ይጓዛል የሚለው ጥያቄ ይሞግተናል፡፡

ተቀዋሚዎቻቸው ደግሞ የሳቸውን ዘመን “ዘመነ ግርምቢጥ” ብለው ሰይመውታል፡፡ ገጣሚ እንዳለው፤

ዘመኑ ሆነና የተገላቢጦሽ

አህያ ወደቤት ውሻ ወደ ግጦሽ፡፡

በአብዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢ አህያ ለእቃ ማጓጓዣነት የሚጠቀሙበት እንስሳ ሲሆን ውሻ ደግሞ ስራው ቤት መጠበቅ ነው፡፡ምግባቸውን የሚያገኙት ደግሞ ከስራ መስኮቻቸው አካባቢ ነው፡፡ ግጥሙ የሚነግረን ነገር ቢኖር አንዱ የአንዱን ስራ ድርሻ ወስዶ እንጀራውን እየበላ መሆኑን ነው፡፡

ኢተዮጵያ በጦርነት ሳይ ሳለች የአማራና የኦሮሞ ብልጽግናዎች ሲናቆሩ ተመልክተናል፡፡ የነዚህ ፓርቲዎች ቁርቁሱ ተዋህደናል ካሉ ጀምሮ እንዳለ ነው ያለው፡፡ ብልጽግና የጋራ መድረክ ያለው አይመስልም፡፡ ከዚያ ይልቅ ብቸኛ አጣባቂው ኃይል የጠ/ሚ አብይ ሃልዎት ይመስላል፡፡ ተደምረው ከእኩል ይሆናል ምልክት ወዲያ ያላቸውን የጋራ ድምር የገባቸው ወይንም ያወቁ ለመሆናቸው ማረጋገጫ አልታየም፡፡

ጠ/ሚ አብይ መደመር ሲሉ ሁሉም ተደማሪዎች ፖሰቲቭ ኮፊሸንት ይዘው እንደቀረቡ ተደርጎ የታሰበ ይመስላል፡፡ የፖለቲካው ሂደት የሚያሳየው ግን ተቃራኒውን ነው፡፡ ፖሰቲቭ ሁለት ቁጥርን ከነገቲቭ አራት ቁጥር ጋር መደመር ጥቅሙ ምንድን ነው? ያው አጠቃላይ ውጤቱ ከዜሮ በታችና ሁለት ቁጥርን የሚያጠፋ ነው፡፡

ጠ/ሚ በጠዋት ተነስተው፣ እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያዬ ሲሉ፣ እነ እንቶኔ ተነስተው ጉምቱ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞችን ያዋርዳሉ፡፡ አንዱ ሌላውን ያንተ መደመር የእኔ የኮንፊውዝና ኮንቪንስ ቀመር ውጤት ነው ይለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢሬቻ – ህዝብ ለዋቃ ምስጋና ፣ ለወያኔ የጦር ቀጠና (ታሪኩ አባዳማ)

እንዲህ ያለ የተሳሳተ የፖለቲካ አጀንዳ ሲደጋገም የህዝብን አመኔታ ስለማይገዛ ከምርጫው በፊት እንደሆነው ሁሉ ቀውሱ ድህረ ምርጫም ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ኢትዮጵያና እስራኤል ሽብርተኝነትን ለመከላከል በጋራ እነደሚሰሩ ገለጹ ብሎ ዜና ሰርቶ ያሰደምጠናል፡፡ በተደረገውም የጋራ ትብበር የእከሌ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ሽብርተኞች ተያዙ፡፡

ይህን በሰማንበት ጆሮችን፣ የጠ/ሚ አብይ ደጋፊዎች ነን የሚሉ አክቲቪስት፣ የፖለቲካ ተንታኞች(አንዳንዴ ስለ ቴክኖሎጂ ያላቸው እውቀት ያስቃል) ሁለት ተጠባብቀው የሚኖሩ ሃገሮችን በጋራ ተጋምደው ሊያጠፉን ነው ሲሉ ይከሳሉ፡፡ እስራኤልንም ዋናዋ የኢትዮጵያ ጠላት አድርገው ይፈርጃሉ፡፡

የጠ/ሚሩ የመደመር ቀመር ግብአቶችን ብንመለከት፤ኦሮሙማ፣አሮአማራ፣ ስልጣን ተነፍገው የነበሩ ብሔሮች፣ ተገፍተናል የዘር ማጽዳት ተካሂዶብናል የሚሉ፣ ያለፈውን ላማሰቀጠልና አውራ ብሔር ለመሆን የሚቃትቱ…ናቸው

የጠ/ሚሩ ርካብና መንበር መሪ ሰዎችን እንዴት መያዝ እንዳለበትንና የኔትዎርክ መዘርጋት አስፈላጊነትን የሚገልጽበት ክፍል አለው፡፡መጽሐፉ የተጻፈው እሳቸው ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት ነው፡፡ ስልጣን ፈላጊ ነቄዎቹ የብሔር መሰላል ሙጢኞች የመረቡን ቋጠሮዎች አስቀድመው የፈተሏቸው እስኪመስል ድረስ በጠ/ሚሩ ዝምታዎች ውስጥ እራሳቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

እኒህ ወግኖች እኮ ህውሓት በመንፈስ ወይም በአካል የወለዳቸውና ያዋለዳቸው ናቸው፡፡ማን የውቃል  ቀሺ-ታጋይ አባ አራሳቸውን ለመለስ እነደዳሩት ሁሉ እነዚህኞቹ እራሳቸውን የጠ/ሚ አብይ ሚሰቶች አድርጋው እየተመለከቱ ቢሆንስ? ፍጥረታቸው እንደዛ ነውና፡፡ አንድ ግዜ ሰማይ ሊተረተር ነው፣ ምድርም ልትሰነጠቅ አያለ አዋጅ ሲያውጅ ከሰማሁት በሃታዊ እንሆ ያለንን የቃል አመሰራረትና አመጣጥ ትንታኔ ላጋራችሁ፡፡

ደላላ የሚለው ቃል የመጣው ከመጥሐፍ ቅዱስ ታሪክ ነው፡፡ ሳምሶን ፍልስጤማዊቷን ደሊላን ወደደና ከእሷ ዘንድ ተቀመጠ፡፡ ደሊላም በፍልስጤማውያን መኳንንት ተመልምላ የኃይሉን ምስጢር ደርሳበት ለነሱ ነገረቻቸው፡፡ ከዚያም ፀጉሩን ላጭተውና አይኑኑ አጥፍተው ለሞት ዳረጉት፤ ምንም እንኳን ሞቱ ለወገኖቹ ድል ቢያጎናጽፍም፡፡ ከዚያን ግዜ ጀምሮ ደሊላ ከሚለው ቃል ደላላ የሚለው ቃል ወጣ፡፡ ይህን ነገር ተጽፎ አለነበብኩትም፤ ግን እንደሰማሁት ነው ያቀረብኩት፡፡ ታዲያ እኛስ እነዚህ እራሳቸውን እንደ ጠ/ሚሩ ሚስቶች በግብራቸው  የሚገልጹ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች፣ የጠ/ሚ አብይ ደሊላዎች ብለን ብንጠራቸው፣ አይገልጻቸውምን?

አንድ ግዜ አንድ ገበሬ በሬዎቹን ጠምዶ ሲያርስ አንዱ በሬ እግሩ ሽንቁር ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ  ተሰበረ፡፡የገበሬው ውሻ እርሻ ሜዳው ላይ ኖራ ኖሮ፣ከደህነኛው ጋር አቀናጅተህ እረስብኝ አለች አሉ፡፡ ሁለት የተለያየ ጉልበት ያላቸውን በሬዎች ጠምዶ ማረስ ምንኛ ፈታኝ እንደሆነ የሚያውቀው ገበሬ፣ ውሻ ምን አገባሽ በእርሻ አላት አሉ፡፡ ወንጀል ሲፈፀም እያዩ እንዳላየ ማለፍ፣ ሁሉንም አጣምዶ የለ ግልጽ ትልም መጓዝ ከማስጠየቁም ባሻገር ውድቀትን ማስከተሉ አይቀርምና ይታሰብበት፡፡

በመጨረሻም ስለ ውሻ

ግመሎቹ ሲመጡ አይቶ የጮኸው ውሻ፣ ስራው ባለቤቱን መጠበቅ ነውና እንግዳ ነገርና ክስተት ባየ ቁጥር ነቁ ሲል ይጣራል፡፡ በታማኝነት ባለቤቱን የሚያገለግለው ውሻ፣ ምግብ እንኳን ባይሰጠው ሜዳ ለሜዳ ተዘዋውሮ ያገኘውን በልቶ ወደ ባለቤቱ ይመለሳል፡፡ የባለቤቱን ጭንቀት የማይወደው ውሻ በችግሩ ሁሉ ለመድረስ ትከሻውን ዝቅ አድርጎ ቀንበር ይሸከማል፡፡ ክብር ለውሻ…!

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜተሮ ቫንኩቨር ካናዳ

 

2 Comments

 1. ይኸውላችሁ ጉዱ ገና ነው! ” Little knowledge is dangerous ” ይላሉ ፈረንጆች!!

  በመፅሀፉ ሚስቶቼ ስላለን
  የእኛ ጠቅላይ በኮድ መናገሩ ነው መሰለኝ ሚስቶቼ ናችሁ አለን እኛን! መፅሀፍ የባረቀባቸውን ሲያማልል!!
  ጠቅላዩ የመደመር መንገድ ላይ የፃፈውን እባካችሁ አትንገሩን ተከድኖ ይብሰል! አድክም ነው!

 2. It is good to have our own say in any subject we want to say about . It is equally good not to say anything because our emotion tells us to do so . It is so desirable to to try hard to see things in a critical and balanced way if we have to make sense and make some sort of positive difference as far as the very question of the absence if democratic and basic human rights is concerned.
  I agree with the very argument that we must be aware enough about foreign powers intervention in the internal affairs of not only our country but also every other country . We are not exceptions of the very hard political game of the world . The only way out is to establish a political system that runs on the very democratic values and practices so that all other sectors of economic and social developments can become fruitful .
  Blaming others without doing one!s homework is really a political stupidity .
  The writer says that the prime minister praised his wife . That was great ! But not doing what he was and us supposed to do for the last three years dose not show that he is a man of his words at all! The way he behaved and acted while
  so many wives , mothers , sisters , and innocent citizens were and are going through unimaginable suffering shows that he is not a man of words and actions but a man of endlessly stupid rhetoric ! He does not have even a sense humanity as I have never seen him with sign of tears in his eyes and on his cheeks when hundreds were murdered and buried in mass without any presence if respect that could say goodbye ! That is way your sympathy to him is so clumsy if not politically idiotic !

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.