ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን መኖር የሚችል ማሰብ ያቆመ ብቻ ነው! – አምባቸው ደጀኔ

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ martyrof2011@gmail.com)

ማሰብ ሲባል ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ስለፍቅረኛህ፣ ስለሚስትህ/ስለባልሽ፣ ስለሥራህ፣ ስለወደፊት ሕይወትህ ወዘተ. ልታስብ/ቢ ትችላለህ/ያለሽ፡፡ ሰው ሆኖ የማያስብ የለም፤ ሃሳቡ ቢለያይም፡፡

እኔ የምለው ማሰብ ግን ከራስ ባለፈ ስለሰው ልጅና ስለዓለም፣ ስለማኅበረሰብና ስለአገር ኅልውና በአጠቃላይ ከአንድ ጤናማ ዜጋ የሚጠበቀውን ጤናማ የማሰብ ችሎታ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ካየነው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ መኖር የሚችል ሰው ከራሱ የዕለት ከዕለት ኑሮ ባለፈ ስለሀገርም ሆነ ስለሕዝብ ምንም ማሰብ የማይችል ልቦናው የተደፈነና አእምሮው የዛገ መሆን አለበት፡፡ አእምሮው የሚሠራና ልቦናው የሚያመዛዝን ከሆነ ተራው የዕለት ከዕለት ኢኮኖሚያዊ ሕይወት የሚከብደው ከመሆኑም ባሻገር በሀገር ጉዳይ በሚገጥመው ጭንቀት ብቻ ኅሊናውን ስቶ ሊያብድም ይችላል፡፡

በበኩሌ እንደ ኤርየል ሻሮል መሆንም ያምረኛል፡፡ ኤርየል ሻሮል የእስራኤል ፕሬዝደንት የነበረና ከአምስት ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ሰመመን ውስጥ ቆይቶ ይህችን ዓለም የተሰናበተ ሰው ነው፡፡ ለበርካታ ዓመታት ሳይሰማና ሳይለማ በህክምና ድጋፍ ሰመመን ውስጥ ገብቶ ሲረዳ ነበር፡፡ እኔም ልክ እንደዚያ ሰው ሰመመን ውስጥ ገብቼ ኢትዮጵያ ስትነሳ ብነቃ ደስታው አይቻለኝም፡፡ የሚገርም ዘመን ላይ ነን፡፡

ከተማ ይፍሩ የተባለ የደርግ ዘመን አንድ ሚንስትር ለሥራ ጉዳይ ይመስለኛል ከሀገር ወጥቶ በዚያው በጠፋበት ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር ይባላል – “Fly out of Ethiopia while you can!” እኔ ደግሞ “እንደዚያ ማለትስ አሁን ነበር” እላለሁ፡፡ የአሁኑ ሁኔታችን ለመጥፋት ከመመኘትም የዘለለ ነውና፡፡

  1. “ለአዲስ አበባ ፋንዲያ ያስፈልጋታል” የሚል የሀገርም በለው የክልል ኩታራ መሪ ጋር ተቻችለህም ይሁን ተስማምተህ እንዴት ትኖራለህ? በአንድ በኩል “ስንኖር ኢትዮጵያ፣ ስንሞትም ኢትዮጵያ” እያለህ በሌላ በኩል በምሥጢር በሚያደራጃቸው ዐረመኔና ቦቅቧቃ ታጣቂዎቹ አማራን ከያለበት ከሚያሳርድ የአናኮንዳ ዝርያ እባብ ጋር እንዴት በአንድ ሀገር ዜግነት አብረህ ትኖራለህ? በአንድ በኩል “ኢትዮጵያ ሱሴ ናት” እያለህ በሌላ በኩል ከሶማሊያና ከአርሲ፣ ከባሌና ከወለጋ ኦሮሞን በገፍ እያመጣ የአዲስ አበባን ቀደምት ነዋሪዎች በማፈናቀል የከተማዋን የሕዝብ አሰፋፈር በቅጽበት ከሚለውጥ አጭበርባሪ ጋር እንዴት ኅብረት ይኖርሃል? “ተረኝነት የለም” እያሉህ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሥልጣንና የሀብት ምንጭ በቂ ትምህርትና ዕውቀት በሌላቸው የሀገር ቤት ኦሮሞዎች ከሚያሲዙና አንተን በገዛ ሀገርህ ባይተዋር ከሚያደርጉህ “ሰዎች” ጋር እንዴት አብረህ ትኖራለህ? ጉድ ነው ዘንድሮ! …
  2. አንዲት ከተማ የሁለት አገሮች ዋና ከተማ የምትሆነው በምን ሥሌት ነው? አንዲት ከተማ በሁለት ስም እየተጠራች ሰሚን ግራ የምታጋባበት ሀገር ያለው በየትኛው ክፍለ ዓለም ነው? አዲስ አበባን ለማጥፋት እየተካሄደ ያለው የኦሮሙማ ሁለገብ ዘመቻ መቼና በማን ይቆማል? ዝርዝሩ ብዙ ነው! አሁን አሁን እኮ አዲስ አበባ ላይ እየኖርክ የሀገር ባቤትነትና የዜግነት ስሜት ሊኖርህ በፍጹም አይችልም፡፡ እ ለምሣሌ አዲስ አበባ ከመጣ 40 ዓመት ከአራት ወር ሆነኝ – ጃዋር ሳይወለድ ማለት ነው፡፡ አዳነች አቤቤ ሳትጸነስ ማለት ነው፡፡ አቢይ አንቀልባ ላይ እያለ መሆኑ ነው … ተመልከት! አሁን እነዚህ አስተዳደግ የበደላቸው የኦነግና የሕወሓት ሥሪቶች እኔን ከአዲስ አበባ ሊያስወጡ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
  3. አክራሪ ኦሮሞ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ የናጠጠ ሀብታም እየሆነ ነው፡፡ ስማቸውን እንኳን አስተካክለው የማይጠሯቸው “ሪቮሉሽን” እና “ሐመር” የተሰኙ ቅንጡ ዘመናዊ መኪኖችን እያሽከረከሩ ምድርን ተጠይፈው ሰማይ ወጥተዋል፡፡ የአዲስ አበባ መሬት በኦሮሞ እየተወረረና እየተቸበቸበ ሌላው ሙልጭ ሲወጣ እነሱ በአንድ አዳር መክበርን ሥራየ ብለው ተያይዘውታል፡፡ በዚያ ላይ ቀበሌውን፣ ወረዳውን፣ ከፍተኛውን …. ሁሉንም እነሱ ስለያዙት የዘረፉትን ሀብትና ንብረት ህጋዊ መደላድል ለመስጠት አይቸገሩም፡፡ በበታችነት ስሜት ራሱን ያጎሳቆለ ሰው ከሚያደርሰው ጥቃት አምላክ ይጠብቅ፡፡ በሙስናው ረገድም ዐይን ያወጡ ሆነዋል፡፡ ለምሣሌ አሥር ሽህ ብር ለምታገኝበት ጉዳይ 50 ሽህ ብር ጉቦ ቢጠይቁህ ከዕውቀት የጸዱ በመሆናቸው ስታስረዳቸው “ኡሱ ያንቴ ጉዳይ ነው” ብለው ያመናጭቁሃል እንጂ አይረዱህም ማለትም አይገነዘቡህም፡፡ ለመጽናናት ያህል ሀገር አለች እንላለን እንጂ ከፈራረሰች ቆየች፡፡
  4. አዲስ አበባ ልትፈነዳ ነው፡፡ መኪና መንገዶች በሁሉም ዓይነት ተሸከርካሪዎች ጢም ብለዋል፡፡ በሥራ ሰዓትም ከሥራ ሰዓት ውጪም መኪናና ሰው እንደጉድ ይርመሰመሳል፡፡ የሁሉም ዜጎች መሸሻ አዲስ አበባ እንደመሆኗ ከየትም አቅጣጫ በሚተሙ ዜጎች እየሞላች ልትፈነዳ ተቃርባለች፡፡ የትራፊክ እንቅስቃሴው ከመኪናና ከሰው መንገዶች አቅም በላይ ሆኗል – የመንግሥትና የፖለቲከኞች ትኩረት ግን የሕዝብ ችግር ላይ ሳይሆን ሥልጣን ላይ ሆነና ነገሩ ሁሉ “የነብር ዐይን ወደ ፍየል፣ የፍየል ዐይን ወደ ቅጠል” እንዲሉ ሆኖ ሀገራችን ወደማይቀርላት አርማጌዴዖን እያመራች ይመስላል፡፡ የመኪኖችን ሞዴል በተመለከተ አንዳንዶቹ ዘመናዊ መኪኖች አሜሪካና አውሮፓ ስለመኖራቸውም ያጠራጥራል፡፡ ሀበሻ ማንነቱን የሚያሳውቀው፣ ጅብዱን የሚያሳየው ቆንጆ መኪና በመያዙ፣ ቆንጆ ቤት በመሥራቱና ቆንጆ ሚስት በማግባቱ/ሀብታም ባል በማግባቷ ይመስላል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖርህን በሚያጠራጥር ሁኔታ የሀብት ውድድሩ ጦፏል (በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ድሃ አፈር ደቼ እየበላ የእህቱን ሠርግ በ40 እና 50 ሚሊዮን ብር ድል አድርጎ የሚደግስ ደንቆሮ ሀብታም የምታገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው፤ የከበረው ደግሞ ድሆችን እንደትኋን ደማቸውን መጥጦና ስንጥቅ አትርፎ በጥቂት ዓመታት ውስጥ መሆኑን ስትረዳ ይበልጥ ያምሃል)፡፡ በዚህ መሀል አብዛኛው ድሃ በቁሙ መቀመቅ እየገባ ነው፡፡ በየደቂቃው ሽቅብ ወደሰማየ ሰማያት የሚወነጨፈው ሰው ሠራሹ የኑሮ ውድነት ደግሞ በቃላት የሚገለጽ አይደለም፡፡ ዛሬ ሁለት መቶ ብር የገዛኸውን ዕቃ ከሦስት ቀናት በኋላ ከአንድ ሽህ ብር በላይ ልትጠየቅበት ትችላለህ፡፡ ሁለት ምርጫ አለህ – ካለህ መግዛት፤ ከሌለህ ትተህ መሄድ ነው፡፡ መተዛዘንና መተሳሰብ በሀገራችን መዝገበ ቃላት ውስጥም የሉም፤ ጠፍተዋል፡፡ ዐውሬነት ነው የነገሠው፤ ጅብነት ነው እግር አውጥቶ እየተራመደ የሚታየው፡፡ ዋጋን የሚያረጋጋና ለምሥኪን ዜጎች “አለሁላችሁ” የሚል መንግሥትም ሆነ የግል ድርጅት የለም፡፡ ሃይማኖቱም የተዘፈቀው በብልጽግና አስተሳሰብ ነው፤ መንግሥትም የብልጽና ወንጌል ተከታይ ነው – ሁሉም ድሃ ጠል ናቸው፡፡ አቅልን የሳተ የሥጋ ሩጫ በሀገራችን ተንሰራፍቶ ኅሊናና ነፍስ ጫጭተዋል፡፡
  5. የመንግሥት ባለሥልጣናት በደሞዝ ስለማይኖሩ አቶ ደሞዝን ከነመፈጠሩ ረስተዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛ በሁለት ሽህ ደሞዝ የሃያ አምስት ሽህ ኑሮ እንዲኖር እየተገደደ ነው፡፡ ሀገራችን በኳስ አበደች የውቂው ደብልቂው ዕብደት ላይ ትገኛለች፡፡ ኩንታል ነጭ ጤፍ አምስት ሽህ ብርን ካለፈ ሰነበተ፤ አንድ ሊትር ዘይት 100 ብርን ከዘለለ ቆዬ፤ ስንቱን አንስተን እንዘልቀዋለን? ሕዝብ ርስ በርሱ ተባልቶ ሊያልቅ ነው፡፡ ሮሮ ቢበዛም መንግሥትም እግዚአብሔሩም ከተደበቁበት ብቅ ብለው የድሃን ጩኸት ሊሰሙ አልቻሉም፡፡ ህግ የለም፡፡ ሥርዓት የለም፡፡ የተፈጥሮ ህግ ብቻ እስካሁን አልተዛነፈም – ይነጋል፤ ይመሻል፡፡ ፀሐይ በምሥራቅ ትወጣለች፤ በምዕራብ ትገባለች፡፡ በተረፈ የመንግሥት ህግ ብሎ ነገር የለም፤ በገንዘብና በዘረኝነት፣ በአምቻና ጋብቻ፣ በዘመድ አዝማድና በትውውቅ የማይደረመስ ህግና የወንጀል/የፍትሐ ብሔር አንቀጽ የለም፡፡ ገንዘብህን ይጭነቀው እንጂ ገድለህ በሟች ልታስፈርድ ትችላለህ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያው ሄዝቦላ!! ‹‹የጥቅምት 24/2013 የሽብር ጥቃት 1ኛ ዓመት መታሰቢያ›› - ክፍል 2

ለማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ከፈለግህ ጭንቅላትህን ሣጥን ውስጥ ቆልፈህ እንደመጋጃ ከብት ማንም የሚጭንህን ለመሸከም ፈቃደኛ ሆነህ መገኘት አለብህ፡፡ አለበለዚያ አስባለሁ ካልክ ማምሻህን ወይም ዘገየህ ቢባል በማግሥቱ ራስህን የምታገኘው ደህና ዘመድ ያለህ ከሆንክ አማኑኤል ሆስፒታል አለበለዚያ በሚቀርብህ ባቡር መንገድ ላይ ራቁትህን ሆነህ የትራፊክ እንቅስቃሴን በበጎ ፈቃደኝነት ስታስተናግድ ነው – ማንም ላይሰማህና ትዕዛዝህን ላያከብር፡፡ ኢትዮጵያ ይህን መስላልሃለች፡፡ “እግዜር ሲቆጣ ሽመል አይቆርጥም፤ ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም” ይባላል፡፡ የኛም ነገር እንደዚያው ነው፡፡ እንትናቸውን በቅጡ ያልጠረጉ ውሪና ዘረኛ መሪዎችን ጫንቃችን ላይ አሸከመንና ገደል መግባታችን ግድ ሊሆን ነው፡፡ አዳሜ ታዲያ ቢጨንቀው ወይም የበላው ቢያብላላው የአጋንንቱን ልዑክ እያመለከ “ጊዜ እንስጠው፤ ወዶ አይደለም፤ ታስሮ ነው፤ አላሠራ ብለውት ነው….” እያለ ራሱን ያታልላል፤ ሌላውንም በዶሮ-ማታ ሊያሞኝ ይሞክራል፡ የተደገሰልን የሚለበልብና የሚሰነፍጥ የበርበሬና የሰናፍጭ ግብዣ ከፊት ለፊታችን አለ፤ መልካም ድግስ እንዲሆንልን ለሁላችን እየተመኘሁ ለዛሬ ተሰናበትኩ፡፡ አሻም!

4 Comments

  1. One major problem is the poor got no access to the banking system while at the same time the government is forcing the rich to have little access to cash. The way it is going with the little amount of cash Ethiopians are allowed to withdraw each day to have outside their bank account on their person , on hand or in their pockets outside of the bank left us Addis Ababa rich people no other choice but to give blind eyes to the poor even if we did not want to.

    Those of us the few , hundreds of years generations Addis Ababa residents who are economically fortunate/rich are having a hard time in finding ways to help the poor because many of the poor do not have valid ID cards or bank accounts in Addis Ababa. We cannot write a check to the poor because the system does not even know them or cash the check for them. Census count had been skipped repeatedly so no one really knows how many poor are roaming the streets of Addis Ababa with no form of ID cards. We the rich write checks for this charity and for that charity in Addis Ababa but most often we get disappointed with the money ending up being pocketed by the very people in the charity buying cars mentioned above hammers and revolutions for themselves with the money that was supposed to go to the poor. If we the none Oromos generations of Moa Anbessa organize Addis Ababa residents to form a charity or other form of organization in Addis Ababa you know the government will throw us in jail. So after thinking about it as the writer above wrote , the government made it seem like the only option left for people of Addis Ababa and beyond is not to think. They stole and are stealing a lot of material things from us but I will not allow them to steal my head too. I rather die thinking than live like an animal without thinking. I will not let them turn me into them. They don’t think , they just let the tedemari think for them. That’s why they are busy recruiting tedemaris , they can not last one second on their own stagnant thinking . Writing book after book on Medemer only for their family members to prosper is criminal. Before this constitution was put in place Ethiopia gave chance for all to prosper , now it is not like that .

  2. የወቅቱን ሁናቴ በትክክል ያስቀመጠ ወይም የገለጠ ግሩም እጥር ምጥን ያለ ጽሑፍ ነው። ሰሚ ቢገኝ። እግዜር ይድረስልን እንጅ እንደነሱ አያያዝ ከሆነስ መላም የለን። ግን የእግዜሩ ይበልጣልና ተሥፋ መቁረጥም አይገባም። ይልቁንስ ወደሱው መመለስና ጸሎትና ምህላ መያዝ ነው የሚያዋጣው። የታሰረን የሚፈታ፣ የተዘጋን የሚከፍት፣ ጨለማን ገፎ ብርሃንን የሚሰጥ፣ ፈርዖናውያንን በባህር አስምጦ ግፉኣንን ከባርነት ቀምበር ነፃ ማውጣት የሚችል … አንድ አምላክ ነውና በሰው መመካቱን ትተን በርሱ እንመካ፤ ወደርሱም ሙጥናን እንበል። ውጤቱን ያኔ እናየዋለን። የወያኔን የ46 ዓመት ዕብሪት በ46 ቀናት የሰባበረ የጌቶች ጌታ የነዚህን ትዕቢት በደቂቃዎች ማሥተንፈስ አይገደውምና ከክፋትና ከተንኮል ተቆጥበን እንጸልይ። አመሰግናለሁ።

  3. In a very short expression, this so called Dr Abiy of Ethiopian pm is not only devil-incarnate; he is rather Devil himself. I can’t understand why people like dn Daniel Kibret and Prof. Birhanu Nega sympathize with this guy. He doesn’t show even a slightest empathy and/or remorse for the nonstop massacre of the innocent Amharas in Wolega and elsrwhere and the Tigrians on warzone Tigray. I think the worst will come if this guy stays in power.
    God bless Ethiopia!!

  4. እንዲህ ነው ማለፊያ ሃሳብና ጽሁፍ ሲገጣጠሙ። አዎን ማሰብ ያቆመ የሚኖርባት ምድር። ለእኔ ለእኔ ብቻ። ትላንት የተገፋው ገፊ፤ የትላንቱ አሳሪ ታሳሪ፤ ያኔም ያለቀሱ አይኖች ዛሬም የሚያነቡባት፤ ሰው ፈጣሪን ለመማጸን በቤ/ክርስቲያን ስር እያለ የሚረሸንባት፤ ሰው ለስብሰባ ተጠርቶ በመትረጌስ የሚታጨድባት በብሄር በሰከሩ እብዶች ምድሪቷ የምትናወጥበት ጊዜ ላይ ነበርን ዛሬም ነን። የጸሃይ ግርዶሽን ተመልክቶ የዓለም ፍጻሜ ሊሆን ነው ከሚል፤ የፈጠራ ወሬን ጨብጦ ትንፋሽ እያጠረው ወሬ ነጋሪ የሆነው፤ የወንድምና የእህቱን ደም ለራሱ የፓለቲካ ንግድ የገበረውና የሚገብረው ያ ነጻነትን አመጣለሁ ብሎ ባርነትን ያመጣ የሙታን የፓለቲካ ስብስብ ትወና እና እውነታ ከተጋጩበት ዘመን አለፈ። በሃበሻ ምድር ለመኖር ወፈፌ መሆን በቂ ነው። ማሰብ የቻሉና ዘመን አሻጋሪ ሃሳብ ያላቸው ወገኖቻችን በየጊዜው ገዢዎች አፈር ተመልሶባቸዋል።
    ይህች ጉድ የማይነጥፍባት የሃበሻ ምድር ሁሉ ታሪክ ጸሃፊ፤ ሁሉ ጦረኛ፤ ሁሉ በዘሩና በክልሉ ዙሪያ የሚያሽካካባት የሰው ጅቦች እንዳሻቸው የሚራወጡባት መሬት ናት። የሚያሳዝነው ከጎኑ ካለው ወንድምና እህቱ ይልቅ የነጭና የአረብ ምክር ሰሚ ልክ ለዘመናት እንደቀለድብን አሁንም የእነርሱ መሳሪያ ለመሆን ስንሰለፍ የምታይ ያቺ ነፍስ ማልቀስ ይነሳት? እውቋ የዓለም አጫዋች አስቴር አወቀ “ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ” እንዳለችው እየሆነ ነው። የአሲምባ ፍቅር በሚለው መጽሃፉ ላይ ካህሣይ አብርሃ ብስራት – ይመር ንጉሤን ከዘመናት በህዋላ ፍለጋ ያስኬደው ዘርና ቋንቋውን ፍለጋ አይደለም። የዛን ጀግና ስብዕናና መስዋ ዕትነት በህይወት መኖርና አለመኖር ለማወቅ እንጂ። አሁን ባለው የዘር ቆጠራ ቢሆን ኑሮ ክህሣይን ወደዚያ የሚወስደው የለም። ዘርን ያለተሻገረ የፓለቲካ እይታ የሻገተ ሃሳብ ነውና!
    አቶ አምባቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት ገጣሚውም እንዲህ ብሎ ነበር
    ለመኖር ነው እንጂ የነገን ለማየት ጀሮዬ እንዳልሰማ አይኔም እንዳላየ ዝም ብዬ የማልፍ
    የሚቀጥለው ቀን ትላንትን ተላብሶ መኖሬን አስጠላኝ አልቀየር ብሎ።
    ከራስ ጋር መዋጋት ይቅርብኝ እንዳላልኩ አሁን ቢብስብኝ ዝምታዬን ሰበርኩ።
    በሉ ተጠራሩ ኑ እና እንሰባሰብ ቀኑን እንፋለም እንግፋው ተባብረን
    ማዘንበሉን ትቶ ቀና ብሎ እስኪሄድ እውነትን እያየ በእውነት ላይ እስኪፈርድ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share