አደዋ –   ማላጂ

ዛሬ የአደዋን ፻፳፭ የድል በዓል ማክበር የወራሪ እና ተስፋፍዎችን  ሽነፈት እና ሞት ብቻ ሳይሆን የዉስጥ ምንደኞች እና ቅጥረኞች  የአገርን ልዑላዊነት እና የህዝብ ማንነትን ለማዛባት የታሪክ ምስቅልቅል እና የክህደት ህልም ላለሙት እና ለሚያልሙትም በአገሩ ነጻነት እና በማንነቱ የማይደራደር  ኩሩዉ ኢትዮጵያዉ ትዉልድ በገቢር ለዉስጥ እና ለዉጭ ታሪካዊ ጠላቶች  ለዓለም ህዝብ ያሳየበት ዓመት መሆኑን ድሉን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል ፡፡

ትናንት“ አበዉ ቀን የሰጠዉ ቅል ድንጊያ ይሰብራል” እንዲሉ  ስለ ኢትዮጵያዊነት ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት ፣ነጻነት፣ ክብር ፣ ስለጀግኖች በደም እና ህይዎት  የተፃፈ ደማቅ  እና እንደንጋት ኮከብ የሚያበራ ዘላለማዊ ክብር እና ልዕልና የሚገባቸዉን ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ ባለዉለታወችን  ምግባር እና ተግባር በመበረዝ እና በመደለዝ ትዉልድ እና አገር ሲያደናግሩ ለራሳቸዉ የማይነጥፍ   ርካሽ  የቁሳቁስ  ትርፍ እና ዉዳሴ ላለፉት  ግማሽ ምዕተ ዓመት  ሲያጋብሱ ለነበሩት መሪር ሀዘን እንደሚሆንባቸዉ ሳይታለም የሚታወቅ ሀቅ ነዉ ፡፡

እናም ድል ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ፤ ዘላለማዊ ክብር እና ምስጋና  ለዕምየ ሚኒሊክ እና ለሁሉም በጊዜዉ ለነበሩ እና ላለፉ ጀግኖች የእኛዎች  እያልን  የኢትዮጵያዉያን ነፃነት እና ለባርነት እምቢባይነት ለሚመራቸዉ  የሩቅ እና የቅርብ ምንዱባን በኢትዮጵያ ምድር ሆኖ ጥላቻ እና የበታችነት ስሜት ማስተጋባት መቻል ጀግኖች ቀደምት አባቶች  በደም እና በአጥንት በሰሯት እናት ምድር አገር  እርሷም የአበሻ  አገር  ለዘላለም ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር ከመተባበር ዉጭ ሌላዉ እንደማያዋጣ ሊታወቅ ይገባል ፡፡

 

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፣

ግብሩ ዕንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከማንነትና ከክልል አስተዳደር ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችና በኃይል ለመፍታት መሞከር የተጀመረውን የለውጥ ሒደት ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱንም ጭምር አደጋ ላይ እንደሚጥል ተገለጸ

የዕምየ ልጅ ሆነን  ያዉም የምኒልክ  የጥቁር  ሠዉ ልጆች የነጻነት ዓርማ ፣

ዛሬም አበሻ ሆይ  ለራስህ ነጻነት ለዚች አንዲት አገር  ፣

ዕምቢ ለናት ምድር ፤ ዕምቢ ለነጻነት በማለት ተስማማ ፡፡

 

ለመላዉ የዓለም የሠዉ ልጆች  እንኳን ለ፻፳፭ኛዉ የድል እና ነጻነት ዕለት አደረሰን !!!

“ዘላለማዊ ክብር እና ሞገስ በህይወት እና ደም ዋጋ አገር ሰርተዉ ፤ ለአገር ኖረዉ ላለፉት  ቀደምት  ዋኖቻችን ”!!!

 

ማላጂ

   “የዓደዋ (፻፳፭ ኛዉ ) ድል ነጻነት እና ተጋድሎ የጥቁር ሠዉ ዘር ትንሳዔ ነዉ   !!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share